-
የሐዋርያት ሥራ 9:3-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 እየተጓዘም ሳለ ወደ ደማስቆ ሲቃረብ ድንገት ከሰማይ የመጣ ብርሃን በዙሪያው አንጸባረቀ፤+ 4 እሱም መሬት ላይ ወደቀ፤ ከዚያም “ሳኦል፣ ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ። 5 ሳኦልም “ጌታዬ፣ አንተ ማን ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም እንዲህ አለው፦ “እኔ አንተ የምታሳድደኝ+ ኢየሱስ ነኝ።+ 6 አሁን ተነስተህ ወደ ከተማዋ ግባ፤ ምን ማድረግ እንዳለብህም ይነገርሃል።” 7 አብረው እየተጓዙ የነበሩትም ሰዎች ድምፅ የሰሙ ቢሆንም ማንንም ባለማየታቸው የሚናገሩት ጠፍቷቸው ዝም ብለው ቆሙ።+ 8 ሳኦልም ከወደቀበት ተነሳ፤ ዓይኖቹ ቢገለጡም ምንም ነገር ማየት አልቻለም። በመሆኑም እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ ወሰዱት።
-