3 በተመሳሳይም አረጋውያን ሴቶች ለቅዱሳን ሰዎች የሚገባ ባሕርይ ያላቸው፣ ስም የማያጠፉ፣ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ እንዲሁም ጥሩ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤ 4 ይህም ወጣት ሴቶችን በመምከር ባሎቻቸውን የሚወዱ፣ ልጆቻቸውን የሚወዱ፣ 5 ጤናማ አስተሳሰብ ያላቸው፣ ንጹሐን፣ በቤት ውስጥ የሚሠሩ፣ ጥሩዎችና ለባሎቻቸው የሚገዙ+ እንዲሆኑ ለማድረግ ያስችላቸዋል፤ ይህም የአምላክ ቃል እንዳይሰደብ ነው።