ዘዳግም
1 ሙሴ በዮርዳኖስ ክልል በሚገኘው ምድረ በዳ ይኸውም በፋራን፣ በጦፌል፣ በላባ፣ በሃጼሮት እና በዲዛሃብ መካከል ከሚገኘው ከሱፈ ፊት ለፊት ባለው በረሃማ ሜዳ ላይ ለነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ የተናገረው ቃል ይህ ነው። 2 ወደ ሴይር ተራራ በሚወስደው መንገድ በኩል ከኮሬብ እስከ ቃዴስበርኔ+ የ11 ቀን መንገድ ነው። 3 በ40ኛው ዓመት፣+ በ11ኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሙሴ ለእስራኤላውያን* እንዲነግራቸው ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ነገራቸው። 4 ይህን ያደረገው በሃሽቦን ይኖር የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን+ ድል ካደረገና በአስታሮት ይኖር የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ኦግን+ ኤድራይ+ ላይ* ካሸነፈ በኋላ ነው። 5 በዮርዳኖስ ክልል፣ በሞዓብ ምድር ሙሴ ይህን ሕግ እንዲህ በማለት ያብራራ ጀመር፦+
6 “ይሖዋ አምላካችን በኮሬብ እንዲህ አለን፦ ‘በዚህ ተራራማ አካባቢ ለረጅም ጊዜ ቆይታችኋል።+ 7 ተነስታችሁ ወደ አሞራውያን+ ተራራማ አካባቢ እንዲሁም በአረባ፣+ በተራራማው አካባቢ፣ በሸፌላ፣ በኔጌብ እና በባሕሩ ዳርቻ+ ወደሚገኙት ጎረቤቶቻቸው ሁሉ ብሎም ወደ ከነአናውያን ምድርና ወደ ሊባኖስ*+ በመጓዝ እስከ ታላቁ ወንዝ ማለትም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ+ ድረስ ሂዱ። 8 እነሆ በፊታችሁ ይህችን ምድር አስቀምጫለሁ። ይሖዋ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና+ ለያዕቆብ+ እንዲሁም ከእነሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቻቸው ሊሰጣቸው የማለላቸውን ምድር+ ገብታችሁ ውረሱ።’
9 “እኔም በዚያን ጊዜ እንዲህ አልኳችሁ፦ ‘እኔ ብቻዬን እናንተን ልሸከማችሁ አልችልም።+ 10 ይሖዋ አምላካችሁ ቁጥራችሁን አብዝቶታል፤ ይኸው ዛሬ ከብዛታችሁ የተነሳ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት ሆናችኋል።+ 11 የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ ሺህ ጊዜ ያብዛችሁ፤+ ደግሞም በገባላችሁ ቃል መሠረት ይባርካችሁ።+ 12 ይሁንና እኔ ብቻዬን የእናንተን ሸክምና ጫና እንዲሁም ጠብ እንዴት መሸከም እችላለሁ?+ 13 ከየነገዶቻችሁ ጥበበኛና አስተዋይ የሆኑ እንዲሁም ተሞክሮ ያካበቱ ወንዶችን ምረጡ፤ እኔም በእናንተ ላይ መሪ አድርጌ እሾማቸዋለሁ።’+ 14 እናንተም ‘አድርጉ ያልከን ነገር መልካም ነው’ በማለት መለሳችሁልኝ። 15 እኔም ጥበበኛ የሆኑትንና ተሞክሮ ያካበቱትን የየነገዳችሁን መሪዎች ወስጄ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆች፣ የሃምሳ አለቆችና የአሥር አለቆች እንዲሁም የየነገዶቻችሁ ሹማምንት አድርጌ በእናንተ ላይ ሾምኳቸው።+
16 “በዚያን ጊዜ ለዳኞቻችሁ ይህን መመሪያ ሰጠኋቸው፦ ‘በወንድሞቻችሁ መካከል የተፈጠረን አንድ ጉዳይ በምትሰሙበት ጊዜ በሰውየውና በወንድሙ ወይም በባዕድ አገሩ ሰው መካከል+ በጽድቅ ፍረዱ።+ 17 በምትፈርዱበት ጊዜ አታዳሉ።+ ትንሹንም ሆነ ትልቁን እኩል ስሙ።+ ፍርድ የአምላክ ስለሆነ+ ሰውን አትፍሩ፤+ አንድ ጉዳይ ከከበዳችሁ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እሰማዋለሁ።’+ 18 በዚያን ጊዜ ማድረግ ስላለባችሁ ነገር ሁሉ መመሪያ ሰጠኋችሁ።
19 “ከዚያም ይሖዋ አምላካችን ባዘዘን መሠረት ከኮሬብ በመነሳት ያን ያያችሁትን ጭልጥ ያለና የሚያስፈራ ምድረ በዳ+ አቋርጠን ወደ አሞራውያን ተራራማ አካባቢዎች+ በሚወስደው መንገድ ተጓዝን፤ በመጨረሻም ቃዴስበርኔ+ ደረስን። 20 እኔም እንዲህ አልኳችሁ፦ ‘አምላካችን ይሖዋ ወደሚሰጠን ወደ አሞራውያን ተራራማ አካባቢዎች ደርሳችኋል። 21 ይኸው አምላካችሁ ይሖዋ ምድሪቱን ለእናንተ ሰጥቷችኋል። የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ በነገራችሁ መሠረት ተነሱና ውረሷት።+ አትፍሩ ወይም አትሸበሩ።’
22 “ሆኖም እናንተ ሁላችሁም ወደ እኔ መጥታችሁ እንዲህ አላችሁኝ፦ ‘ምድሪቱን እንዲሰልሉልን እንዲሁም በየትኛው መንገድ መሄድ እንደሚኖርብንና ምን ዓይነት ከተሞች እንደሚያጋጥሙን አይተው እንዲነግሩን ሰዎችን አስቀድመን እንላክ።’+ 23 ይህም ሐሳብ መልካም መስሎ ታየኝ፤ በመሆኑም ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ አንድ ሰው ይኸውም ከመካከላችሁ 12 ሰዎችን መረጥኩ።+ 24 እነሱም ተነስተው ወደ ተራራማው አካባቢ ሄዱ፤+ እስከ ኤሽኮል ሸለቆ* ድረስ በመዝለቅም ምድሪቱን ሰለሉ። 25 ምድሪቱ ከምታፈራው ፍሬም የተወሰነ ይዘው ወደ እኛ መጡ፤ እንዲሁም ‘አምላካችን ይሖዋ የሚሰጠን ምድር መልካም ናት’ ብለው ነገሩን።+ 26 እናንተ ግን ወደዚያ ለመውጣት ፈቃደኞች አልሆናችሁም፤ በአምላካችሁ በይሖዋ ትእዛዝም ላይ ዓመፃችሁ።+ 27 በየድንኳኖቻችሁ ውስጥ ሆናችሁ እንዲህ በማለት አጉተመተማችሁ፦ ‘ይሖዋ ስለጠላን አሞራውያን እንዲያጠፉን ለእነሱ አሳልፎ ሊሰጠን ከግብፅ ምድር አወጣን። 28 ታዲያ የምንሄደው ወዴት ነው? ወንድሞቻችን “ሰዎቹ ከእኛ ይልቅ ብርቱና ረጃጅሞች ናቸው፤ ከተሞቻቸውም ቢሆኑ ታላላቅና እስከ ሰማይ በሚደርስ ቅጥር የታጠሩ ናቸው፤+ እንዲያውም በዚያ የኤናቅን+ ልጆች አይተናል” በማለት ልባችን እንዲቀልጥ አድርገዋል።’+
29 “በመሆኑም እኔ እንዲህ አልኳችሁ፦ ‘በእነሱ የተነሳ በፍርሃት አትራዱ ወይም አትሸበሩ።+ 30 አምላካችሁ ይሖዋ በፊታችሁ ይሄዳል፤ የገዛ ዓይናችሁ እያየ በግብፅ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ይዋጋላችኋል።+ 31 በምድረ በዳም ተጉዛችሁ እዚህ እስክትደርሱ ድረስ አንድ አባት ልጁን እንደሚሸከም አምላካችሁ ይሖዋም በሄዳችሁበት ሁሉ እንዴት እንደተሸከማችሁ አይታችኋል።’ 32 እናንተ ግን ይህ ሁሉ ተደርጎላችሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እምነት አላሳደራችሁም፤+ 33 እሱ የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ ከፊት ከፊታችሁ ይሄድ ነበር። በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባችሁ ለማሳየትም ሌሊት ሌሊት በእሳት፣ ቀን ቀን ደግሞ በደመና ይመራችሁ ነበር።+
34 “በዚህ ጊዜ ይሖዋ ያላችሁትን ሰማ፤ ተቆጥቶም እንዲህ ሲል ማለ፦+ 35 ‘ለአባቶቻችሁ ለመስጠት የማልኩላቸውን መልካሚቱን ምድር ከዚህ ክፉ ትውልድ መካከል አንድም ሰው አያያትም፤+ 36 ከየፎኒ ልጅ ከካሌብ በስተቀር ማንም አያያትም። እሱ ያያታል፤ ይሖዋን በሙሉ ልቡ ስለተከተለም የረገጣትን ምድር ለእሱና ለልጆቹ እሰጣታለሁ።+ 37 (ይሖዋ በእናንተ የተነሳ በእኔም ላይ እንኳ ተቆጥቶ እንዲህ አለኝ፦ “አንተም ብትሆን ወደዚያ አትገባም።+ 38 ወደ ምድሪቱ የሚገባው+ በፊትህ የሚቆመው የነዌ ልጅ ኢያሱ ነው።+ እስራኤላውያን ምድሪቱን እንዲወርሱ የሚያደርገው እሱ ስለሆነ አበርታው።”)*+ 39 በተጨማሪም ለምርኮ ይዳረጋሉ+ ያላችኋቸው ልጆቻችሁ እንዲሁም ዛሬ ክፉና ደጉን የማያውቁት ወንዶች ልጆቻችሁ ወደዚያ ይገባሉ፤ እኔም ምድሪቱን እንዲወርሷት ለእነሱ እሰጣታለሁ።+ 40 እናንተ ግን አቅጣጫ በመቀየር ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ አድርጋችሁ ወደ ምድረ በዳው ሂዱ።’+
41 “እናንተም በዚህ ጊዜ እንዲህ አላችሁኝ፦ ‘በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናል። በቃ፣ አምላካችን ይሖዋ ባዘዘን መሠረት ወጥተን እንዋጋለን!’ በመሆኑም እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያዎቻችሁን ታጠቃችሁ፤ ወደ ተራራው መውጣት ቀላል መስሎ ታይቷችሁ ነበር።+ 42 ይሁንና ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እንዲህ በላቸው፦ “እኔ አብሬያችሁ ስለማልሆን ወጥታችሁ ውጊያ እንዳትገጥሙ።+ እንዲህ ብታደርጉ ግን ጠላቶቻችሁ ድል ያደርጓችኋል።”’ 43 እኔም ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም። ከዚህ ይልቅ በይሖዋ ትእዛዝ ላይ በማመፅ በእብሪት ወደ ተራራው ለመውጣት ሞከራችሁ። 44 ከዚያም በተራራው ላይ ይኖሩ የነበሩት አሞራውያን እናንተን ለመግጠም ወጡ፤ እነሱም ልክ እንደ ንብ እየተከታተሉ አሳደዷችሁ፤ ከሴይር አንስቶ እስከ ሆርማ ድረስም በታተኗችሁ። 45 ስለሆነም ተመልሳችሁ በይሖዋ ፊት ማልቀስ ጀመራችሁ፤ ሆኖም ይሖዋ ጩኸታችሁን አልሰማም፤ ጆሮውንም አልሰጣችሁም። 46 እነዚያን ሁሉ ቀናት በቃዴስ የተቀመጣችሁትም ለዚህ ነው።
2 ከዚያም ልክ ይሖዋ በነገረኝ መሠረት ተመልሰን ወደ ቀይ ባሕር የሚወስደውን መንገድ በመከተል ወደ ምድረ በዳው ተጓዝን፤+ በሴይር ተራራ አካባቢም ለብዙ ቀናት ተንከራተትን። 2 በመጨረሻም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ 3 ‘እንግዲህ በዚህ ተራራ አካባቢ ብዙ ተንከራታችኋል። አሁን ወደ ሰሜን አቅኑ። 4 ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዝ፦ “እንግዲህ በሴይር በሚኖሩት+ በወንድሞቻችሁ በኤሳው ዘሮች+ ድንበር አልፋችሁ ልትሄዱ ነው፤ እነሱም ይፈሯችኋል፤+ ቢሆንም ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ። 5 ከምድራቸው ላይ የእግር መርገጫ የምታክል መሬት እንኳ ስለማልሰጣችሁ ከእነሱ ጋር እንዳትጣሉ፤* ምክንያቱም የሴይርን ተራራ ለኤሳው ርስት አድርጌ ሰጥቼዋለሁ።+ 6 ለምትበሉት ምግብም ሆነ ለምትጠጡት ውኃ ገንዘብ ክፈሏቸው።+ 7 አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና። በዚህ ጭልጥ ያለ ምድረ በዳ እንደተጓዝክ በሚገባ ያውቃል። በእነዚህ 40 ዓመታት አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ስለነበር ምንም የጎደለብህ ነገር የለም።”’+ 8 ስለዚህ በሴይር በሚኖሩት ወንድሞቻችን በኤሳው ዘሮች በኩል አልፈን ሄድን፤+ ወደ አረባ ከሚወስደው መንገድ፣ ከኤላት እና ከዔጽዮንጋብር ርቀን ተጓዝን።+
“በመቀጠልም ተነስተን ወደ ሞዓብ ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ተጓዝን።+ 9 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ከሞዓብ ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ ስለማልሰጥህ ከእሱ ጋር አትጣላ ወይም ጦርነት አትግጠም፤ ምክንያቱም ኤርን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።+ 10 (ታላቅና ብዙ እንዲሁም ልክ እንደ ኤናቃውያን ቁመተ ረጃጅም የሆኑት ኤሚማውያን+ ቀደም ሲል በዚያ ይኖሩ ነበር። 11 ረፋይማውያንም+ ልክ እንደ ኤናቃውያን+ ይቆጠሩ ነበር፤ ሞዓባውያንም ኤሚማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። 12 ሆራውያን+ ቀደም ሲል በሴይር ይኖሩ ነበር፤ እስራኤላውያን ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጣቸው ምድር ላይ እንደሚያደርጉት ሁሉ የኤሳውም ዘሮች ሆራውያንን በማስለቀቅና በማጥፋት በምድራቸው ላይ መኖር ጀመሩ።)+ 13 በሉ አሁን ተነሱና የዘረድን ሸለቆ* አቋርጣችሁ ሂዱ።’ ስለዚህ የዘረድን ሸለቆ*+ አቋርጠን ሄድን። 14 ከቃዴስበርኔ ተነስተን የዘረድን ሸለቆ* እስክናቋርጥ ድረስ 38 ዓመት ፈጅቶብናል፤ በዚህ ጊዜም ይሖዋ ለእነሱ በማለላቸው መሠረት ለጦርነት ብቁ የሆነው ትውልድ በሙሉ ከሕዝቡ መካከል አለቀ።+ 15 ሙሉ በሙሉ እስኪጠፉም ድረስ የይሖዋ እጅ ከሕዝቡ መካከል ሊያጠፋቸው በእነሱ ላይ ነበር።+
