ክፍል 11
ይሖዋ የእኛን ጸሎት ይቀበላል?
አምላክ ጸሎታችንን ይሰማል። 1 ጴጥሮስ 3:12
ይሖዋ “ጸሎት ሰሚ” አምላክ ነው። (መዝሙር 65:2) የልባችንን አውጥተን እንድንነግረው ይፈልጋል።
መጸለይ ያለብን ወደ ይሖዋ ብቻ ነው።
ስለተለያዩ ጉዳዮች መጸለይ እንችላለን። 1 ዮሐንስ 5:14
የአምላክ ፈቃድ በሰማይና በምድር እንዲፈጸም ጸልይ።
መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርግ እንዲረዳህ ይሖዋን ለምነው። በተጨማሪም ስለ ምግብ፣ ስለ ሥራ፣ ስለ መጠለያ፣ ስለ ልብስና ስለ ጤንነት መጸለይ ትችላለህ።