ዕንባቆም 2:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ኩሩ የሆነውን ተመልከት፤*ውስጡ ቀና አይደለም። ጻድቅ ግን በታማኝነቱ* በሕይወት ይኖራል።+ ገላትያ 3:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በተጨማሪም “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሎ ስለተጻፈ+ በአምላክ ፊት ማንም በሕግ አማካኝነት ጻድቅ ሊባል እንደማይችል ግልጽ ነው።+ ዕብራውያን 10:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 “ሆኖም ጻድቅ አገልጋዬ በእምነት ይኖራል”፤+ ደግሞም “ወደኋላ ቢያፈገፍግ በእሱ ደስ አልሰኝም።”*+