16 “ለጦርነት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ሞተው እንዳለቁ+ 17 ይሖዋ በድጋሚ እንዲህ አለኝ፦ 18 ‘ዛሬ በሞዓብ ክልል ይኸውም በኤር በኩል ታልፋለህ። 19 ወደ አሞናውያን በቀረብክ ጊዜ እነሱን አታስቆጣቸው ወይም አትተናኮላቸው፤ ምክንያቱም ምድሪቱን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ስለሰጠኋቸው ከአሞን ልጆች ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ አልሰጥህም።+ 20 ይህችም ምድር የረፋይማውያን+ ምድር ተደርጋ ትቆጠር ነበር። (ቀደም ሲል ረፋይማውያን በዚያ ይኖሩ ነበር፤ አሞናውያንም ዛምዙሚማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። 21 እነሱም ታላቅና ቁጥራቸው የበዛ እንዲሁም ልክ እንደ ኤናቃውያን+ ቁመተ ረጃጅሞች ነበሩ፤ ይሖዋ ግን ከአሞናውያን ፊት አጠፋቸው፤ እነሱም ምድራቸውን አስለቅቀው በዚያ ሰፈሩ። 22 አሁን በሴይር ለሚኖሩት+ የኤሳው ዘሮች ሆራውያንን+ ከፊታቸው ባጠፋላቸው ጊዜ ያደረገላቸው ይህንኑ ነበር፤ በዚህም የተነሳ የኤሳው ዘሮች እነሱን አስለቅቀው እስከ ዛሬ ድረስ በምድራቸው ላይ እየኖሩ ነው። 23 አዊማውያን ደግሞ ከካፍቶር* የተገኙት ካፍቶሪማውያን+ እነሱን አጥፍተው በምድራቸው ላይ መኖር እስከጀመሩበት ጊዜ ድረስ እስከ ጋዛ+ በሚገኙት መንደሮች ይኖሩ ነበር።)
24 “‘ተነሱና የአርኖንን ሸለቆ*+ አቋርጣችሁ ሂዱ። ይኸው የሃሽቦንን ንጉሥ አሞራዊውን ሲሖንን+ በእጃችሁ ሰጥቻችኋለሁ። በመሆኑም ምድሩን መውረስ ጀምሩ፤ ከእሱም ጋር ጦርነት ግጠሙ። 25 በዚህች ዕለት፣ ስለ እናንተ የሰሙ ከሰማይ በታች ያሉ ሕዝቦች ሁሉ እንዲሸበሩና በፍርሃት እንዲርዱ አደርጋለሁ። በእናንተም የተነሳ ይታወካሉ፤ ምጥም ይይዛቸዋል።’+
26 “ከዚያም እኔ ከቀደሞት+ ምድረ በዳ ለሃሽቦን ንጉሥ ለሲሖን እንዲህ የሚል የሰላም መልእክት እንዲነግሩት መልእክተኞችን ላክሁበት፦+ 27 ‘ምድርህን አቋርጬ እንዳልፍ ፍቀድልኝ። ከመንገዱ አልወጣም፤ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አልልም።+ 28 በገንዘብ የምትሸጥልኝን ምግብ ብቻ እበላለሁ፤ በገንዘብ የምትሰጠኝንም ውኃ ብቻ እጠጣለሁ። ምድሩን ረግጬ እንዳልፍ ብቻ ፍቀድልኝ፤ 29 አምላካችን ይሖዋ ወደሚሰጠን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በሴይር የሚኖሩት የኤሳው ዘሮችና በኤር የሚኖሩት ሞዓባውያን እንዲሁ አድርገውልኛል።’ 30 የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን ግን በእሱ በኩል አቋርጠን እንድናልፍ አልፈቀደልንም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሐሳበ ግትር እንዲሆንና ልቡ እንዲደነድን ፈቅዶ ነበር፤+ ይህን ያደረገው ይኸው ዛሬ እንደምታዩት እጃችሁ ላይ እንዲወድቅ ነው።+
31 “ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እነሆ ሲሖንን እና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ። እንግዲህ ምድሩን ለመውረስ ተነስ።’+ 32 ሲሖንም ከመላው ሕዝቡ ጋር በመሆን ያሃጽ+ ላይ እኛን ለመውጋት በወጣ ጊዜ 33 አምላካችን ይሖዋ በእጃችን አሳልፎ ሰጠው፤ ስለዚህ እሱንም ሆነ ልጆቹን እንዲሁም ሕዝቡን በሙሉ ድል አደረግናቸው። 34 በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ እያንዳንዱን ከተማ ሙሉ በሙሉ አጠፋን። ማንንም በሕይወት አላስተረፍንም።+ 35 ለራሳችን ማርከን የወሰድነው እንስሶችንና በያዝናቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘነውን ንብረት ብቻ ነው። 36 በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ካለችው ከአሮዔር+ (በሸለቆው ውስጥ የምትገኘውን ከተማ ጨምሮ) እስከ ጊልያድ ድረስ ከእጃችን ያመለጠ አንድም ከተማ አልነበረም። አምላካችን ይሖዋ ሁሉንም በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶን ነበር።+ 37 ሆኖም ወደ አሞናውያን ምድር፣+ ወደ ያቦቅ ሸለቆ*+ ዳርቻ ሁሉና በተራራማው አካባቢ ወደሚገኙት ከተሞች ወይም አምላካችን ይሖዋ ወደከለከለን ወደ ሌላ ማንኛውም ቦታ አልቀረባችሁም።
3 “ከዚያም ተመልሰን በባሳን መንገድ ወጣን። የባሳን ንጉሥ ኦግም ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በመሆን ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥመን ወጣ።+ 2 በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እሱንም ሆነ ሕዝቡን ሁሉ እንዲሁም ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ አትፍራው፤ አንተም በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግከው ሁሉ በእሱም ላይ ታደርግበታለህ።’ 3 ስለዚህ አምላካችን ይሖዋ የባሳንን ንጉሥ ኦግንና ሕዝቡን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም ከሕዝቡ መካከል አንድም ሰው ሳናስቀር ሁሉንም ደመሰስን። 4 ከዚያም ከተሞቹን በሙሉ ያዝን። ከእነሱ ያልወሰድነው አንድም ከተማ አልነበረም፤ በባሳን ባለው በኦግ መንግሥት ሥር የሚገኘውን የአርጎብን ክልል በሙሉ ይኸውም 60 ከተሞችን ወሰድን።+ 5 እነዚህ ከተሞች በሙሉ በረጃጅም ቅጥሮች የታጠሩ እንዲሁም በሮችና መቀርቀሪያዎች ያሏቸው ነበሩ፤ ከእነዚህም በተጨማሪ በጣም ብዙ የገጠር ከተሞች ነበሩ። 6 ሆኖም እያንዳንዱን ከተማ እንዲሁም ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን+ በማጥፋት በሃሽቦን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግነው ሁሉ እነዚህንም ሙሉ በሙሉ ደመሰስናቸው።+ 7 ከብቶቹንና ከየከተማው የማረክናቸውን ነገሮች ሁሉ ለራሳችን ወሰድን።
8 “በዚያን ጊዜም ከአርኖን ሸለቆ* አንስቶ እስከ ሄርሞን ተራራ+ ድረስ ባለው በዮርዳኖስ ክልል ከነበሩት ከሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት እጅ ምድራቸውን ወሰድን፤+ 9 (ሲዶናውያን የሄርሞንን ተራራ ሲሪዮን ብለው ሲጠሩት አሞራውያን ደግሞ ሰኒር ብለው ይጠሩት ነበር፤) 10 በባሳን ባለው በኦግ መንግሥት ሥር የሚገኙትን ከተሞች ይኸውም በአምባው ላይ የሚገኙትን ከተሞች በሙሉ፣ ጊልያድን በሙሉ፣ ባሳንን በሙሉ እስከ ሳልካ ድረስ እንዲሁም ኤድራይን+ ወሰድን። 11 ከረፋይም ወገን የተረፈው የባሳን ንጉሥ ኦግ ብቻ ነበር። ቃሬዛው እንኳ የብረት* ቃሬዛ* ነበር፤ አሁንም የአሞናውያን ከተማ በሆነችው በራባ ይገኛል። በሰው ክንድ* ሲለካ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ስፋቱ ደግሞ አራት ክንድ ነበር። 12 በዚያን ጊዜ ይህችን ምድር ወረስን፤ በአርኖን ሸለቆ* አጠገብ ከምትገኘው ከአሮዔር+ አንስቶ ያለውን ምድር እንዲሁም የጊልያድን ተራራማ አካባቢ እኩሌታ ከነከተሞቹ ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው።+ 13 የቀረውን የጊልያድን ክፍልና በኦግ ግዛት ሥር ያለውን ባሳንን በሙሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ።+ የባሳን ይዞታ የሆነው የአርጎብ አካባቢ በሙሉ የረፋይም ምድር ተብሎ ይጠራ ነበር።
14 “የምናሴ ልጅ ያኢር+ የአርጎብን ክልል+ በሙሉ እስከ ገሹራውያን እና እስከ ማአካታውያን+ ወሰን ድረስ ያለውን ወሰደ፤ በባሳን የሚገኙትን እነዚህን መንደሮች በራሱ ስም ሃዎትያኢር*+ ብሎ ሰየማቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሚጠሩት በዚህ ስም ነው። 15 ጊልያድን ደግሞ ለማኪር ሰጠሁት።+ 16 ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን+ የአርኖንን ሸለቆ* መሃል ወሰን በማድረግ ከጊልያድ አንስቶ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ እንዲሁም የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው ሸለቆ ማለትም እስከ ያቦቅ ድረስ ሰጠኋቸው፤ 17 እንዲሁም ከኪኔሬት አንስቶ በአረባ እስከሚገኘው ባሕር ይኸውም በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በጲስጋ ሸንተረር ግርጌ እስከሚገኘው እስከ ጨው ባሕር* ድረስ ያለውን አረባን፣ ዮርዳኖስንና ወሰኑን ሰጠኋቸው።+
18 “ከዚያም ይህን ትእዛዝ ሰጠኋችሁ፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ ይህችን ምድር ርስት አድርጋችሁ እንድትወርሷት ሰጥቷችኋል። ብርቱ የሆናችሁት ወንዶች ሁሉ የጦር መሣሪያችሁን ታጥቃችሁ በወንድሞቻችሁ በእስራኤላውያን ፊት ትሻገራላችሁ።+ 19 ሚስቶቻችሁ፣ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ (መቼም ብዙ ከብቶች እንዳሏችሁ አውቃለሁ) በሰጠኋችሁ ከተሞች ውስጥ ይቀራሉ፤ 20 ይህም ይሖዋ ልክ ለእናንተ እንዳደረገላችሁ ሁሉ ለወንድሞቻችሁም እረፍት እስኪሰጣቸው እንዲሁም አምላካችሁ ይሖዋ ከዮርዳኖስ ማዶ የሚሰጣቸውን ምድር ርስት አድርገው እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚያ በኋላ እያንዳንዳችሁ ወደሰጠኋችሁ ወደየራሳችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።’+
21 “በዚያን ጊዜ ለኢያሱ ይህን ትእዛዝ ሰጠሁት፦+ ‘አምላክህ ይሖዋ በእነዚህ ሁለት ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ በገዛ ዓይንህ አይተሃል። ይሖዋ አልፈሃቸው በምትሄደው መንግሥታት ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋል።+ 22 ስለ እናንተ የሚዋጋው+ አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው።’
23 “እኔም በዚያን ጊዜ ይሖዋን እንዲህ በማለት ተማጸንኩት፦ 24 ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህ ታላቅነትህንና ብርቱ ክንድህን እንዲያይ አድርገሃል፤+ አንተ እንደምታደርጋቸው ያሉ ታላላቅ ነገሮችን መፈጸም የሚችለው በሰማይም ሆነ በምድር ያለ የትኛው አምላክ ነው?+ 25 እባክህ ከዮርዳኖስ ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር፣ አዎ ውብ የሆነችውን ይህችን ተራራማ አካባቢና ሊባኖስን ተሻግሬ እንዳይ ፍቀድልኝ።’+ 26 ይሖዋ ግን በእናንተ የተነሳ በጣም ተቆጥቶኝ ስለነበር+ አልሰማኝም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘በቃ! ዳግመኛ ስለዚህ ጉዳይ እንዳታነሳብኝ። 27 ይህን ዮርዳኖስን ስለማትሻገር ወደ ጲስጋ አናት ውጣና+ ዓይንህን አቅንተህ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ ተመልከት።+ 28 በዚህ ሕዝብ ፊት የሚሻገረውም+ ሆነ አንተ ያየሃትን ምድር እንዲወርሱ የሚያደርገው ኢያሱ ስለሆነ እሱን መሪ አድርገህ ሹመው፤+ አደፋፍረው፤ አበረታታውም።’ 29 ይህ ሁሉ የሆነው በቤትጰኦር+ ፊት ለፊት በሚገኘው ሸለቆ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ ነው።
4 “አሁንም እስራኤል ሆይ፣ በሕይወት እንድትኖሩና+ የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ የሚሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፣ ትጠብቋቸው ዘንድ የማስተምራችሁን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች አዳምጡ። 2 እኔ የማዛችሁን የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት ጠብቁ፤ በምሰጣችሁ ትእዛዝ ላይ ምንም ነገር አትጨምሩ፤ ከዚያም ላይ ምንም አትቀንሱ።+
