የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lff ትምህርት 20
  • የክርስቲያን ጉባኤ አደረጃጀት ምን ይመስላል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የክርስቲያን ጉባኤ አደረጃጀት ምን ይመስላል?
  • ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጠለቅ ያለ ጥናት
  • ማጠቃለያ
  • ምርምር አድርግ
ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
lff ትምህርት 20
ምዕራፍ 20. በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ አንድ ወንድም ጥያቄ ሲጠይቅና የተለያዩ ሰዎች መልስ ለመመለስ እጃቸውን ሲያወጡ

ምዕራፍ 20

የክርስቲያን ጉባኤ አደረጃጀት ምን ይመስላል?

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

ይሖዋ የሥርዓት አምላክ ነው። (1 ቆሮንቶስ 14:33) ከዚህ አንጻር አገልጋዮቹም የተደራጁ ይሆናሉ ብሎ መጠበቅ ምክንያታዊ ነው። የክርስቲያን ጉባኤ የተደራጀው እንዴት ነው? እኛስ በዚህ ረገድ ምን ድርሻ ልናበረክት እንችላለን?

1. ጉባኤውን የሚመራው ማን ነው?

‘የጉባኤው ራስ ክርስቶስ ነው።’ (ኤፌሶን 5:23) ከሰማይ ሆኖ በዓለም ዙሪያ ያሉ የይሖዋ ሕዝቦችን እንቅስቃሴ ይመራል። ኢየሱስ ‘ታማኝና ልባም ባሪያን’ ሾሟል፤ ታማኝና ልባም ባሪያ በመንፈሳዊ የጎለመሱ ሽማግሌዎችን ያቀፈ አነስተኛ ቡድን ሲሆን የበላይ አካል ተብሎም ይታወቃል። (ማቴዎስ 24:45-47⁠ን አንብብ።) በመጀመሪያው መቶ ዘመን በኢየሩሳሌም እንደነበሩት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ሁሉ የበላይ አካሉም ለዓለም አቀፉ ጉባኤ መመሪያ ይሰጣል። (የሐዋርያት ሥራ 15:2) ሆኖም እነዚህ ሰዎች የድርጅታችን መሪዎች አይደሉም። መመሪያ ለማግኘት ይሖዋን የሚጠይቁና ቃሉን የሚያነብቡ ከመሆኑም ሌላ የኢየሱስን አመራር ይከተላሉ።

2. ሽማግሌዎች የሚባሉት እነማን ናቸው? ምን ሥራስ ያከናውናሉ?

ሽማግሌዎች በመንፈሳዊ ጠንካራ የሆኑ ክርስቲያን ወንዶች ናቸው፤ የአምላክን ቃል ያስተምራሉ እንዲሁም የአምላክን ሕዝብ በመርዳትና በማበረታታት እንደ እረኛ ሆነው ይንከባከባሉ። ለሥራቸው ምንም ዓይነት ክፍያ አይከፈላቸውም። ከዚህ ይልቅ ‘ለማገልገል በመጓጓት ሥራቸውን በአምላክ ፊት በፈቃደኝነት ይወጣሉ፤ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት አይመኙም።’ (1 ጴጥሮስ 5:1, 2) በጉባኤ ውስጥ፣ ሽማግሌዎችን የሚያግዙ የጉባኤ አገልጋዮችም አሉ፤ በጊዜ ሂደት እነዚህ አገልጋዮች ራሳቸው፣ ብቃቱን በማሟላት ሽማግሌ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ።

የበላይ አካሉ አንዳንድ ሽማግሌዎች የወረዳ የበላይ ተመልካቾች ሆነው እንዲያገለግሉ ይሾማል። እነዚህ ወንድሞች የተለያዩ ጉባኤዎችን በመጎብኘት መመሪያና ማበረታቻ ይሰጣሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘውን ብቃት ያሟሉ ወንድሞችን ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች አድርገው ይሾማሉ።—1 ጢሞቴዎስ 3:1-10, 12፤ ቲቶ 1:5-9

3. እያንዳንዱ የይሖዋ ምሥክር በጉባኤው ውስጥ ምን አስተዋጽኦ ያበረክታል?

በጉባኤ ውስጥ ያሉ ሁሉ በስብሰባ ላይ ተሳትፎ በማድረግና አቅማቸው በፈቀደ መጠን በአገልግሎት በመካፈል ‘የይሖዋን ስም ያወድሳሉ።’—መዝሙር 148:12, 13⁠ን አንብብ።

ጠለቅ ያለ ጥናት

ኢየሱስ ምን ዓይነት መሪ እንደሆነ፣ ሽማግሌዎች የእሱን ምሳሌ ለመከተል ጥረት የሚያደርጉት እንዴት እንደሆነ እንዲሁም ከኢየሱስና ከሽማግሌዎች ጋር ተባብረን መሥራት የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

4. ኢየሱስ ደግ መሪ ነው

ኢየሱስ አስደሳች ግብዣ አቅርቦልናል። ማቴዎስ 11:28-30⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ኢየሱስ ምን ዓይነት መሪ ነው? እኛስ ምን እንዲሰማን ይፈልጋል?

