39 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ተነስቶ አብሯቸው ሄደ። እዚያም ሲደርስ ደርብ ላይ ወደሚገኘው ክፍል ይዘውት ወጡ፤ መበለቶቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው እያለቀሱ ዶርቃ ከእነሱ ጋር በነበረችበት ጊዜ የሠራቻቸውን በርካታ ልብሶችና ቀሚሶች ያሳዩት ነበር። 40 ጴጥሮስም ሁሉም እንዲወጡ ካደረገ በኋላ+ ተንበርክኮ ጸለየ። ከዚያም ወደ አስከሬኑ ዞር ብሎ “ጣቢታ፣ ተነሽ!” አለ። እሷም ዓይኖቿን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች።+