3 “ይሖዋ ከፌጎር ባአል ጋር በተያያዘ ምን እንዳደረገ በገዛ ዓይናችሁ አይታችኋል፤ አምላክህ ይሖዋ የፌጎርን ባአል የተከተለውን እያንዳንዱን ሰው ከመካከልህ አጥፍቶታል።+ 4 አምላካችሁን ይሖዋን የሙጥኝ ያላችሁት እናንተ ሁላችሁ ግን ይኸው ዛሬም በሕይወት አላችሁ። 5 እኔም አምላኬ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ሥርዓቶችንና ድንጋጌዎችን+ ያስተማርኳችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ እንድትጠብቋቸው ነው። 6 እነዚህንም በጥንቃቄ ጠብቋቸው፤+ ፈጽሟቸውም፤ እንዲህ ብታደርጉ ስለ እነዚህ ሥርዓቶች ሁሉ በሚሰሙ ሕዝቦች ፊት እንደ ጥበበኞችና+ እንደ አስተዋዮች+ ትቆጠራላችሁ፤ እነሱም ‘ይህ ታላቅ ብሔር በእርግጥም ጥበበኛና አስተዋይ ሕዝብ ነው’+ ይላሉ። 7 በምንጠራው ጊዜ ሁሉ ለእኛ ቅርብ እንደሆነው እንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ፣ ለእሱ ቅርብ የሆኑ አማልክት ያሉት ታላቅ ብሔር የትኛው ነው?+ 8 ዛሬ በፊታችሁ እንዳስቀመጥኩት እንደዚህ ሕግ ያለ የጽድቅ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ያሉት የትኛው ታላቅ ብሔር ነው?+
9 “ዓይኖቻችሁ ያዩአቸውን ነገሮች እንዳትረሱና በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ከልባችሁ እንዳይጠፉ ተጠንቀቁ፤ ራሳችሁንም ጠብቁ።* እነዚህንም ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ንገሯቸው።+ 10 በኮሬብ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት በቆማችሁበት ቀን ይሖዋ ‘በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት+ ይማሩና ልጆቻቸውንም ያስተምሩ+ ዘንድ ቃሌን እንዲሰሙ+ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ’ ብሎኝ ነበር።
11 “በመሆኑም እናንተ መጥታችሁ በተራራው ግርጌ ቆማችሁ፤ ተራራውም እስከ ሰማያት ድረስ* እየነደደ ነበር፤ ጨለማ፣ ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ሆኖ ነበር።+ 12 ይሖዋም ከእሳቱ ውስጥ ያነጋግራችሁ ጀመር።+ እናንተም ድምፅ ከመስማት በስተቀር መልክ አላያችሁም፤+ የሰማችሁት ድምፅ ብቻ ነበር።+ 13 እሱም እንድትጠብቁት ያዘዛችሁን ቃል ኪዳኑን ይኸውም አሥርቱን ትእዛዛት* ገለጸላችሁ።+ ከዚያም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው።+ 14 በዚያን ጊዜ ይሖዋ፣ ገብታችሁ በምትወርሷት ምድር የምትፈጽሟቸውን ሥርዓቶችና ደንቦች እንዳስተምራችሁ አዘዘኝ።
15 “በመሆኑም ይሖዋ በኮሬብ በእሳቱ መካከል ሆኖ ባነጋገራችሁ ቀን ምንም መልክ ስላላያችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤* 16 ይኸውም ምግባረ ብልሹ በመሆን በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን የትኛውንም ዓይነት ምስል፣ የወንድ ወይም የሴት ምስል፣+ 17 በምድር ላይ ያለን የማንኛውንም እንስሳ ምስል ወይም በሰማይ ላይ የሚበርን የማንኛውንም ወፍ ምስል፣+ 18 መሬት ለመሬት የሚሄድን የማንኛውንም ነገር ምስል አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ያለን የማንኛውንም ዓሣ ምስል ለራሳችሁ እንዳትሠሩ ነው።+ 19 እንዲሁም ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ይኸውም የሰማይን ሠራዊት በሙሉ በምታይበት ጊዜ ተታለህ እንዳትሰግድላቸውና እንዳታገለግላቸው።+ እነዚህ አምላክህ ይሖዋ ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ የሰጣቸው ናቸው። 20 እናንተን ግን ልክ እንደ ዛሬው ሁሉ ይሖዋ የእሱ የግል ንብረት*+ እንድትሆኑ የብረት ማቅለጫ ምድጃ ከሆነችው ከግብፅ አውጥቶ አመጣችሁ።
21 “ይሖዋ በእናንተ የተነሳ እኔን ተቆጣኝ፤+ ዮርዳኖስን እንደማልሻገርም ሆነ አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንደማልገባ ማለ።+ 22 እንግዲህ እኔ የምሞተው በዚህ አገር ነው፤ ዮርዳኖስን አልሻገርም፤+ እናንተ ግን ተሻግራችሁ ይህችን መልካም ምድር ትወርሳላችሁ። 23 አምላካችሁ ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ+ እንዲሁም አምላካችሁ ይሖዋ የከለከላችሁን የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስል ለራሳችሁ እንዳትሠሩ ተጠንቀቁ።+ 24 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የሚባላ እሳት፣+ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው።+
25 “ልጆችና የልጅ ልጆች ስታፈሩ፣ በምድሪቱም ላይ ረጅም ዘመን ስትኖሩ፣ የጥፋት ጎዳና ወደመከተል ዞር ብትሉና የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስል+ ብትሠሩ እንዲሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ክፉ ነገር በመፈጸም እሱን ብታስቆጡት+ 26 ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትወርሷት ምድር ያለጥርጥር ወዲያውኑ እንደምትደመሰሱ በዚህ ቀን ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምሥክር አድርጌ እጠራባችኋለሁ። በምድሪቱ ላይ ረጅም ዘመን ከመኖር ይልቅ ሙሉ በሙሉ ትደመሰሳላችሁ።+ 27 ይሖዋም በሕዝቦች መካከል ይበትናችኋል፤+ ይሖዋ በሚበትናችሁ ብሔራትም መካከል ጥቂቶቻችሁ ብቻ ትተርፋላችሁ።+ 28 እዚያም ማየትም ሆነ መስማት፣ መብላትም ሆነ ማሽተት የማይችሉ በሰው እጅ የተሠሩ የእንጨትና የድንጋይ አማልክትን ታገለግላላችሁ።+
29 “እዚያ ሆናችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ብትፈልጉት፣ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ብትሹት በእርግጥ ታገኙታላችሁ።+ 30 ከጊዜ በኋላ ከባድ ጭንቀት ውስጥ ስትገባና እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአንተ ላይ ሲደርሱ ያኔ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ትመለሳለህ፤ ድምፁንም ትሰማለህ።+ 31 ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መሐሪ አምላክ ነው።+ አይተውህም፣ አያጠፋህም ወይም ለአባቶችህ በመሐላ ያጸናላቸውን ቃል ኪዳን አይረሳም።+
32 “እንግዲህ ከአንተ ዘመን በፊት ስለነበሩት ስለ ቀደሙት ጊዜያት ይኸውም አምላክ ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ቀን አንስቶ ስላለው ዘመን ጠይቅ፤ ከአንዱ የሰማይ ጥግ እስከ ሌላኛው የሰማይ ጥግ ድረስ እስቲ መርምር። እንዲህ ያለ እጅግ ታላቅ ነገር ተደርጎ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ተሰምቶ ያውቃል?+ 33 ልክ እንደ አንተ፣ አምላክ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሰማና በሕይወት የኖረ ሌላ ሕዝብ አለ?+ 34 ወይስ አምላካችሁ ይሖዋ የገዛ ዓይኖቻችሁ እያዩ ለእናንተ በግብፅ እንዳደረገው ሁሉ በፍርድ እርምጃዎች፣* ድንቅ በሆኑ ምልክቶች፣ በተአምራት፣+ በጦርነት፣+ በብርቱ እጅ፣+ በተዘረጋ ክንድና አስፈሪ በሆኑ ሥራዎች+ ከሌላ ብሔር መካከል ለራሱ ብሔር ለመውሰድ ሞክሯል? 35 እውነተኛው አምላክ፣ ይሖዋ መሆኑን ታውቅ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እንድታይ ተደርገሃል፤+ ከእሱ ሌላ ማንም የለም።+ 36 አንተን ለማረም ከሰማያት ድምፁን እንድትሰማ አደረገህ፤ በምድርም ላይ የእሱን ታላቅ እሳት እንድታይ አደረገህ፤ ድምፁንም ከእሳቱ ውስጥ ሰማህ።+
37 “እሱ አባቶችህን ስለወደደና ከእነሱ በኋላ የሚመጣውን ዘራቸውን ስለመረጠ+ ከአንተ ጋር በመሆን በታላቅ ኃይሉ ከግብፅ አወጣህ። 38 እንዲሁም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ወደ ምድራቸው ሊያስገባህና ምድራቸውን ርስት አድርጎ ሊሰጥህ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ኃያል የሆኑትን ብሔራት ከፊትህ አባረራቸው።+ 39 እንግዲህ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር እውነተኛው አምላክ፣ ይሖዋ እንደሆነ ዛሬ እወቅ፤ እንዲሁም ልብ በል።+ ሌላ ማንም የለም።+ 40 ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁና አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ለረጅም ዘመን እንድትኖር እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ሥርዓትና ትእዛዛት ጠብቅ።”+
41 በዚያን ጊዜ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ሦስት ከተሞችን ለየ።+ 42 ነፍስ ያጠፋ ማንኛውም ግለሰብ ባልንጀራውን የገደለው ሆን ብሎ ካልሆነና የቆየ ጥላቻ ካልነበረው+ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ በዚያ መኖር ይችላል።+ 43 ከተሞቹም ለሮቤላውያን በአምባው ላይ ባለው ምድረ በዳ የምትገኘው ቤጼር፣+ ለጋዳውያን በጊልያድ የምትገኘው ራሞት+ እንዲሁም ለምናሴያውያን በባሳን+ ያለችው ጎላን+ ናቸው።
44 ሙሴ በእስራኤል ሕዝብ ፊት ያስቀመጠው ሕግ+ ይህ ነው። 45 እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ሙሴ የሰጣቸው ማሳሰቢያዎች፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤+ 46 ይህን የነገራቸው በዮርዳኖስ ክልል ከቤትጰኦር+ ባሻገር በሚገኘው ሸለቆ ይኸውም ሙሴና እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ድል ባደረጉት በሃሽቦን+ ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ምድር ነበር።+ 47 እነሱም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው ክልል የነበሩትን የሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ምድር ማለትም የሲሖንን ምድርና የባሳንን ንጉሥ የኦግን+ ምድር ወረሱ፤ 48 ይህም ምድር በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ከሚገኘው ከአሮዔር+ አንስቶ እስከ ሲዎን ተራራ ይኸውም እስከ ሄርሞን+ ድረስ ያለውን አካባቢ ይሸፍናል፤ 49 እንዲሁም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን የአረባን ምድርና በጲስጋ+ ሸንተረር ግርጌ እስከሚገኘው እስከ አረባ ባሕር* ድረስ ያለውን አካባቢ ይጨምራል።
5 ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን በሙሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እስራኤላውያን፣ በዛሬው ዕለት የምነግራችሁን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ስሙ፤ እወቋቸው፤ በጥንቃቄም ፈጽሟቸው። 2 አምላካችን ይሖዋ በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ገብቷል።+ 3 ይሖዋ ይህን ቃል ኪዳን የገባው ከአባቶቻችን ጋር ሳይሆን ዛሬ በሕይወት እዚህ ካለነው ከእኛ ከሁላችን ጋር ነው። 4 ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ከእናንተ ጋር ፊት ለፊት ተነጋገረ።+ 5 በዚያ ወቅት እኔ የይሖዋን ቃል ለእናንተ ለመንገር በይሖዋና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር፤+ ምክንያቱም እናንተ ከእሳቱ የተነሳ ፈርታችሁ ወደ ተራራው አልወጣችሁም።+ እሱም እንዲህ አለ፦
