38 ኤሳውም አባቱን “አባቴ ሆይ፣ ለእኔ የምትሆን አንዲት በረከት እንኳ የለችህም? አባቴ ባርከኝ። እኔንም ባርከኝ እንጂ!” አለው። ኤሳውም ከፍ ባለ ድምፅ ምርር ብሎ አለቀሰ።+ 39 ስለዚህ አባቱ ይስሐቅ እንዲህ አለው፦
“እንግዲህ መኖሪያህ ለም ከሆነው የምድር አፈር እንዲሁም በላይ ካሉት ሰማያት ጠል የራቀ ይሆናል።+ 40 በሰይፍህ ትኖራለህ፤+ ወንድምህንም ታገለግላለህ።+ ይሁንና እየተቅበጠበጥክ ባስቸገርክ ጊዜ ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ ሰብረህ ትጥላለህ።”+