-
ዘፍጥረት 14:17-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 አብራም ኮሎዶጎምርንና ከእሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ድል አድርጎ ከተመለሰ በኋላ የሰዶም ንጉሥ ከአብራም ጋር ለመገናኘት ወደ ሻዌ ሸለቆ* ማለትም ወደ ንጉሡ ሸለቆ+ ወጣ። 18 የሳሌም ንጉሥ+ መልከጼዴቅም+ ምግብና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤ እሱም የልዑሉ አምላክ ካህን+ ነበር።
19 አብራምንም ባረከው፤ እንዲህም አለው፦
“ሰማይንና ምድርን የሠራው
ልዑሉ አምላክ አብራምን ይባርክ፤
20 የሚጨቁኑህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠህ፣
ልዑሉ አምላክ ይወደስ!”
አብራምም ከሁሉም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።+
-