6 “‘ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ።+ 7 ከእኔ በቀር* ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።+
8 “‘በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸ ቅርጽም+ ሆነ የተሠራ ምስል ለራስህ አታብጅ። 9 ለእነሱ አትስገድ፤ አታገልግላቸውም፤+ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና+ በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤+ 10 ሆኖም ለሚወዱኝና ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ታማኝ ፍቅር* የማሳይ አምላክ ነኝ።
11 “‘የአምላክህን የይሖዋን ስም በከንቱ አታንሳ፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ስሙን በከንቱ የሚያነሳውን ሳይቀጣ አይተወውም።+
12 “‘አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ቅዱስ አድርገህ ትጠብቀው ዘንድ የሰንበትን ቀን አክብር።+ 13 ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀን ትሠራለህ፤+ 14 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው።+ በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ በሬህም ሆነ አህያህ ወይም ማንኛውም የቤት እንስሳህ አሊያም በከተሞችህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው+ ምንም ሥራ አትሥሩ፤+ ይህም አንተ እንደምታርፈው ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ እንዲያርፉ ነው።+ 15 አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ በብርቱ እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ እንዳወጣህ አስታውስ።+ አምላክህ ይሖዋ የሰንበትን ቀን እንድታከብር ያዘዘህ ለዚህ ነው።
16 “‘አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ+ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።+
17 “‘አትግደል።+
18 “‘አታመንዝር።+
19 “‘አትስረቅ።+
20 “‘በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመሥክር።+
21 “‘የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ።+ የባልንጀራህን ቤት፣ እርሻውን፣ ወንድ ባሪያውን፣ ሴት ባሪያውን፣ በሬውን፣ አህያውን ወይም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።’+
22 “ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳቱ መካከል በደመናውና በድቅድቅ ጨለማው+ ውስጥ ሆኖ እነዚህን ትእዛዛት* ከፍ ባለ ድምፅ ለመላው ጉባኤያችሁ ተናገረ፤ ከእነዚህም ሌላ ምንም አልጨመረም፤ ከዚያም እነዚህን በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጽፎ ሰጠኝ።+
23 “ይሁን እንጂ ተራራው በእሳት እየነደደ ሳለ+ ከጨለማው ውስጥ ድምፅ ሲወጣ ስትሰሙ የነገድ መሪዎቻችሁና ሽማግሌዎቹ በሙሉ ወደ እኔ መጡ። 24 ከዚያም እንዲህ አላችሁ፦ ‘ይኸው አምላካችን ይሖዋ ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፤ ድምፁንም ከእሳቱ ውስጥ ሰምተናል።+ አምላክ ከሰው ጋር መነጋገር እንደሚችልና ያም ሰው በሕይወት ሊኖር እንደሚችል በዛሬው ቀን አይተናል።+ 25 ታዲያ አሁን ለምን እንሙት? ምክንያቱም ይህ ታላቅ እሳት ሊበላን ይችላል። የአምላካችንን የይሖዋን ድምፅ መስማት ከቀጠልን እንደምንሞት የተረጋገጠ ነው። 26 ለመሆኑ ከሥጋ* ሁሉ መካከል ልክ እኛ እንደሰማነው ሕያው የሆነው አምላክ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር ሰምቶ በሕይወት የኖረ ማን አለ? 27 አንተው ራስህ ቀርበህ አምላካችን ይሖዋ የሚናገረውን ሁሉ ስማ፤ ከዚያም አምላካችን ይሖዋ የነገረህን ሁሉ ትነግረናለህ፤ እኛም እንሰማለን፤ ደግሞም የተባልነውን እናደርጋለን።’+
28 “ከዚያም ይሖዋ ያላችሁኝን ነገር ሰማ፤ ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ ‘ይህ ሕዝብ ምን እንዳለህ ሰምቻለሁ። የተናገሩት ነገር ሁሉ መልካም ነው።+ 29 ምንጊዜም እኔን የሚፈራና+ ትእዛዛቴን ሁሉ የሚጠብቅ ልብ+ ቢኖራቸው ምናለ፤ እንዲህ ቢሆን ለእነሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም ይሆንላቸው ነበር!+ 30 ሂድና “ወደየድንኳናችሁ ተመለሱ” በላቸው። 31 አንተ ግን እዚሁ እኔ ጋ ቆይ፤ እኔም ርስት አድርገው እንዲወርሷት በምሰጣቸው ምድር ውስጥ ይጠብቋቸው ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች በሙሉ እነግርሃለሁ።’ 32 እንግዲህ አምላካችሁ ይሖዋ ያዘዛችሁን በጥንቃቄ ፈጽሙ።+ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበሉ።+ 33 ርስት አድርጋችሁ በምትወርሷት ምድር በሕይወት እንድትኖሩ፣ እንድትበለጽጉና ዕድሜያችሁ እንዲረዝም+ አምላካችሁ ይሖዋ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።+
6 “አምላካችሁ ይሖዋ ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ ትጠብቋቸው ዘንድ እንዳስተምራችሁ የሰጠኝ ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤ 2 ይህም አንተ፣ ልጅህና የልጅ ልጅህ+ ዕድሜያችሁ ይረዝም ዘንድ በሕይወታችሁ ዘመን ሁሉ አምላካችሁን ይሖዋን እንድትፈሩ እንዲሁም እኔ የማዛችሁን የእሱን ደንቦችና ትእዛዛት ሁሉ እንድትጠብቁ ነው።+ 3 እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ ይሖዋ በገባልህ ቃል መሠረት ወተትና ማር በምታፈሰው ምድር እንድትበለጽግና እጅግ እንድትበዛ እነዚህን በጥንቃቄ ጠብቅ።
4 “እስራኤል ሆይ ስማ፣ አምላካችን ይሖዋ አንድ ይሖዋ ነው።+ 5 አንተም አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና*+ በሙሉ ኃይልህ ውደድ።+ 6 እኔ ዛሬ የማዝህን እነዚህን ትእዛዛት በልብህ ያዝ፤ 7 በልጆችህም ውስጥ ቅረጻቸው፤*+ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድ ላይ ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሳ ስለ እነሱ ተናገር።+ 8 በእጅህም ላይ እንደ ማስታወሻ እሰራቸው፤ በግንባርህም ላይ* እንደታሰረ ነገር ይሁኑ።+ 9 በቤትህ መቃኖችና በግቢህ በሮች ላይ ጻፋቸው።
10 “አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር+ ሲያስገባህና በዚያም አንተ ያልገነባሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞች፣+ 11 አንተ ባልደከምክባቸው የተለያዩ መልካም ነገሮች የተሞሉ ቤቶችን፣ አንተ ያልቦረቦርካቸውን የውኃ ማጠራቀሚያዎች እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ስታገኝ፣ በልተህም ስትጠግብ+ 12 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ይሖዋን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።+ 13 ይሖዋ አምላክህን ፍራ፤+ እሱን አገልግል፤+ በስሙም ማል።+ 14 ሌሎች አማልክትን ይኸውም በዙሪያችሁ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን የትኞቹንም አማልክት አትከተሉ፤+ 15 ምክንያቱም በመካከልህ ያለው አምላክህ ይሖዋ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው።+ አለዚያ የአምላክህ የይሖዋ ቁጣ በላይህ ይነድዳል፤+ ከምድርም ገጽ ጠራርጎ ያጠፋሃል።+
16 “በማሳህ እንደተፈታተናችሁት+ አምላካችሁን ይሖዋን አትፈታተኑት።+ 17 አምላካችሁ ይሖዋ እንድትጠብቋቸው ያዘዛችሁን ትእዛዛት እንዲሁም ማሳሰቢያዎቹንና ሥርዓቶቹን በጥንቃቄ ጠብቁ። 18 እንድትበለጽግና ይሖዋ ለአባቶችህ የማለላቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ እንድትወርስ በይሖዋ ፊት ትክክልና መልካም የሆነውን አድርግ፤+ 19 ይሖዋ በገባው ቃል መሠረት ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ አባረህ አስወጣ።+
20 “ወደፊት ልጅህ ‘አምላካችን ይሖዋ የሰጣችሁ ማሳሰቢያዎች፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ትርጉም ምንድን ነው?’ ብሎ ሲጠይቅህ 21 እንዲህ ትለዋለህ፦ ‘እኛ በግብፅ የፈርዖን ባሪያዎች ሆነን ነበር፤ ይሖዋ ግን በብርቱ ክንድ ከግብፅ አወጣን። 22 ይሖዋም በግብፅ፣ በፈርዖንና በቤተሰቡ ሁሉ ላይ+ ታላላቅና አጥፊ የሆኑ ድንቅ ምልክቶችንና ተአምራትን+ ዓይናችን እያየ ፈጸመ። 23 እኛንም ለአባቶቻችን የማለላቸውን ምድር ሊሰጠን ከዚያ አውጥቶ ወደዚህ አመጣን።+ 24 ከዚያም ይሖዋ ምንጊዜም መልካም ይሆንልን ዘንድ እነዚህን ሥርዓቶች ሁሉ እንድንፈጽምና አምላካችንን ይሖዋን እንድንፈራ አዘዘን፤+ ይህም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ በሕይወት እንድንኖር ነው።+ 25 አምላካችንን ይሖዋን በመታዘዝ* ልክ እሱ በሰጠን መመሪያ መሠረት እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ በጥንቃቄ ብንፈጽም ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።’+
7 “አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ ወደምትወርሳት ምድር ሲያመጣህ+ ብዙ ሕዝብ ያላቸውን ብሔራት ይኸውም ከአንተ ይልቅ ብዙ ሕዝብ ያላቸውንና ኃያላን የሆኑትን ሰባት ብሔራት+ ማለትም ሂታውያንን፣ ገርጌሻውያንን፣ አሞራውያንን፣+ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንን እና ኢያቡሳውያንን+ ከፊትህ ያስወግድልሃል።+ 2 አምላክህ ይሖዋ እነሱን አሳልፎ ይሰጥሃል፤ ድልም ታደርጋቸዋለህ።+ አንተም ሙሉ በሙሉ ደምስሳቸው።+ ከእነሱ ጋር ምንም ዓይነት ቃል ኪዳን አትጋባ፤ አትራራላቸውም።+ 3 ከእነሱ ጋር በጋብቻ አትዛመድ። ሴቶች ልጆችህን ለወንዶች ልጆቻቸው አትዳር ወይም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆችህ አትውሰድ።+ 4 ምክንያቱም ልጆችህ ሌሎች አማልክትን ያገለግሉ ዘንድ እኔን ከመከተል ዞር እንዲሉ ያደርጓቸዋል፤+ ከዚያም የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ አንተንም ወዲያው ያጠፋሃል።+
5 “ከዚህ ይልቅ እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ሰባብሩ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ቆራርጡ፤+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።+ 6 ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ አምላክህ ይሖዋ በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ* እንድትሆን መርጦሃል።+
