የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lff ትምህርት 54
  • “ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚጫወተው ሚና

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚጫወተው ሚና
  • ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጠለቅ ያለ ጥናት
  • ማጠቃለያ
  • ምርምር አድርግ
ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
lff ትምህርት 54
ምዕራፍ 54. የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል አባላት አብረው ተሰብስበው

ምዕራፍ 54

“ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚጫወተው ሚና

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

ኢየሱስ የክርስቲያን ጉባኤ ራስ ነው። (ኤፌሶን 5:23) በዛሬው ጊዜ ‘በታማኝና ልባም ባሪያ’ አማካኝነት በምድር ላይ ያሉ ተከታዮቹን ከሰማይ ሆኖ ይመራል። (ማቴዎስ 24:45⁠ን አንብብ።) ይህ “ባሪያ” በራሱ በኢየሱስ የተሾመ እንደመሆኑ መጠን የተወሰነ ሥልጣን አለው፤ ያም ሆኖ የክርስቶስ ባሪያ በመሆን የጌታን ወንድሞች ማገልገሉን ይቀጥላል። ለመሆኑ “ታማኝና ልባም ባሪያ” ማን ነው? እኛን የሚንከባከበንስ እንዴት ነው?

1. “ታማኝና ልባም ባሪያ” ማን ነው?

ከጥንት ጊዜ አንስቶ ይሖዋ ሕዝቡን ለመምራት አንድን ሰው ወይም የተወሰኑ ሰዎችን ያቀፈን አነስተኛ ቡድን ሲጠቀም ቆይቷል። (ሚልክያስ 2:7፤ ዕብራውያን 1:1) ኢየሱስ ከሞተ በኋላ በኢየሩሳሌም ያሉ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች አመራር መስጠት ጀመሩ። (የሐዋርያት ሥራ 15:2) ይህንኑ አሠራር በመከተል በዛሬው ጊዜም የተወሰኑ ሽማግሌዎችን ያቀፈ አንድ አነስተኛ ቡድን ማለትም የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባል፤ እንዲሁም የስብከቱን ሥራ ይመራል። ይህ ቡድን ‘ኢየሱስ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ’ ነው። (ማቴዎስ 24:45ለ) ሁሉም የበላይ አካል አባላት በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ምድራዊ ሕይወታቸው ካበቃ በኋላ ከክርስቶስ ጋር በሰማይ ለመግዛት በተስፋ ይጠባበቃሉ።

2. ታማኙ ባሪያ ምን ዓይነት መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባል?

ኢየሱስ ታማኙ ባሪያ ለክርስቲያኖች ‘በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንደሚሰጥ’ ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:45ሀ) የምንበላው ምግብ ሰውነታችን ጠንካራና ጤናማ እንዲሆን ይረዳናል፤ በተመሳሳይም መንፈሳዊ ምግብ ማለትም በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘው ትምህርት ለይሖዋ ታማኝ ሆነን ለመቀጠልና ኢየሱስ የሰጠንን ሥራ ለማከናወን የሚያስፈልገንን ብርታት ይሰጠናል። (1 ጢሞቴዎስ 4:6) ይህን መንፈሳዊ ምግብ የምናገኘው በጉባኤ ስብሰባዎች፣ በትላልቅ ስብሰባዎች እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተመሠረቱ ጽሑፎችና ቪዲዮዎች አማካኝነት ሲሆን የአምላክን ፈቃድ ለማወቅ ብሎም ከእሱ ጋር ያለንን ወዳጅነት ለማጠናከር ይረዳናል።

ጠለቅ ያለ ጥናት

“ታማኝና ልባም ባሪያ” ማለትም የበላይ አካሉ የሚያስፈልገን ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።

በዓለም ዙሪያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካሉ መመሪያ ሲደርሳቸውና ተግባር ላይ ሲያውሉ የሚያሳዩ ሥዕሎች፦ 1. አንድ ቤተሰብ JW ብሮድካስቲንግ ሲያይ 2. የይሖዋ ምሥክር የሆኑ ፈቃደኛ ሠራተኞች የእርዳታ ቁሳቁሶችን መኪና ላይ ሲጭኑ 3. ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች ከምሥክርነት መስጫ ጋሪ አጠገብ ቆመው ሲሰብኩ 4. አንድ የጉባኤ ሽማግሌ በጉባኤ ስብሰባ ላይ ደብዳቤ ሲያነብ

የበላይ አካሉ በዓለም ዙሪያ ላሉ የይሖዋ ምሥክሮች መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባል፣ አመራር ይሰጣል እንዲሁም አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋል

3. የይሖዋ ሕዝቦች የተደራጁ መሆን አለባቸው

የበላይ አካሉ በኢየሱስ አመራር ሥር ሆኖ የይሖዋ ምሥክሮችን ሥራ ያደራጃል። የጥንቶቹ ክርስቲያኖችም ተመሳሳይ አሠራር ይከተሉ ነበር። ቪዲዮውን ተመልከቱ።

ቪዲዮ፦ ይሖዋ ሕዝቡን ያደራጃል (6:18)

አንደኛ ቆሮንቶስ 14:33, 40⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ይህ ጥቅስ ይሖዋ፣ ምሥክሮቹ የተደራጁ እንዲሆኑ እንደሚፈልግ የሚያሳየው እንዴት ነው?

