ራእይ 8:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የመጀመሪያው መለከቱን ነፋ። ከደም ጋር የተቀላቀለ በረዶና እሳት ታየ፤ ወደ ምድርም ተወረወረ፤+ የምድር አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የዛፎችም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የለመለሙ ተክሎችም ሁሉ ተቃጠሉ።+ 8 ሁለተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። በእሳት የተቀጣጠለ ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገርም ወደ ባሕር ተወረወረ።+ የባሕሩም አንድ ሦስተኛ ደም ሆነ፤+ ራእይ 8:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሦስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። እንደ መብራት ቦግ ያለ አንድ ትልቅ ኮከብም ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞች አንድ ሦስተኛና በውኃ ምንጮች ላይ ወደቀ።+ ራእይ 8:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፣+ የጨረቃ አንድ ሦስተኛና የከዋክብት አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ይህም የሆነው የእነዚህ አካላት አንድ ሦስተኛው እንዲጨልም+ እንዲሁም የቀኑ አንድ ሦስተኛና የሌሊቱ አንድ ሦስተኛ ብርሃን እንዳያገኝ ነው። ራእይ 9:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 አምስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ።+ እኔም ከሰማይ ወደ ምድር የወደቀ አንድ ኮከብ አየሁ፤ ለእሱም የጥልቁ መግቢያ ቁልፍ+ ተሰጠው። ራእይ 9:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ስድስተኛው መልአክ+ መለከቱን ነፋ።+ ደግሞም በአምላክ ፊት ካለው የወርቅ መሠዊያ+ ቀንዶች የወጣ አንድ ድምፅ ሰማሁ፤ ራእይ 11:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ።+ በሰማይም ታላላቅ ድምፆች እንዲህ ሲሉ ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና+ የእሱ መሲሕ+ መንግሥት ሆነ፤ እሱም ለዘላለም ይነግሣል።”+
7 የመጀመሪያው መለከቱን ነፋ። ከደም ጋር የተቀላቀለ በረዶና እሳት ታየ፤ ወደ ምድርም ተወረወረ፤+ የምድር አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የዛፎችም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የለመለሙ ተክሎችም ሁሉ ተቃጠሉ።+ 8 ሁለተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። በእሳት የተቀጣጠለ ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገርም ወደ ባሕር ተወረወረ።+ የባሕሩም አንድ ሦስተኛ ደም ሆነ፤+
12 አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፣+ የጨረቃ አንድ ሦስተኛና የከዋክብት አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ይህም የሆነው የእነዚህ አካላት አንድ ሦስተኛው እንዲጨልም+ እንዲሁም የቀኑ አንድ ሦስተኛና የሌሊቱ አንድ ሦስተኛ ብርሃን እንዳያገኝ ነው።
15 ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ።+ በሰማይም ታላላቅ ድምፆች እንዲህ ሲሉ ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና+ የእሱ መሲሕ+ መንግሥት ሆነ፤ እሱም ለዘላለም ይነግሣል።”+