18 አሕዛብ ታዛዦች እንዲሆኑ ክርስቶስ በእኔ አማካኝነት ስላከናወነው ነገር ካልሆነ በቀር ስለ ሌላ ነገር ለመናገር አልደፍርም። ይህን ያከናወነው እኔ በተናገርኩትና ባደረግኩት ነገር 19 እንዲሁም በተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች+ ደግሞም በአምላክ መንፈስ ኃይል ነው፤ በመሆኑም ከኢየሩሳሌም አንስቶ ዙሪያውን እስከ እልዋሪቆን ድረስ ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች በተሟላ ሁኔታ ሰብኬአለሁ።+