5 ሰውየውም የሆነ ነገር ሊሰጡኝ ነው ብሎ በማሰብ ትኩር ብሎ ተመለከታቸው። 6 ይሁንና ጴጥሮስ “እኔ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ። በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነስና ተራመድ!” አለው።+ 7 ከዚያም ቀኝ እጁን ይዞ አስነሳው።+ ወዲያውም እግሩና ቁርጭምጭሚቱ ጠነከረ፤+ 8 ዘሎም ተነሳ፤+ መራመድም ጀመረ፤ ደግሞም እየተራመደና እየዘለለ እንዲሁም አምላክን እያወደሰ ከእነሱ ጋር ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ።