33 ሙሴም ከእነሱ ጋር ተነጋግሮ ሲጨርስ ፊቱን በመሸፈኛ ይሸፍን ነበር።+ 34 ሙሴ፣ ይሖዋ ፊት ቀርቦ ከእሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ግን ከዚያ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን ያነሳ ነበር።+ ከዚያም ወጥቶ የተቀበለውን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን ይነግራቸው ነበር።+ 35 እስራኤላውያንም የሙሴ ፊት እንደሚያንጸባርቅ ተመለከቱ፤ ከዚያም ሙሴ አምላክን ለማነጋገር ወደ ውስጥ እስከሚገባበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን መልሶ ፊቱ ላይ አደረገው።+