-
የሐዋርያት ሥራ 2:29-32አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 “ወንድሞች፣ ከቀድሞ አባቶች አንዱ የሆነው ዳዊት እንደሞተና እንደተቀበረ+ እንዲሁም መቃብሩ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ እንደሚገኝ ለእናንተ በግልጽ እንድናገር ፍቀዱልኝ። 30 እሱ ነቢይ ስለነበረና አምላክ ከዘሮቹ አንዱን* በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ በመሐላ ቃል እንደገባለት ስላወቀ+ 31 አምላክ ክርስቶስን በመቃብር* እንደማይተወውና ሥጋውም እንደማይበሰብስ* አስቀድሞ ተረድቶ ስለ ትንሣኤው ተናገረ።+ 32 ይህን ኢየሱስን አምላክ ከሞት አስነሳው፤ እኛ ሁላችንም ለዚህ ነገር ምሥክሮች ነን።+
-
-
ሮም 1:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 በሥጋ ከዳዊት ዘር+ ስለተወለደው ልጁ የሚገልጽ ነው፤
-