ማቴዎስ 10:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን* ግን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤+ ከዚህ ይልቅ ነፍስንም ሆነ ሥጋን በገሃነም* ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ።+ 2 ጴጥሮስ 2:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ደግሞም ፈሪሃ አምላክ ለሌላቸው ሰዎች ለወደፊቱ ምሳሌ እንዲሆኑ+ የሰዶምና የገሞራ ከተሞችን አመድ በማድረግ ፈርዶባቸዋል።+ ይሁዳ 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በተመሳሳይም ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በዙሪያቸው የነበሩ ከተሞች ራሳቸውን ልቅ ለሆነ የፆታ ብልግና* አሳልፈው የሰጡ ከመሆኑም ሌላ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሥጋ ፍላጎታቸውን ያሳድዱ ነበር፤+ በመሆኑም በዘላለም እሳት ፍርድ ተቀጥተው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆነዋል።+ ራእይ 20:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ሞትና መቃብርም* ወደ እሳቱ ሐይቅ ተወረወሩ።+ ይህም የእሳት ሐይቅ+ ሁለተኛውን ሞት ያመለክታል።+
7 በተመሳሳይም ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በዙሪያቸው የነበሩ ከተሞች ራሳቸውን ልቅ ለሆነ የፆታ ብልግና* አሳልፈው የሰጡ ከመሆኑም ሌላ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሥጋ ፍላጎታቸውን ያሳድዱ ነበር፤+ በመሆኑም በዘላለም እሳት ፍርድ ተቀጥተው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆነዋል።+