የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 28
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የኤፍሬም ሰካራሞች ወዮላቸው! (1-6)

      • የይሁዳ ካህናትና ነቢያት ይንገዳገዳሉ (7-13)

      • “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” (14-22)

        • በጽዮን የተቀመጠ ክቡር የማዕዘን ድንጋይ (16)

        • ይሖዋ ያከናወነው እንግዳ የሆነ ተግባር (21)

      • የይሖዋን ተግሣጽ የሚያሳይ ምሳሌ (23-29)

ኢሳይያስ 28:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ትዕቢተኛ ወይም ኩሩ ለሆነችው።”

  • *

    ዋና ከተማዋን ሰማርያን የምታመለክት ልትሆን ትችላለች።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 7:2

ኢሳይያስ 28:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ትዕቢተኛ ወይም ኩሩ የሆኑት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:6፤ ኢሳ 17:3

ኢሳይያስ 28:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 11:16

ኢሳይያስ 28:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 18:34፤ 68:35

ኢሳይያስ 28:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 16:10, 11፤ ኤር 5:31

ኢሳይያስ 28:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በመለኪያ ገመድ ላይ መለኪያ ገመድ፣ በመለኪያ ገመድ ላይ መለኪያ ገመድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 21:13፤ ኢሳ 28:17፤ ሰቆ 2:8

ኢሳይያስ 28:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:49, 50፤ ኤር 5:15፤ 1ቆሮ 14:21

ኢሳይያስ 28:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 81:10, 11

ኢሳይያስ 28:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በመለኪያ ገመድ ላይ መለኪያ ገመድ፣ በመለኪያ ገመድ ላይ መለኪያ ገመድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 28:17
  • +2ዜና 36:15, 16፤ ኢሳ 8:14, 15

ኢሳይያስ 28:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከሲኦልም።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

  • *

    “ራእይ አይተናል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 28:18
  • +ኢሳ 30:9, 10

ኢሳይያስ 28:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 118:22
  • +ኤፌ 2:19, 20
  • +ማቴ 21:42፤ ማር 12:10፤ ሉቃስ 20:17፤ ሥራ 4:11
  • +ሮም 9:33፤ 10:11፤ 1ጴጥ 2:4, 6

ኢሳይያስ 28:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቱምቢ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 21:13
  • +ኤር 11:20

ኢሳይያስ 28:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከሲኦልም።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 28:15

ኢሳይያስ 28:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የተነገረውን ነገር ሲረዱ በሽብር ይዋጣሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 24:1

ኢሳይያስ 28:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሰቆ 2:15፤ ዕን 1:5-7
  • +ኢያሱ 10:8-14፤ 2ሳሙ 5:20፤ 1ዜና 14:10-16

ኢሳይያስ 28:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መላዋን ምድር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:15, 16፤ ኤር 20:7
  • +ኢሳ 10:23፤ 24:1

ኢሳይያስ 28:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 30:5፤ 103:9፤ ሚክ 7:18

ኢሳይያስ 28:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 9:31, 32፤ ሕዝ 4:9

ኢሳይያስ 28:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰውን . . . ይገሥጸዋል፤ ይቀጣዋል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 119:71

ኢሳይያስ 28:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ጥርስ መሳይ ጉጦች ያሉት የእህል መውቂያ።

  • *

    ተሽከርካሪ እግር።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 41:15፤ አሞጽ 1:3

ኢሳይያስ 28:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 103:9፤ ኢሳ 21:10፤ ሚክ 7:18
  • +ዘሌ 26:44፤ ኤር 10:24

ኢሳይያስ 28:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዓላማ።”

  • *

    ወይም “ጥበቡ ታላቅ ከሆነው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 40:5፤ ኤር 32:19፤ ሮም 11:33

