2 በመንፈስ የተነገረው ቃል ከአምላክ የመነጨ መሆኑን በዚህ ማወቅ ትችላላችሁ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የሚመሠክር በመንፈስ የተነገረ ቃል ሁሉ ከአምላክ የመነጨ ነው።+ 3 ሆኖም ስለ ኢየሱስ የማይመሠክር በመንፈስ የተነገረ ቃል ሁሉ ከአምላክ የሚመነጭ አይደለም።+ ይህ በመንፈስ የተነገረ ቃል ከፀረ ክርስቶስ የሚመነጭ ነው፤ ፀረ ክርስቶስ እንዲህ ያሉ ነገሮችን እንደሚናገር ሰምታችኋል፤+ አሁንም እንኳ ይህ ቃል በዓለም ላይ እየተነገረ ነው።+