-
ይሁዳ 12, 13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 እነዚህ ሰዎች ፍቅራችሁን ለመግለጽ በምታዘጋጁት ግብዣ ላይ ተገኝተው አብረዋችሁ ሲመገቡ ልክ በባሕር ውስጥ እንደተደበቀ ዓለት+ ከመሆናቸውም ሌላ ያላንዳች ኀፍረት ለሆዳቸው ብቻ የሚያስቡ እረኞች ናቸው፤+ በነፋስ ወዲያና ወዲህ የሚነዱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች+ እንዲሁም በመከር ጊዜ ፍሬ የማይገኝባቸው፣ ሁለት ጊዜ የሞቱና* ከሥራቸው የተነቀሉ ዛፎች ናቸው፤ 13 አረፋ እንደሚደፍቅ ኃይለኛ የባሕር ማዕበል አሳፋሪ ድርጊታቸውን ይገልጣሉ፤+ ለዘላለም ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚጣሉ ተንከራታች ከዋክብት ናቸው።+
-