7 “ይሖዋ እናንተን የወደዳችሁና የመረጣችሁ+ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ይልቅ ቁጥራችሁ ስለበዛ አይደለም፤ ቁጥራችሁማ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ አነስተኛ ነበር።+ 8 ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እናንተን ከባርነት ቤት ይኸውም ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ ይታደጋችሁ ዘንድ ይሖዋ በብርቱ እጅ ያወጣችሁ+ ስለወደዳችሁና ለአባቶቻችሁ የማለላቸውን መሐላ ስለጠበቀ ነው።+ 9 አንተም አምላክህ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ፣ ታማኝ አምላክ እንዲሁም ለሚወዱትና ትእዛዛቱን ለሚጠብቁ ሁሉ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር የሚያሳይ መሆኑን በሚገባ ታውቃለህ።+ 10 የሚጠሉትን ግን በማጥፋት በግልጽ ይበቀላቸዋል።+ በሚጠሉት ላይ እርምጃ ለመውሰድ አይዘገይም፤ በግልጽ ይበቀላቸዋል። 11 ስለዚህ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች በማክበር በጥንቃቄ ጠብቃቸው።
12 “እነዚህን ድንጋጌዎች ብትሰሙና ብትጠብቋቸው እንዲሁም ብትፈጽሟቸው አምላካችሁ ይሖዋ ለአባቶቻችሁ በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳንና ታማኝ ፍቅር ይጠብቃል። 13 ይወድሃል፣ ይባርክሃል እንዲሁም ያበዛሃል። አዎ፣ ለአንተ ሊሰጥህ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር ላይ የሆድህን ፍሬ፣+ የመሬትህን ምርት፣ እህልህን፣ አዲሱን የወይን ጠጅህን፣ ዘይትህን፣+ የከብቶችህን ጥጆችና የመንጋህን ግልገሎች ይባርክልሃል።+ 14 አንተም ከሕዝቦች ሁሉ ይበልጥ የተባረክ ትሆናለህ፤+ በመካከልህ ልጅ የሌለው ወንድ ወይም ሴት አይገኝም፤ እንስሶችህም ግልገል የሌላቸው አይሆኑም።+ 15 ይሖዋ በሽታን ሁሉ ያስወግድልሃል፤ በግብፅ ሳለህ ታውቃቸው ከነበሩት አሰቃቂ በሽታዎች አንዱንም በአንተ ላይ አያመጣም።+ ከዚህ ይልቅ በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል። 16 አምላክህ ይሖዋ አሳልፎ የሚሰጥህን ሕዝቦች ሁሉ ታጠፋለህ።+ አትዘንላቸው፤*+ አማልክታቸውንም አታገልግል፤+ ምክንያቱም እንዲህ ማድረግህ ወጥመድ ይሆንብሃል።+
17 “ምናልባት በልብህ ‘እነዚህ ብሔራት እኮ ከእኛ ይልቅ ብዙ ናቸው። ታዲያ እንዴት ላባርራቸው እችላለሁ?’ ትል ይሆናል፤+ 18 ሆኖም አትፍራቸው።+ አምላክህ ይሖዋ በፈርዖንና በግብፅ ሁሉ ላይ ያደረገውን አስታውስ፤+ 19 ዓይኖችህ ያዩአቸውን ታላላቅ የፍርድ እርምጃዎች* እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ አንተን ለማውጣት የተጠቀመባቸውን ድንቅ ምልክቶች፣ ተአምራት፣+ ብርቱ እጅና የተዘረጋ ክንድ አስብ።+ አምላክህ ይሖዋ በምትፈራቸው ሕዝቦች ሁሉ ላይ የሚያደርገው ይህንኑ ነው።+ 20 አምላክህ ይሖዋ በሕይወት የተረፉትና ከፊትህ የተሸሸጉት እስኪጠፉ ድረስ ጭንቀት* ይለቅባቸዋል።+ 21 ታላቅና የሚያስፈራ አምላክ+ የሆነው አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ስለሆነ+ በእነሱ የተነሳ አትሸበር።
22 “አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት በጥቂት በጥቂቱ ከፊትህ ያባርራቸዋል።+ የዱር አራዊት እንዳይበዙብህ በአንድ ጊዜ ጠራርገህ እንድታጠፋቸው አይፈቀድልህም። 23 አምላክህ ይሖዋ እነሱን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ እስኪጠፉም ድረስ ሙሉ በሙሉ ድል ታደርጋቸዋለህ።+ 24 እሱም ነገሥታታቸውን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤+ አንተም ስማቸውን ከሰማይ በታች ትደመስሳለህ።+ ድምጥማጣቸውን እስክታጠፋ+ ድረስ ማንም አይቋቋምህም።+ 25 የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች በእሳት አቃጥሉ።+ ወጥመድ ሊሆንብህ ስለሚችል በእነሱ ላይ ያለውን ብርም ሆነ ወርቅ አትመኝ ወይም ለራስህ አትውሰድ፤+ ምክንያቱም ይህ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነገር ነው።+ 26 አስጸያፊ ነገር ወደ ቤትህ በማምጣት ልክ እንደ እሱ ራስህን ለጥፋት አትዳርግ። ለጥፋት የተለየ ነገር ስለሆነ ፈጽመህ ጥላው፤ ሙሉ በሙሉም ተጸየፈው።
8 “በሕይወት እንድትኖሩና+ እንድትበዙ እንዲሁም ይሖዋ ለአባቶቻችሁ የማለላቸውን ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ ዛሬ የማዛችሁን እያንዳንዱን ትእዛዝ በጥንቃቄ ጠብቁ።+ 2 አምላክህ ይሖዋ በልብህ ምን እንዳለ+ ይኸውም ትእዛዛቱን ትጠብቅ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ ይፈትንህና ትሑት ያደርግህ ዘንድ+ በእነዚህ 40 ዓመታት በምድረ በዳ እንድትጓዝበት ያደረገህን ረጅሙን መንገድ አስታውስ።+ 3 ትሑት እንድትሆን አደረገህ፤ ካስራበህም+ በኋላ አንተ የማታውቀውን፣ አባቶችህም የማያውቁትን መና መገበህ፤+ ይህን ያደረገው፣ ሰው ከይሖዋ አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ ሊኖር እንደማይችል ሊያሳውቅህ ነው።+ 4 በእነዚህ 40 ዓመታት፣ የለበስከው ልብስ አላለቀም፤ እግርህም አላበጠም።+ 5 አንድ ሰው ለልጁ እርማት እንደሚሰጥ ሁሉ አምላክህ ይሖዋም እርማት ይሰጥህ+ እንደነበር ልብህ በሚገባ ያውቃል።
6 “እንግዲህ አንተ በመንገዶቹ በመሄድና እሱን በመፍራት የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ጠብቅ። 7 ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መልካም ወደሆነች ምድር ሊያስገባህ ነው፤+ ይህች ምድር ጅረቶች* ያሏት፣ በሸለቋማ ሜዳዋና በተራራማ አካባቢዋ ምንጮች የሚፈልቁባትና ውኃዎች የሚንዶለዶሉባት፣ 8 ስንዴ፣ ገብስ፣ ወይን፣ በለስና ሮማን+ የሚበቅልባት፣ የወይራ ዘይትና ማር የሚገኝባት፣+ 9 የምግብ እጥረት የሌለባት፣ ምንም ነገር የማታጣባት፣ ብረት ያለባቸው ድንጋዮች የሚገኙባት እንዲሁም ከተራሮቿ መዳብ ቆፍረህ የምታወጣባት ምድር ናት።
10 “በልተህ በምትጠግብበት ጊዜ ስለሰጠህ ስለ መልካሚቱ ምድር አምላክህን ይሖዋን አመስግነው።+ 11 እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛት፣ ድንጋጌዎችና ደንቦች ችላ በማለት አምላክህን ይሖዋን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ። 12 በልተህ ስትጠግብ፣ ጥሩ ጥሩ ቤቶችን ሠርተህ በዚያ መኖር ስትጀምር፣+ 13 ከብትህና መንጋህ ሲበዛ፣ ብርህና ወርቅህ ሲበራከት እንዲሁም የአንተ የሆነው ሁሉ እየበዛ ሲሄድ 14 ልብህ እንዳይታበይና+ ከግብፅ ምድር ይኸውም ከባርነት ቤት ያወጣህን አምላክህን ይሖዋን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ፤+ 15 መርዛማ እባቦችና ጊንጦች በሞሉበት እንዲሁም ውኃ የተጠማ ደረቅ ምድር ባለበት በዚያ ጭልጥ ያለና የሚያስፈራ ምድረ በዳ+ አቋርጠህ እንድታልፍ ያደረገህን አምላክህን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ። እሱ ከጠንካራ ዓለት* ውኃ አፍልቆልሃል፤+ 16 እንዲሁም ወደፊት መልካም እንዲሆንልህ አንተን ትሑት ለማድረግና ለመፈተን ሲል+ አባቶችህ የማያውቁትን መና በምድረ በዳ መግቦሃል።+ 17 በልብህም ‘ይህን ሀብት ያፈራሁት በራሴ ኃይልና በእጄ ብርታት ነው’+ ብለህ ብታስብ 18 ሀብት እንድታፈራ ኃይል የሰጠህ አምላክህ ይሖዋ መሆኑን አስታውስ፤+ ይህን ያደረገው ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ለአባቶችህ በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ነው።+
19 “አምላክህን ይሖዋን ብትረሳና ሌሎች አማልክትን ብትከተል እንዲሁም እነሱን ብታገለግልና ለእነሱ ብትሰግድ፣ በእርግጥ እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ እመሠክርባችኋለሁ።+ 20 የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ስላልሰማችሁ ይሖዋ ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው ብሔራት እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።+
9 “እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ እንግዲህ ዛሬ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ኃያል የሆኑ ብሔራትን+ እንዲሁም ታላላቅና እስከ ሰማያት የሚደርስ ቅጥር ያላቸውን ከተሞች+ በማስለቀቅ ወደ ምድሪቱ ለመግባት ዮርዳኖስን ልትሻገር ነው፤+ 2 ‘የኤናቅን ልጆች ማን ሊቋቋማቸው ይችላል?’ ሲባልላቸው የሰማኸውን፣ አንተ ራስህ የምታውቃቸውን ብርቱና ቁመተ ረጃጅም ሕዝብ የሆኑትን የኤናቅን ልጆችም+ ልታስለቅቅ ነው። 3 ስለሆነም አምላክህ ይሖዋ ዛሬ ከአንተ ቀድሞ እንደሚሻገር እወቅ።+ እሱ የሚባላ እሳት ነው፤+ ደግሞም ያጠፋቸዋል። ልክ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት በፍጥነት ታባርራቸውና* ታጠፋቸው ዘንድ ዓይንህ እያየ ድል ያደርጋቸዋል።+
4 “አምላክህ ይሖዋ እነሱን ከፊትህ በሚያባርራቸው ጊዜ በልብህ ‘ይሖዋ ይህችን ምድር እንድወርስ ወደዚህ ያመጣኝ እኮ በራሴ ጽድቅ ነው’ አትበል፤+ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት ከፊትህ የሚያባርራቸው በራሳቸው ክፋት የተነሳ ነው።+ 5 የእነሱን ምድር ገብተህ የምትወርሰው ከጽድቅህ ወይም ከልብህ ቅንነት የተነሳ አይደለም። ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት ከፊትህ የሚያባርራቸው ከራሳቸው ክፋት የተነሳ ነው፤+ እንዲሁም ይሖዋ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣+ ለይስሐቅና+ ለያዕቆብ+ የማለላቸውን ቃል ለመፈጸም ሲል ነው። 6 ስለዚህ አምላክህ ይሖዋ ይህችን መልካም ምድር እንድትወርሳት የሚሰጥህ ከጽድቅህ የተነሳ እንዳልሆነ እወቅ፤ ምክንያቱም አንተ ግትር* ሕዝብ ነህ።+
7 “በምድረ በዳ አምላክህን ይሖዋን እንዴት እንዳስቆጣኸው+ አስታውስ፤ ፈጽሞም አትርሳ። ከግብፅ ምድር ከወጣችሁበት ጊዜ አንስቶ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ በይሖዋ ላይ ዓምፃችኋል።+ 8 በኮሬብም እንኳ ይሖዋን አስቆጥታችሁት ነበር፤ ይሖዋም በእናንተ ላይ እጅግ ከመቆጣቱ የተነሳ እናንተን ለማጥፋት አስቦ ነበር።+ 9 እኔም የድንጋይ ጽላቶቹን+ ይኸውም ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን የተጻፈባቸውን ጽላቶች+ ለመቀበል ወደ ተራራው በወጣሁ ጊዜ እህል ሳልበላና ውኃ ሳልጠጣ በተራራው ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆይቼ ነበር።+ 10 ከዚያም ይሖዋ በአምላክ ጣት የተጻፈባቸውን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ፤ በእነሱም ላይ ይሖዋ እዚያ ተሰብስባችሁ በነበረበት ቀን በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የነገራችሁ ነገር ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር።+ 11 ከ40 ቀንና ከ40 ሌሊት በኋላ ይሖዋ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች ይኸውም የቃል ኪዳኑን ጽላቶች ሰጠኝ፤ 12 ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ ‘ተነስ፤ ቶሎ ብለህ ውረድ፤ ምክንያቱም ከግብፅ ያወጣኸው ሕዝብህ የጥፋት ጎዳና እየተከተለ ነው።+ እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ፈጥነው ዞር ብለዋል። ከብረት የተሠራ ምስልም* ለራሳቸው አበጅተዋል።’+ 13 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ፤ በእርግጥም ግትር* ሕዝብ ነው።+ 14 አጠፋቸውና ስማቸውን ከሰማይ በታች እደመስሰው ዘንድ ተወኝ፤ አንተን ግን ከእነሱ ይልቅ ኃያልና ብዙ ሕዝብ ያቀፈ ብሔር አደርግሃለሁ።’+
