የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 6
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • በእስራኤል ተራሮች ላይ የተነገረ ትንቢት (1-14)

        • አስጸያፊ የሆኑት ጣዖታት ውርደት ይከናነባሉ (4-6)

        • ‘እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ’ (7)

ሕዝቅኤል 6:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 27:9
  • +ዘሌ 26:30

ሕዝቅኤል 6:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 8:1, 2

ሕዝቅኤል 6:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 2:15፤ 32:29፤ ሚክ 3:12
  • +ሕዝ 16:39

ሕዝቅኤል 6:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 14:18
  • +ሕዝ 7:4

ሕዝቅኤል 6:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 30:10፤ 44:28፤ ሕዝ 14:22

ሕዝቅኤል 6:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሥነ ምግባር የጎደለው፤ ሴሰኛ።”

  • *

    ወይም “ሥነ ምግባር በጎደለው መንገድ በተከተሉት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 30:1, 2፤ መዝ 137:1
  • +መዝ 78:40, 41፤ ኢሳ 63:10
  • +ዘኁ 15:39
  • +ሕዝ 20:43፤ 36:31

ሕዝቅኤል 6:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 33:29፤ ዳን 9:12፤ ዘካ 1:6

ሕዝቅኤል 6:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 15:2፤ 16:4፤ ሕዝ 5:12

ሕዝቅኤል 6:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 5:13

ሕዝቅኤል 6:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደስ የሚያሰኙ መዓዛዎች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 20:28
  • +ኤር 8:2
  • +ሕዝ 12:15

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 6:4ኢሳ 27:9
ሕዝ. 6:4ዘሌ 26:30
ሕዝ. 6:5ኤር 8:1, 2
ሕዝ. 6:6ኤር 2:15፤ 32:29፤ ሚክ 3:12
ሕዝ. 6:6ሕዝ 16:39
ሕዝ. 6:7ኤር 14:18
ሕዝ. 6:7ሕዝ 7:4
ሕዝ. 6:8ኤር 30:10፤ 44:28፤ ሕዝ 14:22
ሕዝ. 6:9ዘዳ 30:1, 2፤ መዝ 137:1
ሕዝ. 6:9መዝ 78:40, 41፤ ኢሳ 63:10
ሕዝ. 6:9ዘኁ 15:39
ሕዝ. 6:9ሕዝ 20:43፤ 36:31
ሕዝ. 6:10ሕዝ 33:29፤ ዳን 9:12፤ ዘካ 1:6
ሕዝ. 6:11ኤር 15:2፤ 16:4፤ ሕዝ 5:12
ሕዝ. 6:12ሕዝ 5:13
ሕዝ. 6:13ሕዝ 20:28
ሕዝ. 6:13ኤር 8:2
ሕዝ. 6:13ሕዝ 12:15
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 6:1-14

ሕዝቅኤል

6 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አዙረህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር። 3 እንዲህም በል፦ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለተራሮቹ፣ ለኮረብቶቹ፣ ለጅረቶቹና ለሸለቆዎቹ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እኔ በእናንተ ላይ ሰይፍ አመጣለሁ፤ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎቻችሁንም አጠፋለሁ። 4 መሠዊያዎቻችሁ ይፈርሳሉ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁ ይሰባበራሉ፤+ የታረዱ ወገኖቻችሁንም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ* ፊት እጥላለሁ።+ 5 የእስራኤልን ሕዝብ ሬሳ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ፊት እጥላለሁ፤ አጥንቶቻችሁንም በመሠዊያዎቻችሁ ዙሪያ እበትናለሁ።+ 6 በምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ያሉት ከተሞች ይወድማሉ፤+ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎቹም ፈራርሰው ባድማ ይሆናሉ።+ መሠዊያዎቻችሁ ፈራርሰው እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ አስጸያፊ የሆኑት ጣዖቶቻችሁ ይወገዳሉ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁ ተገንድሰው ይወድቃሉ፤ የሠራችኋቸው ሥራዎችም ተጠራርገው ይጠፋሉ። 7 የታረዱትም ሰዎች በመካከላችሁ ይወድቃሉ፤+ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+

8 “‘“ይሁንና የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ በየአገሩ በምትበተኑበት ጊዜ፣ ከእናንተ ውስጥ አንዳንዶቻችሁ በብሔራት መካከል ስትኖሩ ከሰይፍ ታመልጣላችሁና።+ 9 የተረፉትም ሰዎች በምርኮ በተወሰዱባቸው ብሔራት መካከል ሆነው እኔን ያስታውሳሉ።+ ከእኔ በራቀው ከሃዲ* ልባቸውና+ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን በፍትወት ስሜት በተመለከቱት* ዓይኖቻቸው የተነሳ+ ምን ያህል ልቤ እንዳዘነ ይገነዘባሉ። በሠሯቸው መጥፎና አስነዋሪ ነገሮች ሁሉ ያፍራሉ፤ እነዚህንም ነገሮች ይጸየፋሉ።+ 10 እኔ ይሖዋ እንደሆንኩና ይህን ጥፋት እንደማመጣባቸው የዛትኩት በከንቱ እንዳልሆነ ያውቃሉ።”’+

11 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የእስራኤል ቤት ሰዎች በሠሯቸው ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሳ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ስለሚወድቁ በእጅህ እያጨበጨብክ፣ በእግርህም መሬቱን እየደበደብክ አልቅስ።+ 12 በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፤ በቅርብ ያለው በሰይፍ ይወድቃል፤ ከእነዚህ ነገሮች ያመለጠና በሕይወት የተረፈ ሁሉ በረሃብ ያልቃል፤ ቁጣዬንም ሁሉ በእነሱ ላይ አወርዳለሁ።+ 13 የታረዱት ወገኖቻቸው አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው መካከል፣ በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ፣ ከፍ ባለ ኮረብታ ሁሉና በተራሮች አናት ሁሉ ላይ፣ ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች እንዲሁም በትላልቅ ዛፎች ቅርንጫፎች ሥር ይኸውም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ሁሉ ቁጣ ለማብረድ፣ ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያላቸው መባዎች*+ ባቀረቡባቸው ቦታዎች በሚወድቁበት ጊዜ+ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ 14 በእነሱ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱንም ባድማ አደርጋለሁ፤ መኖሪያ ቦታዎቻቸውም ሁሉ በዲብላ አቅራቢያ ካለው ምድረ በዳ የባሰ ባድማ ይሆናሉ። እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