የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lff ትምህርት 1
  • መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?
  • ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠለቅ ያለ ጥናት
  • ማጠቃለያ
  • ምርምር አድርግ
  • መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ማስተዋወቂያ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • መጽሐፍ ቅዱስን መማርህን እንድትቀጥል ምን ሊረዳህ ይችላል?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ብርሃን ይፈነጥቃል
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
lff ትምህርት 1
ምዕራፍ 1. የተከፈተ መጽሐፍ ቅዱስ

ምዕራፍ 01

መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

ሁላችንም ስለ ሕይወት፣ ስለ ሞትና ስለ ወደፊቱ ጊዜ የተለያዩ ጥያቄዎችን እናነሳለን፤ እንዲሁም መከራ የሚደርስብን ለምን እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን። በተጨማሪም በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚያጋጥሙን ጉዳዮች ያስጨንቁናል፤ ለምሳሌ ለኑሮ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ማግኘት ወይም የቤተሰባችንን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምንችልበት መንገድ ያሳስበናል። ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ በአእምሯቸው ውስጥ ለሚፈጠሩ ትላልቅ ጥያቄዎች መልስ እንደሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ለዕለት ተዕለት ሕይወታቸው የሚጠቅም ምክር እንደያዘም አስተውለዋል። ታዲያ ሁሉም ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ቢማር ጠቃሚ አይመስልህም?

1. መጽሐፍ ቅዱስ ለየትኞቹ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል?

መጽሐፍ ቅዱስ ለሚከተሉት ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፦ ሕይወት ያገኘነው እንዴት ነው? የተፈጠርንበት ዓላማ ምንድን ነው? ጥሩ ሰዎች መከራ የሚደርስባቸው ለምንድን ነው? ሰው ሲሞት ምን ይሆናል? ሰዎች ሰላም ሰፍኖ ማየት ቢፈልጉም ጦርነት ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው? ወደፊት ምድር ትጠፋ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ላሉ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ጥረት እንድናደርግ ያበረታታናል። ደግሞም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለጥያቄዎቻቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መልስ ማግኘት ችለዋል።

2. መጽሐፍ ቅዱስ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ደስተኛ እንድንሆን የሚረዳን እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ምክሮች ይዟል። ለምሳሌ ያህል፣ የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ያስተምራል። ጭንቀትን መቋቋምና በምንሠራው ሥራ ደስተኛ መሆን ስለምንችልበት መንገድ ምክር ይሰጣል። ይህን ጽሑፍ ተጠቅመህ መወያየትህን ስትቀጥል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እነዚህ ጉዳዮች ምን እንደሚያስተምር ትረዳለህ። ይህም ‘ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ [በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት ሐሳቦች በሙሉ] ጠቃሚ’ እንደሆኑ እንድትገነዘብ ያደርግሃል።—2 ጢሞቴዎስ 3:16

ይህ ጽሑፍ መጽሐፍ ቅዱስን የሚተካ አይደለም። ከዚህ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን አንተው ራስህ እንድትመረምር ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በመሆኑም በምዕራፉ ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች አውጥተህ እንድታነብና ከምትማረው ነገር ጋር እንድታነጻጽር እናበረታታሃለን።

ጠለቅ ያለ ጥናት

መጽሐፍ ቅዱስ ብዙዎችን የረዳቸው እንዴት እንደሆነ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነና መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ለመረዳት የሌሎች እገዛ የሚያስፈልግህ ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።

3. መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ መመሪያ ይሰጠናል

መጽሐፍ ቅዱስ ልክ እንደ ደማቅ መብራት ነው። ጥሩ ውሳኔዎችን እንድናደርግ እንዲሁም ከፊታችን የሚጠብቀን ነገር ፍንትው ብሎ እንዲታየን ይረዳናል።

መዝሙር 119:105⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • የዚህ ጥቅስ ጸሐፊ ለመጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት ነበረው?

  • አንተስ ለመጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ?

አመሻሹ ላይ በአንድ ሐይቅ ዳርቻ በሚገኝ ድንጋያማ አካባቢ መንገዱ ላይ የእጅ ባትሪ እያበራ የሚጓዝ ሰው

4. መጽሐፍ ቅዱስ ለጥያቄዎቻችን መልስ ይሰጠናል

አንዲት ሴት ለበርካታ ዓመታት ሲያስጨንቋት ለነበሩ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ መልስ አግኝታለች። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

ቪዲዮ፦ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጡ! (1:48)

  • በቪዲዮው ላይ የታየችው ሴት ምን ጥያቄዎች ነበሯት?

  • መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቷ የጠቀማት እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን እንድንጠይቅ ያበረታታናል። ማቴዎስ 7:7⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለየትኛው ጥያቄህ መልስ ማግኘት ትፈልጋለህ?

5. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን አስደሳች ማድረግ ትችላለህ

ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ያስደስታቸዋል። እንዲህ በማድረጋቸውም የተለያዩ ጥቅሞች እያገኙ ነው። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

ቪዲዮ፦ የአምላክን ቃል በቋንቋዬ አየሁት (3:40)

  • በቪዲዮው ላይ የታየው ዲሜትሮ፣ መፍሐፍ ቅዱስን በቋንቋው በማየቱ ምን ተሰማው?

  • እሱንና ቤተሰቡን መጽሐፍ ቅዱስ ማየታቸው የጠቀማቸው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ በውስጡ የያዘው ሐሳብ መጽናኛና ተስፋ እንደሚሰጠን ይናገራል። ሮም 15:4⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኘው ማጽናኛና ተስፋ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?

6. መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ለመረዳት የሌሎች እርዳታ ያስፈልገናል

ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስን በግላቸው ከማንበብ በተጨማሪ ከሌሎች ጋር መወያየቱን ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። የሐዋርያት ሥራ 8:26-31⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ምን ያስፈልገናል?—ቁጥር 30 እና 31⁠ን ተመልከት።

1. ወንጌላዊው ፊልጶስ ለኢትዮጵያዊው ሰው ቅዱሳን መጻሕፍትን ሲያብራራለት 2. አንዲት የይሖዋ ምሥክር ሁለት ልጆች ከያዘች እናት ጋር ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስትወያይ

ኢትዮጵያዊው ሰው የሚያነበውን ነገር ለመረዳት እርዳታ አስፈልጎት ነበር። በዛሬው ጊዜ በርካታ ሰዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች ጋር መወያየታቸው ጠቃሚ እንደሆነ ይሰማቸዋል

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጊዜ ማባከን ነው።”

  • አንተስ ምን ትላለህ?

ማጠቃለያ

መጽሐፍ ቅዱስ ለዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚጠቅም ምክር ይሰጣል፣ ለምናነሳቸው ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ ይዟል እንዲሁም ማጽናኛና ተስፋ ይሰጠናል።

ክለሳ

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን ምክሮች እናገኛለን?

  • መጽሐፍ ቅዱስ ለየትኞቹ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል?

  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለ ምን መማር ትፈልጋለህ?

ግብ

ምርምር አድርግ

መጽሐፍ ቅዱስ ከልጅነቱ ጀምሮ ከአሉታዊ ስሜት ጋር ሲታገል የኖረን ሰው የረዳው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

“አየሁ፤ ነገር ግን አላስተዋልሁትም” (መጠበቂያ ግንብ፣ ሰኔ 15, 2013)

መጽሐፍ ቅዱስ የዚህን ዓለም ገዢ በተመለከተ የያዘው ሐሳብ ከብዙዎች አመለካከት የሚለየው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው?—ሙሉው ቪዲዮ (3:13)

    የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