ሽማግሌዎች የኢየሱስን ምሳሌ የሚከተሉት እንዴት ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ።

ቪዲዮ፦ በኔፓል የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ሽማግሌዎች አፋጣኝ እርምጃ ወስደዋል (4:56)

መጽሐፍ ቅዱስ ሽማግሌዎች ሥራቸውን ማከናወን ያለባቸው እንዴት እንደሆነ በግልጽ ይናገራል።

ኢሳይያስ 32:2⁠ን እና 1 ጴጥሮስ 5:1-3⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ሽማግሌዎች ልክ እንደ ኢየሱስ ለሌሎች የእረፍት ምንጭ ለመሆን ጥረት እንደሚያደርጉ ማወቅህ ምን ስሜት ያሳድርብሃል?

  • ሽማግሌዎች ኢየሱስን እንደሚመስሉ የሚያሳዩባቸው ሌሎች አቅጣጫዎች የትኞቹ ናቸው?

5. ሽማግሌዎች እነሱ ራሳቸው ምሳሌ በመሆን ያስተምራሉ

ኢየሱስ፣ ሽማግሌዎች ለተሰጣቸው ሥራ ምን አመለካከት እንዲኖራቸው ይፈልጋል? ቪዲዮውን ተመልከቱ።

ቪዲዮ፦ ሽማግሌዎች ግንባር ቀደም ሁኑ! (7:39)

ኢየሱስ በጉባኤው ውስጥ ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል። ማቴዎስ 23:8-12⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በዚህ ጥቅስ መሠረት ከሽማግሌዎች ምን ይጠበቃል? የሃይማኖት መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን እየተከተሉ ያሉ ይመስልሃል?

ሀ. አንድ ሽማግሌ የራሱንም ሆነ የቤተሰቡን መንፈሳዊ ፍላጎት ለማሟላት ጥረት ሲያደርግ የሚያሳዩ ምስሎች፦ 1. መጽሐፍ ቅዱስን ከማጥናቱ በፊት ሲጸልይ 2. ከባለቤቱ ጋር ሆኖ ሴት ልጁን መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስተምር ለ. ይኸው ወንድምና ሚስቱ በጉባኤያቸው ያለች ሆስፒታል የገባችን እህት ሲጠይቁ ሐ. ይኸው ወንድም ለአንድ ሰው ቤቱ ሄዶ ሲሰብክ መ. 1. ይኸው ወንድም በጉባኤ ስብሰባ ላይ ንግግር ሲሰጥ 2. የስብሰባ አዳራሹን ወለል ሲያጸዳ የሚያሳዩ ምስሎች
  1. ሀ. ሽማግሌዎች የራሳቸውንም ሆነ የቤተሰባቸውን መንፈሳዊነት ለመጠበቅ ጥረት ያደርጋሉ

  2. ለ. ሽማግሌዎች በጉባኤ ውስጥ ላሉ ሁሉ አሳቢነት ያሳያሉ

  3. ሐ. ሽማግሌዎች አዘውትረው ይሰብካሉ

  4. መ. ሽማግሌዎች አስተማሪዎች ናቸው። በተጨማሪም እንደ ጽዳት ያሉ ሌሎች ሥራዎችን ይሠራሉ

6. ከሽማግሌዎች ጋር ተባብረን መሥራት አለብን

መጽሐፍ ቅዱስ ከሽማግሌዎች ጋር ተባብረን መሥራት ያለብን ለምን እንደሆነ ይነግረናል። ዕብራውያን 13:17⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • መጽሐፍ ቅዱስ አመራር ለሚሰጡን ሰዎች እንድንታዘዝና እንድንገዛ የሚመክረን መሆኑ ተገቢ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

ሉቃስ 16:10⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ቀላል በሚመስሉ ጉዳዮች ጭምር ሽማግሌዎችን መታዘዛችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “የአንድ ሃይማኖታዊ ድርጅት አባል መሆን አያስፈልግም።”

  • አንድ ሰው ከሌሎች ጋር አብሮ አምላክን ማገልገሉ ምን ጥቅም የሚያስገኝለት ይመስልሃል?

ማጠቃለያ

የክርስቲያን ጉባኤ ራስ ኢየሱስ ነው። በኢየሱስ አመራር ሥር ሆነው የሚያገለግሉትን ሽማግሌዎች በደስታ እንታዘዛለን፤ ምክንያቱም እነዚህ ወንድሞች የእረፍት ምንጭ ይሆኑልናል። በተጨማሪም እነሱ ራሳቸው ምሳሌ በመሆን ያስተምሩናል።

ክለሳ

  • የጉባኤው ራስ ማን ነው?

  • ሽማግሌዎች በጉባኤው ውስጥ ምን ጠቃሚ ሥራ ያከናውናሉ?

  • እያንዳንዱ የይሖዋ አገልጋይ በጉባኤው ውስጥ ምን አስተዋጽኦ ያበረክታል?

ግብ

ምርምር አድርግ

የበላይ አካሉና ሌሎች ሽማግሌዎች በዘመናችን ላሉ ክርስቲያኖች በጥልቅ እንደሚያስቡ የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ?

በእገዳ ሥር ያሉ ወንድሞችን ማበረታታት (4:22)

የወረዳ የበላይ ተመልካቾች ስለሚያከናውኑት ሥራ ማወቅ ትፈልጋለህ?

በገጠራማ ክልል የሚያገለግል የወረዳ የበላይ ተመልካች (4:51)

    የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