የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ሳሙኤል 30
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • አማሌቃውያን በጺቅላግ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤ በእሳትም አቃጠሏት (1-6)

        • ዳዊት በአምላኩ በይሖዋ ራሱን አበረታ (6)

      • ዳዊት አማሌቃውያንን ድል አደረጋቸው (7-31)

        • ዳዊት ምርኮኞቹን አስመለሰ (18, 19)

        • ዳዊት ምርኮ መከፋፈልን በተመለከተ ያወጣው ደንብ (23, 24)

1 ሳሙኤል 30:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በኔጌብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:21, 31፤ 1ሳሙ 27:5, 6
  • +ዘፍ 36:12፤ ዘፀ 17:14፤ 1ሳሙ 15:2፤ 27:8

1 ሳሙኤል 30:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 27:3

1 ሳሙኤል 30:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 25:42, 43

1 ሳሙኤል 30:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሰዎቹ ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 18:6፤ 31:1, 9፤ 34:19፤ 143:5

1 ሳሙኤል 30:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 22:20፤ 1ነገ 2:26
  • +1ሳሙ 23:9

1 ሳሙኤል 30:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 27:21፤ መሳ 20:28፤ 1ሳሙ 23:2, 11፤ 28:6
  • +1ሳሙ 30:18፤ መዝ 34:19

1 ሳሙኤል 30:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 23:13፤ 27:2

1 ሳሙኤል 30:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 30:21

1 ሳሙኤል 30:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “መንፈሱ ተመለሰለት።”

1 ሳሙኤል 30:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ኔጌብ።”

  • *

    ወይም “ኔጌብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 8:18፤ 1ነገ 1:38፤ 1ዜና 18:17፤ ሕዝ 25:16፤ ሶፎ 2:5
  • +ኢያሱ 14:13

1 ሳሙኤል 30:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 17:14

1 ሳሙኤል 30:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 30:3

1 ሳሙኤል 30:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 30:8፤ መዝ 34:19

1 ሳሙኤል 30:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 30:10

1 ሳሙኤል 30:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 30:8

1 ሳሙኤል 30:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 30:10
  • +ዘኁ 31:27፤ ኢያሱ 22:8፤ መዝ 68:12

1 ሳሙኤል 30:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በረከት።”

1 ሳሙኤል 30:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በደቡብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:4, 8
  • +ኢያሱ 15:20, 48፤ 21:8, 14

1 ሳሙኤል 30:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:20, 50፤ 21:8, 14

1 ሳሙኤል 30:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 27:10፤ 1ዜና 2:9
  • +መሳ 1:16፤ 1ሳሙ 15:6

1 ሳሙኤል 30:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 21:3፤ ኢያሱ 19:1, 4፤ መሳ 1:17

1 ሳሙኤል 30:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 14:13፤ 2ሳሙ 2:1

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ሳሙ. 30:1ኢያሱ 15:21, 31፤ 1ሳሙ 27:5, 6
1 ሳሙ. 30:1ዘፍ 36:12፤ ዘፀ 17:14፤ 1ሳሙ 15:2፤ 27:8
1 ሳሙ. 30:21ሳሙ 27:3
1 ሳሙ. 30:51ሳሙ 25:42, 43
1 ሳሙ. 30:6መዝ 18:6፤ 31:1, 9፤ 34:19፤ 143:5
1 ሳሙ. 30:71ሳሙ 22:20፤ 1ነገ 2:26
1 ሳሙ. 30:71ሳሙ 23:9
1 ሳሙ. 30:8ዘኁ 27:21፤ መሳ 20:28፤ 1ሳሙ 23:2, 11፤ 28:6
1 ሳሙ. 30:81ሳሙ 30:18፤ መዝ 34:19
1 ሳሙ. 30:91ሳሙ 23:13፤ 27:2
1 ሳሙ. 30:101ሳሙ 30:21
1 ሳሙ. 30:142ሳሙ 8:18፤ 1ነገ 1:38፤ 1ዜና 18:17፤ ሕዝ 25:16፤ ሶፎ 2:5
1 ሳሙ. 30:14ኢያሱ 14:13
1 ሳሙ. 30:17ዘፀ 17:14
1 ሳሙ. 30:181ሳሙ 30:3
1 ሳሙ. 30:191ሳሙ 30:8፤ መዝ 34:19
1 ሳሙ. 30:211ሳሙ 30:10
1 ሳሙ. 30:231ሳሙ 30:8
1 ሳሙ. 30:241ሳሙ 30:10
1 ሳሙ. 30:24ዘኁ 31:27፤ ኢያሱ 22:8፤ መዝ 68:12
1 ሳሙ. 30:27ኢያሱ 19:4, 8
1 ሳሙ. 30:27ኢያሱ 15:20, 48፤ 21:8, 14
1 ሳሙ. 30:28ኢያሱ 15:20, 50፤ 21:8, 14
1 ሳሙ. 30:291ሳሙ 27:10፤ 1ዜና 2:9
1 ሳሙ. 30:29መሳ 1:16፤ 1ሳሙ 15:6
1 ሳሙ. 30:30ዘኁ 21:3፤ ኢያሱ 19:1, 4፤ መሳ 1:17
1 ሳሙ. 30:31ኢያሱ 14:13፤ 2ሳሙ 2:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ሳሙኤል 30:1-31

