የሐዋርያት ሥራ 5:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ሐዋርያትንም ይዘው እስር ቤት ከተቷቸው።+ 19 ይሁን እንጂ ሌሊት የይሖዋ* መልአክ የእስር ቤቱን በሮች ከፍቶ+ አወጣቸውና እንዲህ አላቸው፦ ዕብራውያን 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በተጨማሪም ስለ መላእክት ሲናገር “መላእክቱን መናፍስት፣ አገልጋዮቹን*+ ደግሞ የእሳት ነበልባል ያደርጋል”+ ይላል። ዕብራውያን 1:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ሁሉም መዳን የሚወርሱትን እንዲያገለግሉ የሚላኩ ቅዱስ አገልግሎት* የሚያከናውኑ መናፍስት አይደሉም?+