15 “እኔም ተራራው በእሳት እየተቀጣጠለ+ እያለ ተመልሼ ከተራራው ወረድኩ፤ ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶችም በእጆቼ ይዤ ነበር።+ 16 ከዚያም ስመለከት በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እንደፈጸማችሁ አየሁ! ለራሳችሁም የብረት* ጥጃ ሠርታችሁ ነበር። ይሖዋ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ዞር ብላችሁ ነበር።+ 17 ስለዚህ ሁለቱን ጽላቶች አሽቀንጥሬ በመወርወር ዓይናችሁ እያየ ሰባበርኳቸው።+ 18 ከዚያም እንደ መጀመሪያው ጊዜ ሁሉ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት በይሖዋ ፊት ተደፋሁ። በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በማድረግና እሱን በማስቆጣት በፈጸማችሁት ኃጢአት ሁሉ የተነሳ እህል አልቀመስኩም፤ ውኃም አልጠጣሁም።+ 19 ምክንያቱም ይሖዋ በእናንተ ላይ እጅግ ከመቆጣቱ የተነሳ ሊያጠፋችሁ ስለተዘጋጀ+ ፈርቼ ነበር። ይሁንና ይሖዋ በዚያን ጊዜም ሰማኝ።+
20 “ይሖዋ አሮንን ለማጥፋት እስኪያስብ ድረስ በእሱ ላይ ተቆጥቶ ነበር፤+ ሆኖም በዚያን ጊዜ ስለ አሮንም ምልጃ አቀረብኩ። 21 ከዚያም የኃጢአት ሥራችሁን ይኸውም ጥጃውን+ ወስጄ በእሳት አቃጠልኩት፤ ሰባበርኩት፤ እንደ አቧራ ብናኝ እስኪሆንም ድረስ ፈጨሁት፤ ብናኙንም ከተራራው በሚወርደው ጅረት ውስጥ በተንኩት።+
22 “በተጨማሪም በታበራ፣+ በማሳህ+ እና በቂብሮትሃታባ+ ይሖዋን አስቆጣችሁት። 23 ይሖዋ ከቃዴስበርኔ+ በላካችሁና ‘ውጡ፤ የምሰጣችሁንም ምድር ውረሱ!’ ባላችሁ ጊዜ በአምላካችሁ በይሖዋ ትእዛዝ ላይ በድጋሚ ዓመፃችሁ፤+ በእሱ አልታመናችሁም፤+ እንዲሁም አልታዘዛችሁትም። 24 እኔ እናንተን ካወቅኩበት ጊዜ አንስቶ በይሖዋ ላይ እንዳመፃችሁ ነው።
25 “በመሆኑም 40 ቀንና 40 ሌሊት በይሖዋ ፊት ተደፋሁ፤+ እንዲህ በፊቱ የተደፋሁት፣ ይሖዋ እንደሚያጠፋችሁ ተናግሮ ስለነበር ነው። 26 ከዚያም እንዲህ በማለት ይሖዋን መማጸን ጀመርኩ፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን አታጥፋ። እነሱ በታላቅነትህ የታደግካቸውና በኃያል ክንድህ ከግብፅ ያወጣሃቸው+ የግል ንብረቶችህ*+ ናቸው። 27 አገልጋዮችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስብ።+ የዚህን ሕዝብ ግትርነት፣ ክፋትና ኃጢአት አትመልከት።+ 28 አለዚያ እኛን ባወጣህበት ምድር የሚገኙ ሰዎች “ይሖዋ ቃል ወደገባላቸው ምድር ሊያስገባቸው ስላልቻለና ስለጠላቸው በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው” ሊሉ ይችላሉ።+ 29 እነሱ በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋ ክንድህ ያወጣሃቸው+ ሕዝቦችህና የግል ንብረቶችህ*+ ናቸው።’
10 “በዚያን ጊዜ ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጠርበህ+ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፤ የእንጨት ታቦትም* ለራስህ ሥራ። 2 እኔም በጽላቶቹ ላይ አንተ በሰበርካቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፋለሁ፤ አንተም ጽላቶቹን በታቦቱ ውስጥ አስቀምጣቸው።’ 3 ስለዚህ ከግራር እንጨት ታቦት ሠራሁ፤ ከዚያም እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ የድንጋይ ጽላቶችን ከቀረጽኩ በኋላ ሁለቱን ጽላቶች ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ።+ 4 እሱም በጽላቶቹ ላይ ቀደም ሲል ጽፏቸው የነበሩትን ቃላት+ ይኸውም ተሰብስባችሁ በነበረበት ቀን+ ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ+ ለእናንተ ነግሯችሁ የነበሩትን አሥርቱን ትእዛዛት*+ ጻፈባቸው፤ ይሖዋም ጽላቶቹን ለእኔ ሰጠኝ። 5 እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድኩ፤+ ይሖዋም ባዘዘኝ መሠረት ጽላቶቹን፣ በሠራሁት ታቦት ውስጥ አስቀመጥኳቸው። እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይገኛሉ።
6 “ከዚያም እስራኤላውያን ከበኤሮት ብኔያዕቃን ተነስተው ወደ ሞሴራ ሄዱ። አሮንም በዚያ ቦታ ሞቶ ተቀበረ፤+ ልጁ አልዓዛርም በእሱ ምትክ ካህን ሆኖ ማገልገል ጀመረ።+ 7 ከዚያም ተነስተው ወደ ጉድጎዳ ተጓዙ፤ ከጉድጎዳም ተነስተው ጅረቶች* ወደሚፈስሱባት ምድር ወደ ዮጥባታ+ ሄዱ።
8 “በዚያን ጊዜ ይሖዋ፣ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፣+ ይሖዋን ለማገልገል በፊቱ እንዲቆምና እስከ ዛሬ እንደሚያደርገው በስሙ እንዲባርክ+ የሌዊን ነገድ ለየ።+ 9 ሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ድርሻ ወይም ርስት ያልተሰጠው ለዚህ ነው። አምላክህ ይሖዋ በነገረው መሠረት ይሖዋ ርስቱ ነው።+ 10 እኔም እንደ መጀመሪያው ጊዜ ሁሉ በተራራው ላይ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት ቆየሁ፤+ በዚህ ጊዜም ደግሞ ይሖዋ ሰማኝ።+ ይሖዋ ሊያጠፋህ አልፈለገም። 11 ከዚያም ይሖዋ ‘ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማልኩላቸውን ምድር ገብተው እንዲወርሱ ተነስና ከሕዝቡ ፊት ፊት ሂድ’ አለኝ።+
12 “እንግዲህ እስራኤል ሆይ፣ አምላክህ ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?+ አምላክህን ይሖዋን እንድትፈራው፣+ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄድ፣+ እንድትወደው፣ አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ* እንድታገለግለው+ 13 እንዲሁም ለገዛ ጥቅምህ ስትል እኔ ዛሬ የማዝህን የይሖዋን ትእዛዛትና ደንቦች እንድትጠብቅ ብቻ ነው።+ 14 እነሆ ሰማያት፣ ሌላው ቀርቶ ሰማየ ሰማያት* እንዲሁም ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ የአምላክህ የይሖዋ ናቸው።+ 15 ይሁንና ይሖዋ የቀረበውና ፍቅሩን የገለጸው ለአባቶችህ ብቻ ነው፤ ስለሆነም ይኸው ዛሬ እንደሆነው የእነሱ ዘር የሆናችሁትን እናንተን ከሕዝቦች ሁሉ መካከል መረጠ።+ 16 ስለዚህ ልባችሁን አንጹ፤*+ ከእንግዲህም ወዲህ ግትር መሆናችሁን ተዉ።*+ 17 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የአማልክት አምላክና+ የጌቶች ጌታ እንዲሁም ታላቅ፣ ኃያል፣ የሚያስፈራ፣ ለማንም የማያዳላና+ ጉቦ የማይቀበል አምላክ ነው። 18 አባት ለሌለው* ልጅና ለመበለት ይፈርዳል፤+ እንዲሁም የባዕድ አገሩን ሰው ይወደዋል፤+ ምግብና ልብስም ይሰጠዋል። 19 እናንተም የባዕድ አገሩን ሰው ውደዱ፤ ምክንያቱም በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ።+
20 “አምላክህን ይሖዋን ፍራ፤ አገልግለው፤+ ከእሱም ጋር ተጣበቅ፤ በስሙም ማል። 21 ልታወድሰው የሚገባህ እሱን ነው።+ እሱ በዓይኖችህ ያየሃቸውን እነዚያን ታላላቅና አስፈሪ ነገሮች ሁሉ ያደረገልህ አምላክህ ነው።+ 22 አባቶችህ ወደ ግብፅ ሲወርዱ 70* ነበሩ፤+ አሁን ግን አምላክህ ይሖዋ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት ቁጥርህን አብዝቶታል።+
11 “አንተም አምላክህን ይሖዋን ውደድ፤+ ለእሱ ያለብህንም ግዴታ ምንጊዜም ተወጣ፤ እንዲሁም ደንቦቹን፣ ድንጋጌዎቹንና ትእዛዛቱን ሁልጊዜ ጠብቅ። 2 ዛሬ እየተናገርኩ ያለሁት ለእናንተ እንጂ የአምላካችሁን የይሖዋን ተግሣጽ፣+ የእሱን ታላቅነት፣+ የእሱን ብርቱ እጅና+ የተዘረጋ ክንድ ላላወቁት ወይም ላላዩት ለልጆቻችሁ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። 3 እነሱ በግብፅ ይኸውም በግብፁ ንጉሥ በፈርዖን ፊትና በመላው ምድሩ ላይ ያሳየውን ተአምራዊ ምልክትም ሆነ ያደረገውን ነገር አልተመለከቱም፤+ 4 ወይም እናንተን እያሳደዱ ሳሉ በቀይ ባሕር ውስጥ በሰጠሙት በግብፅ ሠራዊት፣ በፈርዖን ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች ላይ ያደረገውን አላዩም፤ ይሖዋም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ* አጠፋቸው።+ 5 እናንተ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን ነገር አልተመለከቱም፤ 6 ወይም ደግሞ የሮቤል ልጅ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንን እና አቤሮንን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ ድንኳኖቻቸውንና ከእነሱ ጋር ያበረውን ማንኛውንም ሕያው ፍጡር እስራኤላውያን ሁሉ እያዩ ምድር ተከፍታ በዋጠቻቸው ጊዜ በእነሱ ላይ ያደረገውን ነገር አልተመለከቱም።+ 7 እናንተ፣ ይሖዋ ያደረጋቸውን ታላላቅ ሥራዎች በሙሉ በገዛ ዓይናችሁ አይታችኋል።
8 “ብርታት እንድታገኙና ወደምትወርሷት ምድር ተሻግራችሁ እንድትገቡ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ፤ 9 ይሖዋ ለአባቶቻችሁና ለዘሮቻቸው ለመስጠት በማለላቸው+ ወተትና ማር በምታፈሰው ምድር+ ላይ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም+ እነዚህን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ።
10 “የምትወርሳት ምድር ዘር ትዘራባት እንዲሁም ልክ እንደ አትክልት ስፍራ በእግርህ* በመስኖ ታጠጣት እንደነበረችው እንደወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም። 11 ከዚህ ይልቅ ተሻግራችሁ የምትወርሷት ምድር ተራሮችና ሸለቋማ ሜዳዎች ያሉባት ምድር ናት።+ የሰማይን ዝናብ የምትጠጣ ምድር ናት፤+ 12 አምላክህ ይሖዋ የሚንከባከባት ምድር ናት። የአምላክህም የይሖዋ ዓይን ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ መጨረሻው ድረስ ዘወትር በእሷ ላይ ነው።
13 “እኔ ዛሬ የማዛችሁን ትእዛዛቴን በትጋት ብትፈጽሙ፣ አምላካችሁን ይሖዋን ብትወዱት እንዲሁም በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ* ብታገለግሉት፣+ 14 እኔ ደግሞ ለምድራችሁ በወቅቱ ዝናብን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እሰጣለሁ፤ አንተም እህልህን፣ አዲስ የወይን ጠጅህንና ዘይትህን ትሰበስባለህ።+ 15 ለእንስሶችህም በሜዳህ ላይ ዕፀዋት አበቅልልሃለሁ፤ አንተም በልተህ ትጠግባለህ።+ 16 ልባችሁ እንዳይታለልና ዞር ብላችሁ ሌሎች አማልክትን እንዳታመልኩ እንዲሁም እንዳትሰግዱላቸው ተጠንቀቁ።+ 17 አለዚያ የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ ዝናብ ዘንቦ ምድሪቱ ምርት እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤+ እናንተም ይሖዋ ከሚሰጣችሁ መልካም ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።+
18 “እነዚህን ቃሎቼን በልባችሁና በነፍሳችሁ* ላይ አትሟቸው፤ በእጃችሁም ላይ እንደ ማስታወሻ እሰሯቸው፤ በግንባራችሁም ላይ* እንደታሰረ ነገር ይሁኑ።+ 19 በቤታችሁ ስትቀመጡ፣ በመንገድ ላይ ስትሄዱ፣ ስትተኙና ስትነሱ ስለ እነሱ በመናገር ለልጆቻችሁ አስተምሯቸው።+ 20 በቤታችሁ መቃኖችና በግቢያችሁ በሮች ላይ ጻፏቸው፤ 21 ይህን ካደረጋችሁ ሰማይ ከምድር በላይ እስካለ ድረስ ይሖዋ ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር+ ላይ የእናንተም ሆነ የልጆቻችሁ ዕድሜ ይረዝማል።+