አንደኛ ሳሙኤል

30 በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ጺቅላግ+ ሲመጡ አማሌቃውያን+ በስተ ደቡብ* ያለውን አካባቢና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ እነሱም በጺቅላግ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤ በእሳትም አቃጠሏት። 2 ሴቶችንና+ በዚያ የነበሩትንም ሁሉ ትንሽ ትልቅ ሳይሉ ማርከው ወሰዱ። አንድም ሰው አልገደሉም፤ ከዚህ ይልቅ ሁሉንም ይዘው ሄዱ። 3 ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ጺቅላግ ሲመጡ ከተማዋ በእሳት ተቃጥላ አገኟት፤ ሚስቶቻቸውም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በምርኮ ተወስደው ነበር። 4 በመሆኑም ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ለማልቀስ አቅም እስኪያጡ ድረስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ። 5 ሁለቱ የዳዊት ሚስቶችም ማለትም ኢይዝራኤላዊቷ አኪኖዓም እና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢጋኤል በምርኮ ተወስደው ነበር።+ 6 ዳዊት ሰዎቹ ሊወግሩት እየተማከሩ ስለነበር እጅግ ተጨነቀ፤ ምክንያቱም ሰዎቹ* ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በመወሰዳቸው ተመርረው ነበር። ይሁንና ዳዊት በአምላኩ በይሖዋ ራሱን አበረታ።+

7 ከዚያም ዳዊት የአሂሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን+ “እባክህ፣ ኤፉዱን አምጣልኝ”+ አለው። አብያታርም ኤፉዱን ለዳዊት አመጣለት። 8 ዳዊትም “ይህን ወራሪ ቡድን ላሳደው? እደርስበት ይሆን?” ሲል ይሖዋን ጠየቀ።+ እሱም “በእርግጥ ስለምትደርስባቸውና የወሰዱትን ሁሉ ከእጃቸው ስለምታስጥል ሂድ አሳዳቸው” አለው።+

9 ዳዊትም ወዲያውኑ አብረውት ከነበሩት 600 ሰዎች+ ጋር ወጣ፤ እነሱም እስከ በሶር ሸለቆ* ድረስ ሄዱ፤ በዚያም የተወሰኑ ሰዎች ወደ ኋላ ቀሩ። 10 ዳዊትም ከ400 ሰዎች ጋር ሆኖ ማሳደዱን ቀጠለ፤ በጣም ከመድከማቸው የተነሳ የበሶርን ሸለቆ መሻገር ያልቻሉት 200 ሰዎች ግን እዚያው ቀሩ።+

11 ከዚያም ሜዳ ላይ አንድ ግብፃዊ አግኝተው ወደ ዳዊት አመጡት። የሚበላው ምግብና የሚጠጣው ውኃ ሰጡት። 12 በተጨማሪም ቁራሽ የበለስ ጥፍጥፍና ሁለት የዘቢብ ቂጣ ሰጡት። እሱም ከበላ በኋላ ብርታት አገኘ፤* ምክንያቱም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ሙሉ እህልም ሆነ ውኃ አልቀመሰም ነበር። 13 ዳዊትም “ለመሆኑ አንተ የማን ነህ? የመጣኸውስ ከየት ነው?” አለው፤ እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እኔ ለአንድ አማሌቃዊ ባሪያ የሆንኩ ግብፃዊ ነኝ፤ ሆኖም ከሦስት ቀን በፊት ታምሜ ስለነበር ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ። 14 የከሪታውያንን+ ምድር ደቡባዊ ክፍል፣* የይሁዳን ግዛትና የካሌብን+ ደቡባዊ ክፍል* ወረርን፤ ጺቅላግንም በእሳት አጋየናት።” 15 በዚህ ጊዜ ዳዊት “ይህ ወራሪ ቡድን ወዳለበት መርተህ ትወስደኛለህ?” አለው። እሱም “ብቻ እንደማትገድለኝና ለጌታዬ አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ በአምላክ ማልልኝ እንጂ ወራሪው ቡድን ወዳለበት መርቼ አደርስሃለሁ” አለው።