ተዛማጅ ሐሳብ

ኢሳ. 28:1ኢሳ 7:2
ኢሳ. 28:32ነገ 17:6፤ ኢሳ 17:3
ኢሳ. 28:5ኢሳ 11:16
ኢሳ. 28:6መዝ 18:34፤ 68:35
ኢሳ. 28:72ነገ 16:10, 11፤ ኤር 5:31
ኢሳ. 28:102ነገ 21:13፤ ኢሳ 28:17፤ ሰቆ 2:8
ኢሳ. 28:11ዘዳ 28:49, 50፤ ኤር 5:15፤ 1ቆሮ 14:21
ኢሳ. 28:12መዝ 81:10, 11
ኢሳ. 28:13ኢሳ 28:17
ኢሳ. 28:132ዜና 36:15, 16፤ ኢሳ 8:14, 15
ኢሳ. 28:15ኢሳ 28:18
ኢሳ. 28:15ኢሳ 30:9, 10
ኢሳ. 28:16መዝ 118:22
ኢሳ. 28:16ኤፌ 2:19, 20
ኢሳ. 28:16ማቴ 21:42፤ ማር 12:10፤ ሉቃስ 20:17፤ ሥራ 4:11
ኢሳ. 28:16ሮም 9:33፤ 10:11፤ 1ጴጥ 2:4, 6
ኢሳ. 28:172ነገ 21:13
ኢሳ. 28:17ኤር 11:20
ኢሳ. 28:18ኢሳ 28:15
ኢሳ. 28:19ኢሳ 24:1
ኢሳ. 28:21ሰቆ 2:15፤ ዕን 1:5-7
ኢሳ. 28:21ኢያሱ 10:8-14፤ 2ሳሙ 5:20፤ 1ዜና 14:10-16
ኢሳ. 28:222ዜና 36:15, 16፤ ኤር 20:7
ኢሳ. 28:22ኢሳ 10:23፤ 24:1
ኢሳ. 28:24መዝ 30:5፤ 103:9፤ ሚክ 7:18
ኢሳ. 28:25ዘፀ 9:31, 32፤ ሕዝ 4:9
ኢሳ. 28:26መዝ 119:71
ኢሳ. 28:27ኢሳ 41:15፤ አሞጽ 1:3
ኢሳ. 28:28መዝ 103:9፤ ኢሳ 21:10፤ ሚክ 7:18
ኢሳ. 28:28ዘሌ 26:44፤ ኤር 10:24
ኢሳ. 28:29መዝ 40:5፤ ኤር 32:19፤ ሮም 11:33
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኢሳይያስ 28:1-29

ኢሳይያስ

28 ጎልታ ለምትታየው* ለኤፍሬም+ ሰካራሞች አክሊል* ወዮላት!

ይህች የምታምር ጌጥ በወይን ጠጅ የተሸነፉ ሰዎች በሚኖሩበት

ለም ሸለቆ አናት ላይ የምትገኝ የምትጠወልግ አበባ ናት።

 2 እነሆ፣ ይሖዋ ጠንካራና ብርቱ የሆነውን ይልካል።

እሱም እንደ ነጎድጓዳማ የበረዶ ውሽንፍር፣ እንደ አጥፊ አውሎ ነፋስ፣

ኃይለኛ ጎርፍ እንደሚያስከትል ነጎድጓዳማ ውሽንፍር

በኃይል አሽቀንጥሮ ወደ ምድር ይጥላታል።

 3 ጎልተው የሚታዩት* የኤፍሬም ሰካራሞች ያደረጓቸው አክሊሎች

በእግር ይረገጣሉ።+

 4 ለም በሆነው ሸለቆ አናት ላይ የምትገኘውና

የምታምር ጌጥ የሆነችው የምትጠወልግ አበባ

ከበጋ በፊት፣ በመጀመሪያው ወቅት እንደምትበስል በለስ ትሆናለች።

ሰውም ባያት ጊዜ ቀጥፎ ወዲያውኑ ይውጣታል።

5 በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከሕዝቡ መካከል ለተረፉት ሰዎች የሚያምር አክሊልና ውብ የአበባ ጉንጉን ይሆናል።+ 6 በፍርድ ወንበር ለተቀመጠውም የፍትሕ መንፈስ፣ የከተማዋ በር ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ለሚመክቱም የብርታት ምንጭ ይሆናል።+

 7 እነዚህም ከወይን ጠጅ የተነሳ መንገድ ይስታሉ፤

ከሚያሰክር መጠጥ የተነሳም ይንገዳገዳሉ።

ካህኑና ነቢዩ ከጠጡት መጠጥ የተነሳ መንገድ ይስታሉ፤

ከወይን ጠጅ የተነሳ ግራ ይጋባሉ፤

ከሚያሰክር መጠጥ የተነሳም ይንገዳገዳሉ፤

የሚያዩት ራእይ መንገድ ያስታቸዋል፤

ፍርድ ሲሰጡም ይሳሳታሉ።+

 8 ገበታቸው ሁሉ በሚያስጸይፍ ትውከት ተሞልቷል፤

ያልተበላሸ ቦታም የለም።

 9 እነሱም እንዲህ ይላሉ፦ “እውቀትን የሚያካፍለው ለማን ነው?

መልእክቱንስ የሚያስረዳው ለማን ነው?

ገና ወተት ለተዉ፣

ጡትም ለጣሉ ሕፃናት ነው?