22 “አምላካችሁን ይሖዋን እንድትወዱ፣+ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄዱና ከእሱ ጋር እንድትጣበቁ የሰጠኋችሁን እነዚህን ሁሉ ትእዛዛት በጥብቅ ብትከተሉና ብትፈጽሟቸው+ 23 ይሖዋም እነዚህን ሁሉ ብሔራት ከፊታችሁ ያባርራቸዋል፤+ እናንተም ከእናንተ ይልቅ ታላቅ የሆኑትንና ብዙ ሕዝብ ያላቸውን ብሔራት ታስለቅቃላችሁ።+ 24 እግራችሁ የረገጠው ቦታ ሁሉ የእናንተ ይሆናል።+ ወሰናችሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ሊባኖስ እንዲሁም ከወንዙ ይኸውም ከኤፍራጥስ ወንዝ አንስቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር* ድረስ ይሆናል።+ 25 ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም።+ አምላካችሁ ይሖዋም ቃል በገባላችሁ መሠረት በምትረግጡት ምድር ሁሉ ላይ ሽብርና ፍርሃት ይለቃል።+
26 “እንግዲህ ዛሬ ይህን በረከትና እርግማን በፊታችሁ አስቀምጫለሁ፦+ 27 እኔ ዛሬ የማዛችሁን የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት ከፈጸማችሁ በረከቱን ታገኛላችሁ፤+ 28 የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት ካልፈጸማችሁና እኔ ዛሬ እንድትከተሉት ከማዛችሁ መንገድ ዞር በማለት የማታውቋቸውን አማልክት ከተከተላችሁ ግን እርግማኑ ይደርስባችኋል።+
29 “አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጋችሁ ወደምትወርሷት ምድር በሚያስገባችሁ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ ላይ እርግማኑን ደግሞ በኤባል ተራራ ላይ ታውጃላችሁ።*+ 30 እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ፣* በአረባ በሚኖሩት በከነአናውያን ምድር ከጊልጋል ትይዩ በሞሬ ትላልቅ ዛፎች አጠገብ አይደለም?+ 31 አሁን አምላካችሁ ይሖዋ የሚሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ነው።+ እንግዲህ ምድሪቱን ወርሳችሁ በእሷ ላይ ስትኖሩ 32 ዛሬ በፊታችሁ ያስቀመጥኳቸውን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽሙ።+
12 “የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ እንድትወርሷት በሚሰጣችሁ ምድር ላይ በሕይወት በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ በጥንቃቄ ልትፈጽሟቸው የሚገቡ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው። 2 ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው ብሔራት አማልክታቸውን ያመልኩባቸው የነበሩትን ቦታዎች በሙሉ፣ በረጃጅም ተራሮችም ሆነ በኮረብቶች ላይ ወይም በተንዠረገጉ ዛፎች ሥር ያሉትን ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ አጥፉ።+ 3 መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም* በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤+ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ።+
4 “እነሱ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት መንገድ አምላካችሁን ይሖዋን አታምልኩ።+ 5 ከዚህ ይልቅ በነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ስሙን ሊያጸናበትና ማደሪያ ስፍራው ሊያደርገው በሚመርጠው በማንኛውም ቦታ አምላካችሁን ይሖዋን ፈልጉ፤ ወደዚያም ስፍራ ሂዱ።+ 6 የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣+ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣+ ከእጃችሁ የሚዋጣውን መዋጮ፣+ የስእለት መባዎቻችሁን፣ የፈቃደኝነት መባዎቻችሁን+ እንዲሁም የከብታችሁንና የመንጋችሁን በኩራት+ የምትወስዱት ወደዚያ ስፍራ ነው። 7 እናንተም ሆናችሁ ቤተሰቦቻችሁ በዚያ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ብሉ፤+ አምላካችሁ ይሖዋ ስለባረካችሁ በሥራችሁ ሁሉ ተደሰቱ።+
8 “ዛሬ እዚህ እያደረግን እንዳለነው እያንዳንዳችሁ በራሳችሁ አመለካከት ትክክል መስሎ የታያችሁን ማድረግ የለባችሁም፤ 9 ምክንያቱም አሁን ይህን የምታደርጉት ወደምታርፉበት ቦታና+ አምላካችሁ ይሖዋ ወደሚሰጣችሁ ርስት ገና ስላልገባችሁ ነው። 10 ዮርዳኖስን በምትሻገሩበትና+ አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ በዙሪያችሁ ካሉ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ያሳርፋችኋል፤ እናንተም ያለስጋት ትቀመጣላችሁ።+ 11 የማዛችሁንም ነገር በሙሉ ይኸውም የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣+ የእጃችሁን መዋጮና ለይሖዋ የተሳላችሁትን ማንኛውንም የስእለት መባ አምላካችሁ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ታመጣላችሁ።+ 12 እናንተ፣ ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ሴቶች ልጆቻችሁ፣ ወንድ ባሪያዎቻችሁ፣ ሴት ባሪያዎቻችሁ እንዲሁም በከተሞቻችሁ* ውስጥ የሚኖር ሌዋዊ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ትደሰታላችሁ፤+ ምክንያቱም ሌዋዊው በእናንተ መካከል ድርሻም ሆነ ውርሻ አልተሰጠውም።+ 13 የሚቃጠሉ መባዎችህን በፈለግከው በየትኛውም ቦታ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ።+ 14 ከዚህ ይልቅ የሚቃጠሉ መባዎችህን ይሖዋ በሚመርጠው የነገዶችህ ይዞታ በሆነው ቦታ ብቻ አቅርብ፤ በዚያም እኔ የማዝህን ነገር ሁሉ አድርግ።+
15 “አምላክህ ይሖዋ በሰጠህ በረከት መጠን በከተሞችህ ሁሉ* አንተን ባሰኘህ* በማንኛውም ጊዜ እንስሳትን አርደህ ሥጋ መብላት ትችላለህ።+ የሜዳ ፍየልና ርኤም* እንደምትበላ ሁሉ ንጹሕ ያልሆነው ሰውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል። 16 ደሙን ግን እንዳትበሉ፤+ ከዚህ ይልቅ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍሱት።+ 17 የእህልህን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አንድ አሥረኛ፣ የከብትህንና የመንጋህን በኩር፣+ የምትሳለውን ማንኛውንም የስእለት መባ፣ የፈቃደኝነት መባዎችህን ወይም የእጅህን መዋጮ በከተሞችህ* ውስጥ እንድትበላ አይፈቀድልህም። 18 እነዚህንም አንተ፣ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህ፣ ሴት አገልጋይህ እንዲሁም በከተሞችህ* የሚኖሩ ሌዋውያን አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ+ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትበሏቸዋላችሁ፤ አንተም በሥራህ ሁሉ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትደሰታለህ። 19 በምድርህ ላይ በሕይወት እስካለህ ድረስ ሌዋውያንን ቸል እንዳትል ተጠንቀቅ።+
20 “አምላክህ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት+ ግዛትህን በሚያሰፋልህ ጊዜ+ ሥጋ መብላት ፈልገህ* ‘ሥጋ አማረኝ’ ብትል ባሰኘህ* ጊዜ ሁሉ ሥጋ ብላ።+ 21 አምላክህ ይሖዋ ስሙ እንዲኖርበት የሚመርጠው ስፍራ+ አንተ ካለህበት የራቀ ከሆነ ይሖዋ ከሰጠህ ከከብትህ ወይም ከመንጋህ መካከል እኔ ባዘዝኩህ መሠረት አርደህ ባሰኘህ* ጊዜ ሁሉ በከተሞችህ* ውስጥ ብላ። 22 የሜዳ ፍየልንና ርኤምን እንደምትበላው ሁሉ ይህንም ልትበላው ትችላለህ፤+ ንጹሕ ያልሆነው ሰውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል። 23 ብቻ ደሙን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ፤+ ምክንያቱም ደም ሕይወት* ነው፤+ ሕይወትን* ደግሞ ከሥጋ ጋር መብላት የለብህም። 24 ደሙን ፈጽሞ እንዳትበላ። ከዚህ ይልቅ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍስሰው።+ 25 ደሙን አትብላ፤ ምክንያቱም እንዲህ ስታደርግ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ትፈጽማለህ፤ ይህን የምታደርገው ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ ነው። 26 ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ስትመጣ የአንተ የሆኑትን ቅዱስ ነገሮችና የስእለት መባዎችህን ብቻ መያዝ ይኖርብሃል። 27 የሚቃጠሉ መባዎችህን፣ ሥጋውንና ደሙን+ በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ላይ ታቀርባለህ፤ የመሥዋዕቶችህም ደም በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ላይ መፍሰስ ይኖርበታል፤+ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ።
28 “እኔ የማዝህን እነዚህን ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም፤ ምክንያቱም እንዲህ ስታደርግ በአምላክህ በይሖዋ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ትፈጽማለህ፤ ይህን የምታደርገው ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ምንጊዜም መልካም እንዲሆንላችሁ ነው።
29 “ከምድራቸው የምታስለቅቃቸውን ብሔራት አምላክህ ይሖዋ ሲያጠፋቸውና+ በምድራቸው ላይ ስትኖር 30 እነሱ ከጠፉ በኋላ በእነሱ እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ። ‘እነዚህ ብሔራት አማልክታቸውን ያመልኩ የነበረው እንዴት ነው? ቆይ እኔም እንደ እነሱ አደርጋለሁ’ ብለህ ስለ አማልክታቸው አትጠይቅ።+ 31 አንተ በአምላክህ በይሖዋ ላይ ይህን ማድረግ የለብህም፤ ምክንያቱም እነሱ ይሖዋ የሚጠላውን አስጸያፊ ነገር ሁሉ ለአማልክታቸው ያደርጋሉ፤ ሌላው ቀርቶ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአማልክታቸው በእሳት ያቃጥላሉ።+ 32 እናንተ እኔ የማዛችሁን እያንዳንዱን ነገር በጥንቃቄ ፈጽሙ።+ በእሱ ላይ ምንም አትጨምሩ፤ ከእሱም ላይ ምንም አትቀንሱ።+
13 “አንድ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ከመካከልህ ተነስቶ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር እንደሚያሳይ ቢነግርህና 2 የነገረህ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር ቢፈጸም፣ እሱም ‘ሌሎች አማልክትን እንከተል’ ይኸውም አንተ የማታውቃቸውን አማልክት እንከተል፣ ‘እናገልግላቸውም’ ቢልህ፣ 3 የዚያን ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቃል እንዳትሰማ፤+ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ* አምላካችሁን ይሖዋን ትወዱት+ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ እየፈተናችሁ ነው።+ 4 እናንተ አምላካችሁን ይሖዋን ተከተሉ፤ እሱን ፍሩ፤ ትእዛዛቱን ጠብቁ፤ ቃሉን ስሙ፤ እሱን አገልግሉ፤ እንዲሁም እሱን አጥብቃችሁ ያዙ።+ 5 ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ግን ይገደል፤+ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ እንድትሄዱበት ካዘዛችሁ መንገድ ዞር እንድትሉ፣ ከግብፅ ምድር ባወጣችሁና ከባርነት ቤት በታደጋችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እንድታምፁ አበረታቷችኋል። አንተም ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ።+