4. ታማኙ ባሪያ የስብከቱ ሥራችንን ያደራጃል

የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ለስብከቱ ሥራ ከሁሉ የላቀ ቦታ ይሰጡ ነበር። የሐዋርያት ሥራ 8:14, 25⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ከጥንቶቹ ክርስቲያኖች መካከል ለስብከቱ ሥራ አመራር ይሰጡ የነበሩት እነማን ናቸው?

  • ጴጥሮስና ዮሐንስ ሌሎቹ ሐዋርያት ለሰጧቸው መመሪያ ምን ምላሽ ሰጥተዋል?

የበላይ አካሉ ለስብከቱ ሥራ ትልቅ ቦታ ይሰጣል። ቪዲዮውን ተመልከቱ።

ቪዲዮ፦ በስብከቱ ሥራ ላይ ማተኮር (1:24)

ኢየሱስ የስብከቱ ሥራ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ተናግሯል። ማርቆስ 13:10⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • የበላይ አካሉ ለስብከቱ ሥራ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ለምንድን ነው?

  • ይህን ዓለም አቀፋዊ ሥራ ለማደራጀት “ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

5. ታማኙ ባሪያ አመራር ይሰጣል

የበላይ አካሉ በዓለም ዙሪያ ላሉ ክርስቲያኖች አመራር ይሰጣል። አመራር የሚሰጠው በምን ላይ ተመሥርቶ ነው? በጥንቶቹ ክርስቲያኖች ዘመን የነበረውን የበላይ አካል እንደ ምሳሌ እንመልከት። የሐዋርያት ሥራ 15:1, 2⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በጥንት ዘመን በነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች መካከል ምን ውዝግብ ተነስቶ ነበር?

  • ጳውሎስ፣ በርናባስና ሌሎች ወንድሞች ለጉዳዩ መፍትሔ ለማግኘት ምን አደረጉ?

የሐዋርያት ሥራ 15:12-18, 23-29⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • የበላይ አካሉ ውሳኔ ከማድረጉ በፊት የአምላክን አመራር ለማግኘት ምን አደረገ?—ቁጥር 12, 15 እና 28⁠ን ተመልከት።

የሐዋርያት ሥራ 15:30, 31⁠ን እንዲሁም 16:4, 5⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ለበላይ አካሉ መመሪያ ምን ምላሽ ሰጡ?

  • ታዛዥ በመሆናቸው ይሖዋ የባረካቸው እንዴት ነው?

ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 3:16⁠ን እና ያዕቆብ 1:5⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በዛሬው ጊዜ የበላይ አካሉ ውሳኔ የሚያደርገው እንዴት ነው?

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “በበላይ አካሉ መመራት ማለት የሰው ተከታይ መሆን ማለት ነው።”

  • የበላይ አካሉን የሚመራው ኢየሱስ ነው ብለህ እንድታምን የሚያደርግህ ምንድን ነው?

ማጠቃለያ

በክርስቶስ የተሾመው “ታማኝና ልባም ባሪያ” የበላይ አካሉ ነው። በዓለም ዙሪያ ላሉ ክርስቲያኖች አመራር ይሰጣል እንዲሁም መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባል።

ክለሳ

  • ‘ታማኝና ልባም ባሪያን’ የሾመው ማን ነው?

  • የበላይ አካሉ እኛን የሚንከባከበን እንዴት ነው?

  • በክርስቶስ የተሾመው “ታማኝና ልባም ባሪያ” የበላይ አካሉ እንደሆነ ታምናለህ?

ግብ

ምርምር አድርግ

የበላይ አካሉ የተደራጀው እንዴት ነው?

“የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል ማን ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

የበላይ አካሉ እምነት የሚጣልበት መንፈሳዊ ምግብ እንድናገኝ የሚያደርገው እንዴት ነው?

ትክክለኛ መረጃ የያዙ ጽሑፎችን ማዘጋጀት (17:18)

አንዲትን እህት በጣም ያስደሰታት የበላይ አካሉ ያደረገው የትኛው ዝግጅት ነው?

በፔሩ ያሉ መስማት የተሳናቸው ያገኙት በረከት (5:17)

የጉባኤ ስብሰባዎቻችንና ትላልቅ ስብሰባዎቻችን ይሖዋ የበላይ አካሉን እየመራው እንዳለ የሚያሳዩት እንዴት ነው?

ይሖዋ ሕዝቡን ያስተምራል (9:39)

    የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