የሐዋርያት ሥራ 13:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 በኢየሱስ የሚያምን ማንኛውም ሰው፣ በእሱ አማካኝነት ‘ከበደል ነፃ ነህ’ ሊባል ይችላል፤+ የሙሴ ሕግ ግን እናንተን ከበደል ነፃ ሊያደርጋችሁ አልቻለም።+ ሮም 5:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ስለዚህ አሁን በእምነት አማካኝነት ጻድቃን ናችሁ+ ስለተባልን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል+ ከአምላክ ጋር ያለንን ሰላም ጠብቀን እንኑር፤* ሮም 8:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 አምላክ የመረጣቸውን ማን ሊከሳቸው ይችላል?+ ምክንያቱም የሚያጸድቃቸው አምላክ ራሱ ነው።+