16 በመሆኑም ሰዎቹ ከፍልስጤማውያን ምድርና ከይሁዳ ምድር በወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሳ በየቦታው ተበታትነው ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ይደሰቱ ወደነበረበት ቦታ መርቶ ወሰደው። 17 ከዚያም ዳዊት ጎህ ሳይቀድ ጀምሮ እስከ ማግስቱ ምሽት ድረስ መታቸው፤ ፈጽሞም አጠፋቸው፤ በግመል ተቀምጠው ከሸሹት 400 ሰዎች በስተቀር አንድም ሰው አላመለጠም።+ 18 ዳዊትም አማሌቃውያን የወሰዱትን ሁሉ አስጣለ፤+ ሁለቱን ሚስቶቹንም አስመለሰ። 19 ከትንሽ እስከ ትልቅ ምንም የጎደለ ነገር አልነበረም። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ሆነ ዘርፈው የወሰዱባቸውን ንብረት ሁሉ አስመለሱ፤+ ዳዊት የወሰዱትን ሁሉ አስመለሰ። 20 በመሆኑም ዳዊት መንጎቹንና ከብቶቹን በሙሉ ወሰደ፤ እነሱም ከራሳቸው ከብቶች ፊት ፊት ነዷቸው። እነሱም “ይህ የዳዊት ምርኮ ነው” አሉ።

21 ከዚያም ዳዊት በጣም ከመድከማቸው የተነሳ አብረውት ሊሄዱ ወዳልቻሉትና በበሶር ሸለቆ+ ቀርተው ወደነበሩት 200 ሰዎች መጣ፤ እነሱም ዳዊትንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች ለመቀበል ወጡ። ዳዊትም ወደ ሰዎቹ በቀረበ ጊዜ ስለ ደህንነታቸው ጠየቃቸው። 22 ሆኖም ከዳዊት ጋር አብረው ከሄዱት መካከል ክፉ የሆኑትና የማይረቡት ሰዎች “እነዚህ ሰዎች አብረውን ስላልሄዱ እያንዳንዳቸው ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ይዘው ይሂዱ እንጂ ካመጣነው ምርኮ ላይ ምንም ነገር አንሰጣቸውም” አሉ። 23 ዳዊት ግን እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼ ይሖዋ በሰጠን ነገርማ እንዲህ ማድረግ የለባችሁም። የጠበቀንና የመጣብንን ወራሪ ቡድን በእጃችን አሳልፎ የሰጠን እሱ ነው።+ 24 ታዲያ አሁን ይህን የምትሉትን ማን ይሰማችኋል? ወደ ውጊያ የዘመተው ሰው የሚያገኘው ድርሻና ጓዝ የጠበቀው ሰው የሚያገኘው ድርሻ እኩል ነው።+ ሁሉም ድርሻ ይኖረዋል።”+ 25 ዳዊትም ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከዚህ ዕለት ድረስ ይህን ለእስራኤል ሥርዓትና ደንብ አድርጎ አጸደቀው።

26 ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በተመለሰ ጊዜ “ከይሖዋ ጠላቶች ከተገኘው ምርኮ የተሰጠ ስጦታ* ይኸውላችሁ” በማለት ወዳጆቹ ለሆኑት የይሁዳ ሽማግሌዎች ከምርኮው ላይ የተወሰነውን ላከ። 27 ስጦታውንም በቤቴል፣+ በኔጌብ* ራሞት፣ በያቲር፣+ 28 በአሮዔር፣ በሲፍሞት፣ በኤሽተሞዓ፣+ 29 በራካል፣ በየራህምኤል+ ከተሞች፣ በቄናውያን+ ከተሞች፣ 30 በሆርማ፣+ በቦርአሻን፣ በአታክ፣ 31 በኬብሮን+ እንዲሁም ዳዊትና ሰዎቹ በሚያዘወትሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለነበሩት ላከ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