የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lff ትምህርት 23
  • ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!
  • ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠለቅ ያለ ጥናት
  • ማጠቃለያ
  • ምርምር አድርግ
  • ጥምቀት ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
lff ትምህርት 23
ምዕራፍ 23. አንዲት ሴት በይሖዋ ምሥክሮች ሥርዓት መሠረት ሙሉ በሙሉ ውኃ ውስጥ በመጥለቅ ስትጠመቅ

ምዕራፍ 23

ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

ኢየሱስ ክርስቲያኖች መጠመቅ እንዳለባቸው አስተምሯል። (ማቴዎስ 28:19, 20⁠ን አንብብ።) ይሁንና ጥምቀት ምንድን ነው? በተጨማሪም አንድ ሰው እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ ምን ማድረግ ይኖርበታል?

1. ጥምቀት ምንድን ነው?

“መጠመቅ” የሚለው ቃል ውኃ ውስጥ “መጥለቅ” የሚል ትርጉም ካለው የግሪክኛ ቃል የተወሰደ ነው። ኢየሱስ በተጠመቀበት ወቅት ዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ከጠለቀ በኋላ “ከውኃው እንደወጣ” መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ማርቆስ 1:9, 10) በተመሳሳይም እውነተኛ ክርስቲያኖች የሚጠመቁት ሙሉ በሙሉ ውኃ ውስጥ በመግባት ወይም በመጥለቅ ነው።

2. አንድ ሰው መጠመቁ ምን ያሳያል?

አንድ ሰው መጠመቁ ሕይወቱን ለይሖዋ አምላክ ለመስጠት እንደወሰነ ያሳያል። ግለሰቡ ይህን ውሳኔ የሚያደርገው እንዴት ነው? ከመጠመቁ በፊት በግሉ ወደ ይሖዋ በመጸለይ እሱን ለዘላለም ማገልገል እንደሚፈልግ ይነግረዋል። ይሖዋን ብቻ ለማምለክና በሕይወቱ ውስጥ ለአምላክ ፈቃድ ቅድሚያ ለመስጠት ቃል ይገባል። ‘ራሱን ለመካድ’ እንዲሁም የኢየሱስን ትምህርትና ምሳሌ ‘ያለማቋረጥ ለመከተል’ ይወስናል። (ማቴዎስ 16:24) ሕይወቱን ለአምላክ ለመስጠት መወሰኑና መጠመቁ ከይሖዋና ከሌሎች የአምላክ አገልጋዮች ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ለመመሥረት ያስችለዋል።

3. አንድ ሰው ለጥምቀት ብቁ እንዲሆን ምን ማድረግ ይኖርበታል?

ከመጠመቅህ በፊት ስለ ይሖዋ መማርና በእሱ ላይ ጠንካራ እምነት መገንባት ይኖርብሃል። (ዕብራውያን 11:6⁠ን አንብብ።) እውቀትህና እምነትህ እያደገ ሲሄድ ለይሖዋ ያለህ ፍቅርም ይጨምራል። ይህ ደግሞ ስለ እሱ ለመስበክና እሱ ባወጣቸው መሥፈርቶች ለመመራት እንድትነሳሳ ያደርግሃል። (2 ጢሞቴዎስ 4:2፤ 1 ዮሐንስ 5:3) አንድ ሰው ‘ለይሖዋ በሚገባ ሁኔታ መመላለስና እሱን ሙሉ በሙሉ ማስደሰት’ ሲችል ሕይወቱን ለአምላክ ለመስጠትና ለመጠመቅ መወሰኑ አይቀርም።—ቆላስይስ 1:9, 10a

ጠለቅ ያለ ጥናት

ከኢየሱስ ጥምቀት ምን ትምህርት እንደምናገኝና አንድ ሰው ለዚህ ወሳኝ እርምጃ መዘጋጀት የሚችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

4. ከኢየሱስ ጥምቀት ትምህርት ማግኘት እንችላለን

ስለ ኢየሱስ ጥምቀት ይበልጥ ለማወቅ ማቴዎስ 3:13-17⁠ን አንብቡ። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ኢየሱስ የተጠመቀው በሕፃንነቱ ነው?

  • የተጠመቀው እንዴት ነው? እንዲሁ ውኃ በመረጨት ነው?

ኢየሱስ በምድር ላይ አምላክ የሰጠውን ልዩ ተልእኮ ማከናወን የጀመረው ከተጠመቀ በኋላ ነው። ሉቃስ 3:21-23⁠ን እና ዮሐንስ 6:38⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ በሕይወቱ ውስጥ ቅድሚያ የሰጠው ለየትኛው ሥራ ነው?

