18 ልጆቼ ሆይ፣ ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ እንደሰማችሁትም ፀረ ክርስቶስ እየመጣ ነው፤+ አሁንም እንኳ ብዙ ፀረ ክርስቶሶች መጥተዋል፤+ ከዚህም በመነሳት ይህ የመጨረሻው ሰዓት መሆኑን እናውቃለን። 19 በእኛ መካከል ነበሩ፤ ሆኖም ከእኛ ወገን ስላልነበሩ ትተውን ሄደዋል።+ ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር። ሆኖም ከእኛ ወገን የሆኑት ሁሉም አለመሆናቸው በግልጽ ይታይ ዘንድ ከእኛ ተለይተው ወጡ።+