-
ገላትያ 1:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ለአባቶቼ ወግ ከፍተኛ ቅንዓት ስለነበረኝ ከወገኖቼ መካከል በእኔ ዕድሜ ካሉት ከብዙዎቹ የበለጠ በአይሁዳውያን ሃይማኖት የላቀ እድገት እያደረግኩ ነበር።+
-
-
ፊልጵስዩስ 3:4-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ይሁንና በሥጋ የምመካበት ነገር አለኝ የሚል ማንም ቢኖር ያ ሰው እኔ ነኝ።
በሥጋ የሚመካበት ነገር እንዳለው አድርጎ የሚያስብ ሌላ ማንም ሰው ቢኖር እኔ እበልጣለሁ፦ 5 በስምንተኛው ቀን የተገረዝኩና+ ከእስራኤል ብሔር፣ ከቢንያም ነገድ የተገኘሁ ስሆን ከዕብራውያን የተወለድኩ ዕብራዊ ነኝ፤+ ስለ ሕግ ከተነሳ ፈሪሳዊ ነበርኩ፤+ 6 ስለ ቅንዓት ከተነሳ በጉባኤው ላይ ስደት አደርስ ነበር፤+ ሕጉን በመታዘዝ ስለሚገኘው ጽድቅ ከተነሳ ደግሞ እንከን የማይገኝብኝ መሆኔን አስመሥክሬአለሁ።
-