ዘፍጥረት 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋም ለአብራም ተገለጠለትና “ይህችን ምድር ለዘርህ+ እሰጣለሁ”+ አለው። ስለዚህ አብራም ተገልጦለት ለነበረው ለይሖዋ በዚያ መሠዊያ ሠራ። ዘፍጥረት 14:18-20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የሳሌም ንጉሥ+ መልከጼዴቅም+ ምግብና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤ እሱም የልዑሉ አምላክ ካህን+ ነበር። 19 አብራምንም ባረከው፤ እንዲህም አለው፦ “ሰማይንና ምድርን የሠራውልዑሉ አምላክ አብራምን ይባርክ፤20 የሚጨቁኑህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠህ፣ልዑሉ አምላክ ይወደስ!” አብራምም ከሁሉም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።+ ዘፍጥረት 17:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እጅግ አበዛሃለሁ፤ ብዙ ብሔርም አደርግሃለሁ፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ።+ ዘፍጥረት 22:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ በእርግጥ አበዛዋለሁ፤+ ዘርህም የጠላቶቹን በር* ይወርሳል።+
18 የሳሌም ንጉሥ+ መልከጼዴቅም+ ምግብና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤ እሱም የልዑሉ አምላክ ካህን+ ነበር። 19 አብራምንም ባረከው፤ እንዲህም አለው፦ “ሰማይንና ምድርን የሠራውልዑሉ አምላክ አብራምን ይባርክ፤20 የሚጨቁኑህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠህ፣ልዑሉ አምላክ ይወደስ!” አብራምም ከሁሉም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።+