ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። ማስኪል። የዚፍ ሰዎች ወደ ሳኦል መጥተው “ዳዊት እኛ ጋ ተደብቋል” ባሉት ጊዜ ዳዊት የዘመረው መዝሙር።+
54 አምላክ ሆይ፣ በስምህ አድነኝ፤+
በኃይልህም ደግፈኝ።+
2 አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+
ለአፌም ቃል ትኩረት ስጥ።
3 ባዕዳን በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤
ጨካኝ ሰዎችም ሕይወቴን ይሻሉ።+
ስለ አምላክ ምንም ግድ የላቸውም።+ (ሴላ)
4 እነሆ፣ አምላክ ረዳቴ ነው፤+
ይሖዋ እኔን ከሚደግፉ ጋር ነው።
5 የገዛ ክፋታቸውን በጠላቶቼ ላይ ይመልስባቸዋል፤+
በታማኝነትህ አስወግዳቸው።+
6 ለአንተ በፈቃደኝነት መሥዋዕት አቀርባለሁ።+
ይሖዋ ሆይ፣ መልካም ነውና፣ ስምህን አወድሳለሁ።+
7 ከጭንቅ ሁሉ ያድነኛልና፤+
ጠላቶቼንም በድል አድራጊነት እመለከታለሁ።+