10 ‘በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣

በሥርዓት ላይ ሥርዓት፣ በሥርዓት ላይ ሥርዓት፣*+

እዚህ ጥቂት፣ እዚያ ጥቂት’ ነውና።”

11 ስለዚህ በሚንተባተቡ ሰዎች አንደበትና በባዕድ ቋንቋ ለዚህ ሕዝብ ይናገራል።+ 12 በአንድ ወቅት “ይህ የእረፍት ቦታ ነው። የዛለው እንዲያርፍ አድርጉ፤ ይህ የእፎይታ ቦታ ነው” ብሏቸው ነበር፤ እነሱ ግን ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም።+ 13 የይሖዋም ቃል ለእነሱ

“በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣

በሥርዓት ላይ ሥርዓት፣ በሥርዓት ላይ ሥርዓት፣*+

እዚህ ጥቂት፣ እዚያ ጥቂት” ይሆንባቸዋል፤

በመሆኑም ሲሄዱ፣

ተሰናክለው ወደ ኋላ ይወድቃሉ፤

ደግሞም ይሰበራሉ፣ ይጠመዳሉ እንዲሁም ይያዛሉ።+

14 ስለዚህ እናንተ ጉረኞች፣

በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ገዢዎች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦

15 እናንተ እንዲህ ብላችኋልና፦

“ከሞት ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል፤+

ከመቃብርም * ጋር ስምምነት አድርገናል።*

በድንገት የሚያጥለቀልቅ ጎርፍ ሲያልፍ

እኛን አይነካንም፤

ውሸትን መጠጊያችን አድርገናልና፤

በሐሰትም ውስጥ ተደብቀናል።”+

16 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እነሆ፣ በጽዮን የመሠረት ድንጋይ ይኸውም የተፈተነ ድንጋይ፣+

አስተማማኝ መሠረት+ ሆኖ የተጣለ ክቡር የማዕዘን ድንጋይ+ አኖራለሁ።

በእሱ የሚያምን አይደናገጥም።+

17 እኔም ፍትሕን የመለኪያ ገመድ፣+

ጽድቅንም ውኃ ልክ* አደርጋለሁ።+

የውሸት መጠጊያውን፣ በረዶ ጠራርጎ ይወስደዋል፤

ውኃዎቹም መደበቂያ ቦታውን ያጥለቀልቁታል።

18 ከሞት ጋር የገባችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፤

ከመቃብርም * ጋር ያደረጋችሁት ስምምነት አይጸናም።+

በድንገት የሚያጥለቀልቀው ጎርፍ ሲያልፍ

ድምጥማጣችሁን ያጠፋል።

19 ጎርፉ ባለፈ ቁጥር

ጠራርጎ ይወስዳችኋል፤+

በየማለዳው እንዲሁም

በቀንና በሌሊት ያልፋልና።

የተነገረውን ነገር እንዲረዱ የሚያደርገው ሽብር ብቻ ነው።”*

20 እግር ተዘርግቶ እንዳይተኛ አልጋው አጭር ነውና፤

ተሸፋፍኖም እንዳይተኛ ጨርቁ በጣም ጠባብ ነው።

21 ይሖዋ ተግባሩን ይኸውም እንግዳ የሆነ ተግባሩን ያከናውን ዘንድ

እንዲሁም ሥራውን ይኸውም ያልተለመደ ሥራውን ይሠራ ዘንድ+

በጰራጺም ተራራ እንዳደረገው ይነሳልና፤

በገባኦን አቅራቢያ ባለው ሸለቆ* እንዳደረገውም ራሱን ያነሳሳል።+

22 እንግዲህ ፌዘኞች አትሁኑ፤+

አለዚያ እስራቱ ይበልጥ ይጠብቅባችኋል፤

ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ

አገሪቱን በሙሉ* ለማጥፋት ያስተላለፈውን ፍርድ ሰምቻለሁና።+

23 ጆሯችሁን አዘንብሉ፤ ድምፄንም ስሙ፤

ለምናገረው ነገር ትኩረት ስጡ፤ በጥሞናም አዳምጡ።

24 ገበሬ ዘር ከመዝራቱ በፊት ቀኑን ሙሉ ሲያርስ ይውላል?

ደግሞስ ጓሉን ሲከሰክስና መሬቱን ሲያለሰልስ ይከርማል?+

25 ከዚህ ይልቅ መሬቱን ከደለደለ በኋላ

ጥቁር አዝሙድና ከሙን አይዘራም?

ስንዴውን፣ ማሽላውንና ገብሱንስ በቦታ በቦታቸው አይዘራም?

ደግሞስ አጃውን+ ዳር ላይ አይዘራም?

26 አምላክ ሰውን በትክክለኛው መንገድ ያስተምረዋል፤*

ደግሞም ይመራዋል።+

27 ጥቁር አዝሙድ በማሄጃ*+ አይወቃም፤

በከሙንም ላይ የመውቂያ መንኮራኩር* እንዲሄድ አይደረግም።

ጥቁር አዝሙድ በበትር፣

ከሙንም በዘንግ ይወቃል።

28 ሰው የዳቦ እህል እንዲደቅ ያደርጋል?

በጭራሽ፤ እስኪደቅ ድረስ አይወቃውም፤+

በፈረሶቹ የሚጎተተውን የመውቂያ መንኮራኩር በሚያስኬድበት ጊዜ፣

እህሉን አያደቀውም።+

29 ይህም የተገኘው፣ አስደናቂ ምክር* ካለውና

ታላላቅ ሥራዎችን ካከናወነው*

ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ነው።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