20 ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ማንም ሰው በፊቱ ጻድቅ ነህ ሊባል አይችልም፤+ ምክንያቱም ስለ ኃጢአት ትክክለኛ ግንዛቤ የሚገኘው በሕጉ አማካኝነት ነው።+
21 አሁን ግን ሕግ ሳያስፈልግ፣ በሕጉና በነቢያት የተመሠከረለት+ የአምላክ ጽድቅ ግልጽ ሆኗል፤+ 22 እምነት ያላቸው ሁሉ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት አማካኝነት የአምላክን ጽድቅ ያገኛሉ። ይህም የሆነው በሰዎች መካከል ምንም ልዩነት ስለሌለ ነው።+