የግርጌ ማስታወሻ a በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የሐሰት ሃይማኖት፣ ታላቂቱ ባቢሎን እና “ታላቂቱ አመንዝራ” ተብሎ ተገልጿል። (ራእይ 17:1, 5) ታላቂቱ ባቢሎንን የሚያጠፋው ደማቅ ቀይ አውሬ፣ አንድን ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ይወክላል፤ የዚህ ድርጅት ዓላማ የዓለምን መንግሥታት ማስተባበርና መወከል ነው። ይህ ድርጅት በመጀመሪያ የመንግሥታት ቃል ኪዳን ማኅበር ይባል የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተብሏል።