ጥያቄ 13
መጽሐፍ ቅዱስ ሥራን አስመልክቶ ምን ይላል?
“በሥራው የተካነን ሰው አይተሃል? በነገሥታት ፊት ይቆማል፤ ተራ በሆኑ ሰዎች ፊት አይቆምም።”
“የሚሰርቅ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ከዚህ ይልቅ ለተቸገረ ሰው የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በእጆቹ መልካም ተግባር እያከናወነ በትጋት ይሥራ።”
“ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ተግቶ በሚሠራው ሥራ ሁሉ ደስታ ከማግኘት የተሻለ ነገር የለም። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።”