5. ጥምቀት ሊደረስበት የሚችል ግብ ነው

ሕይወትህን ለአምላክ ስለ መወሰንና ስለ መጠመቅ ስታስብ መጀመሪያ ላይ ፍርሃት ሊያድርብህ ይችላል። ሆኖም ይሖዋን ይበልጥ እያወቅከው ስትሄድ ይህን ትልቅ ውሳኔ ለማድረግ ብቁ እንደሆንክ ይሰማሃል። ይህን ውሳኔ ያደረጉ ሰዎችን ተሞክሮ ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ።

ቪዲዮ፦ ከይሖዋ ጋር ወዳጅነት መመሥረት (1:11)

ዮሐንስ 17:3⁠ን እና ያዕቆብ 1:5⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • አንድ ሰው ለመጠመቅ ብቁ እንዲሆን ምን ሊረዳው ይችላል?

ሀ. አንዲት ሴት በግሏ በምታቀርበው ጸሎት አማካኝነት ሕይወቷን ለአምላክ ለመስጠት ስትወስን ለ. ያቺው ሴት በይሖዋ ምሥክሮች ሥርዓት መሠረት ሙሉ በሙሉ ውኃ ውስጥ በመጥለቅ ስትጠመቅ
  1. ሀ. ለዘላለም ልናገለግለው እንደምንፈልግ ለይሖዋ በጸሎት በመንገር ሕይወታችንን ለእሱ ለመስጠት እንወስናለን

  2. ለ. ስንጠመቅ ሕይወታችንን ለአምላክ ለመስጠት እንደወሰንን ለሌሎች እናሳያለን

6. ስንጠመቅ የይሖዋ ቤተሰብ አባል እንሆናለን

ስንጠመቅ አንድነት ያለው ዓለም አቀፍ ቤተሰብ አባል እንሆናለን። ያደግንበት ቦታ ወይም የኋላ ታሪካችን የተለያየ ቢሆንም የምናምንባቸው ነገሮችም ሆኑ የምንመራባቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ተመሳሳይ ናቸው። መዝሙር 25:14⁠ን እና 1 ጴጥሮስ 2:17⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ጥምቀት አንድ ሰው ከይሖዋ ጋርም ሆነ ከሌሎች የይሖዋ አገልጋዮች ጋር ባለው ዝምድና ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?

አንዲት የተጠመቀች እህት ፊቷ በፈገግታ ተሞልቶ በጉባኤው ውስጥ ካሉ ሌሎች ወንድሞችና እህቶች ጋር ስላላት ጥሩ ዝምድና ስታስብ የሚያሳዩ ሥዕሎች፦ 1. ለአንዲት እህት ያሳሰባትን ነገር ስትነግራቸው 2. አንዲትን በዕድሜ የገፉ እህት በመደገፍ እንዲራመዱ ስትረዳ 3. በተለያየ ዕድሜ ላይ ከሚገኙ ጓደኞቿ ጋር አብራ ስትመገብ 4. ከሌላ እህት ጋር ሆና ለአንድ ሰው ስትሰብክ 5. በአንድ ትልቅ ስብሰባ ላይ የተለያየ ዘር ካላቸው ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች ጋር ፎቶ ስትነሳ

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ለመጠመቅ ዝግጁ አይደለሁም።”

  • አንተስ እንዲህ ይሰማሃል? ያም ሆኖ እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ መጣጣርህ አስፈላጊ እንደሆነ ታምናለህ?

ማጠቃለያ

ኢየሱስ ክርስቲያኖች መጠመቅ እንዳለባቸው አስተምሯል። አንድ ሰው እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ በይሖዋ ላይ ጠንካራ እምነት መገንባት፣ በእሱ መሥፈርቶች መመራትና ሕይወቱን ለእሱ ለመስጠት መወሰን አለበት።

ክለሳ

  • ጥምቀት ምንድን ነው? መጠመቅ አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው?

  • አንድ ሰው መጠመቁ ምን ያሳያል?

  • አንድ ሰው ሕይወቱን ለአምላክ ለመስጠት ከመወሰኑና ከመጠመቁ በፊት የትኞቹን ነገሮች ማድረግ አለበት?

ግብ

ምርምር አድርግ

ጥምቀት ምንድን ነው? ብዙዎች ስለ ጥምቀት ምን የተሳሳተ አመለካከት አላቸው?

“ጥምቀት ምንድን ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

a አንድ ሰው ከዚህ በፊት በሌላ ሃይማኖት ውስጥ ተጠምቆ የነበረ ቢሆንም እንኳ እንደገና መጠመቅ ያስፈልገዋል። ለምን? ምክንያቱም ቀደም ሲል የተጠመቀበት ሃይማኖት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት አያስተምርም።—የሐዋርያት ሥራ 19:1-5⁠ን እና ምዕራፍ 13⁠ን ተመልከት።

    የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