6 “የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ አሊያም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ጓደኛህ* ‘ሌሎች አማልክትን እናምልክ’+ በማለት በሚስጥር ሊያባብልህ ቢሞክርና እነዚህ አማልክት ደግሞ አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸው 7 እንዲሁም በቅርብም ሆነ በሩቅ፣ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ የሚገኙ በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸው አማልክት ቢሆኑ 8 እሺ አትበለው ወይም አትስማው+ አሊያም አትዘንለት ወይም ደግሞ አትራራለት፤ ከለላም አትሁነው፤ 9 ከዚህ ይልቅ ያለማመንታት ግደለው።+ እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጅህን መሰንዘር ያለብህ አንተ ነህ፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ይሰንዝርበት።+ 10 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከይሖዋ ዞር እንድትል ሊያደርግህ ስለሞከረ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው።+ 11 ከዚያም እስራኤላውያን ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ በመካከልህም እንዲህ ያለ መጥፎ ነገር ዳግመኛ አያደርጉም።+
12 “አምላክህ ይሖዋ እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ትሰማ ይሆናል፦ 13 ‘እናንተ የማታውቋቸውን “ሌሎች አማልክት ሄደን እናምልክ” እያሉ የከተማቸውን ነዋሪዎች ለማሳት የሚሞክሩ የማይረቡ ሰዎች ከመካከልህ ተነስተዋል’፤ 14 በዚህ ጊዜ ጉዳዩን በጥልቀት በመመርመርና በማጣራት ስለ ሁኔታው ማወቅ ይኖርብሃል፤+ ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ ተፈጽሞ ከሆነና ነገሩ እውነት መሆኑ ከተረጋገጠ 15 የከተማዋን ነዋሪዎች በሰይፍ ግደላቸው።+ እንስሶቿን ጨምሮ ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ በሰይፍ ሙሉ በሙሉ አጥፋ።+ 16 ከዚያም በከተማዋ ውስጥ የተገኘውን ምርኮ በሙሉ በአደባባይዋ ላይ ሰብስብ፤ ከተማዋን በእሳት አቃጥል፤ በውስጧ የተገኘው ምርኮ ደግሞ ለአምላክህ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባ ይሆናል። እሷም ለዘላለም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች። ፈጽሞ ተመልሳ አትገነባም። 17 ይሖዋ ከሚነድ ቁጣው እንዲመለስ፣ ለአባቶችህ በማለላቸው መሠረት+ ምሕረት እንዲያደርግልህና እንዲራራልህ እንዲሁም እንዲያበዛህ ከፈለግክ፣ እንዲጠፉ ከተለዩት ነገሮች መካከል እጅህ ምንም አይውሰድ።+ 18 እኔ ዛሬ የምሰጥህን የእሱን ትእዛዛት በሙሉ በመጠበቅ አምላክህን ይሖዋን ታዘዝ፤* በዚህ መንገድ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ታደርጋለህ።+
14 “እናንተ የአምላካችሁ የይሖዋ ልጆች ናችሁ። ለሞተ ሰው ብላችሁ ሰውነታችሁን አትተልትሉ፤+ ቅንድባችሁንም* አትላጩ።+ 2 ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤+ ይሖዋም በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ* እንድትሆን መርጦሃል።+
3 “ማንኛውንም አስጸያፊ ነገር አትብላ።+ 4 የምትበሏቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው፦+ በሬ፣ በግ፣ ፍየል፣ 5 ርኤም፣ የሜዳ ፍየል፣ ድኩላ፣ የዱር ፍየል፣ አጋዘን፣ የዱር በግ እና የተራራ በግ። 6 ለሁለት የተከፈለ የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውን እንዲሁም የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ። 7 ሆኖም ከሚያመሰኩት ወይም የተሰነጠቀ ሰኮና ካላቸው እንስሳት መካከል እነዚህን አትብሉ፦ ግመል፣ ጥንቸልና ሽኮኮ፤ ምክንያቱም እነዚህ እንስሳት ቢያመሰኩም ሰኮናቸው ስንጥቅ አይደለም። እነሱ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።+ 8 አሳማም እንደዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ሰኮናው ስንጥቅ ቢሆንም አያመሰኳም። ለእናንተ ርኩስ ነው። ሥጋቸውን መብላትም ሆነ በድናቸውን መንካት የለባችሁም።
9 “በውኃ ውስጥ ከሚኖሩ መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ሁሉ መብላት ትችላላችሁ።+ 10 ሆኖም ክንፍና ቅርፊት የሌለውን ማንኛውንም ነገር አትብሉ። ለእናንተ ርኩስ ነው።
11 “ንጹሕ የሆነውን ወፍ ሁሉ መብላት ትችላላችሁ። 12 እነዚህን ግን አትብሉ፦ ንስር፣ ዓሣ በል ጭላት፣ ጥቁር ጥምብ አንሳ፣+ 13 ቀይ ጭልፊትም ሆነ ጥቁር ጭልፊት እንዲሁም ሁሉንም ዓይነት ሌሎች ጭልፊቶች፣ 14 ማንኛውንም ዓይነት ቁራ፣ 15 ሰጎን፣ ጉጉት፣ ዓሣ አዳኝ ወፍ፣ ማንኛውንም ዓይነት ሲላ፣ 16 ትንሿ ጉጉት፣ ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉት፣ ዝይ፣ 17 ሻላ፣ ጥምብ አንሳ፣ ለማሚት፣ 18 ራዛ፣ ማንኛውንም ዓይነት ሽመላ፣ ጅንጅላቴና የሌሊት ወፍ። 19 በተጨማሪም ክንፍ ያላቸው የሚርመሰመሱ ፍጥረታት* በሙሉ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። መበላት የለባቸውም። 20 ንጹሕ የሆነን ማንኛውንም የሚበር ፍጥረት መብላት ትችላላችሁ።
21 “ሞቶ የተገኘን ማንኛውንም እንስሳ አትብሉ።+ ከዚህ ይልቅ በከተሞችህ* ውስጥ ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው ልትሰጠውና እሱ ሊበላው ይችላል፤ አሊያም ለባዕድ አገር ሰው ሊሸጥ ይችላል። ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ።
“የፍየልን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።+
22 “በየዓመቱ ከእርሻህ ላይ ከምታገኘው ምርት ሁሉ አንድ አሥረኛውን* መስጠት አለብህ።+ 23 ዘወትር አምላክህን ይሖዋን መፍራትን+ እንድትማር የእህልህን፣ የአዲስ የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አንድ አሥረኛ እንዲሁም የከብትህንና የመንጋህን በኩራት በአምላክህ በይሖዋ ፊት ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ ብላ።+
24 “ሆኖም አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን የሚመርጠው ስፍራ+ አንተ ካለህበት ቦታ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ መንገዱ በጣም ቢረዝምብህና (አምላክህ ይሖዋ ስለባረከህ) እዚያ ድረስ ተሸክመኸው መሄድ ባትችል 25 ወደ ገንዘብ ልትቀይረው ትችላለህ፤ ገንዘቡንም ይዘህ አምላክህ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ። 26 ከዚያም በገንዘቡ የምትሻውን* ነገር ይኸውም ከብት፣ በግ፣ ፍየል፣ የወይን ጠጅ፣ ሌላ የሚያሰክር መጠጥና የሚያስደስትህን* ማንኛውንም ነገር መግዛት ትችላለህ፤ አንተና ቤተሰብህም በአምላክህ በይሖዋ ፊት በዚያ ብሉ፤ ተደሰቱም።+ 27 በከተሞችህ ውስጥ የሚኖረውን ሌዋዊ ችላ አትበለው፤+ ምክንያቱም እሱ ከአንተ ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ አልተሰጠውም።+
28 “በየሦስት ዓመቱ መጨረሻ ላይ በዚያ ዓመት ያገኘኸውን ምርት አንድ አሥረኛ በሙሉ አምጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች።+ 29 አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ+ ከአንተ ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ ያልተሰጠው ሌዋዊ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች፣ አባት የሌላቸው* ልጆችና መበለቶች መጥተው እስኪጠግቡ ድረስ ይብሉ።+
15 “በየሰባት ዓመቱ መጨረሻ የሌሎችን ዕዳ መሰረዝ ይኖርብሃል።+ 2 ዕዳ የሚሰረዘው በሚከተለው መንገድ ነው፦ እያንዳንዱ አበዳሪ ባልንጀራው ያለበትን ዕዳ ይሰርዝለታል። ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ክፍያ መጠየቅ የለበትም፤ ምክንያቱም ለይሖዋ ሲባል ዕዳ እንዲሰረዝ ይታወጃል።+ 3 ከባዕድ አገር ሰው ክፍያ መጠየቅ ትችላለህ፤+ ወንድምህ ለአንተ መመለስ ያለበትን ማንኛውንም ነገር ግን ተውለት። 4 ይሁንና አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ላይ ይሖዋ ስለሚባርክህ+ ከእናንተ መካከል ማንም ድሃ አይሆንም፤ 5 ይህ የሚሆነው ግን የአምላክህን የይሖዋን ቃል በትኩረት የምትሰማና እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዛት በሙሉ በጥንቃቄ የምትፈጽም ከሆነ ነው።+ 6 አምላክህ ይሖዋ በገባልህ ቃል መሠረት ይባርክሃልና፤ አንተም ለብዙ ብሔራት ታበድራለህ* እንጂ አትበደርም፤+ ብዙ ብሔራትን ትገዛለህ እንጂ አንተን አይገዙህም።+
7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።* 9 ‘ዕዳ የሚሰረዝበት ሰባተኛው ዓመት ቀርቧል’ የሚል ክፉ ሐሳብ በልብህ አድሮ ለድሃው ወንድምህ ከመለገስ ወደኋላ እንዳትልና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር ተጠንቀቅ።+ እሱ በአንተ ላይ ቅር ተሰኝቶ ወደ ይሖዋ ቢጮኽ ኃጢአት ይሆንብሃል።+ 10 በልግስና ስጠው፤+ ስትሰጠው ልብህ ቅር እያለው መሆን የለበትም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በሥራህ ሁሉና በምታከናውነው በማንኛውም ነገር የሚባርክህ በዚህ የተነሳ ነው።+ 11 መቼም ቢሆን ከምድሪቱ ላይ ድሆች አይጠፉምና።+ ‘በምድርህ ላይ ለሚኖር ጎስቋላና ድሃ ወንድምህ በልግስና እጅህን ዘርጋለት’ በማለት ያዘዝኩህ ለዚህ ነው።+
12 “ከወንድሞችህ አንዱ ይኸውም አንድ ዕብራዊ ወይም አንዲት ዕብራዊ፣ ለአንተ ቢሸጥና ስድስት ዓመት ቢያገለግልህ በሰባተኛው ዓመት ነፃ አውጣው።+ 13 ነፃ የምታወጣው ከሆነ ባዶ እጁን አትስደደው። 14 ከመንጋህና ከአውድማህ እንዲሁም ከዘይትና ከወይን መጭመቂያህ በልግስና ስጠው። አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን ስጠው። 15 አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ እንደተቤዠህ አስታውስ። እኔ ዛሬ ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው።
16 “ሆኖም ይህ ሰው ከአንተ ጋር በነበረበት ጊዜ ደስተኛ ስለነበር አንተንና ቤተሰብህን በመውደድ ‘ፈጽሞ ከአንተ አልለይም!’ ቢልህ+ 17 ጆሮውን በር ላይ አስደግፈህ በወስፌ ብሳው፤ እሱም ዕድሜ ልኩን የአንተ ባሪያ ይሆናል። ሴት ባሪያህንም በተመለከተ እንደዚሁ አድርግ። 18 ባሪያህን ነፃ አድርጎ ማሰናበት ሊከብድህ አይገባም፤ ምክንያቱም እሱ በስድስት ዓመት ውስጥ የሰጠህ አገልግሎት በቅጥር ሠራተኛ ደሞዝ ቢሰላ እጥፍ ዋጋ ያስወጣህ ነበር፤ ደግሞም አምላክህ ይሖዋ በምትሠራው ነገር ሁሉ ባርኮሃል።
19 “ከከብትህና ከመንጋህ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለአምላክህ ለይሖዋ ቀድሰው።+ በከብትህ* በኩር ምንም ሥራ አትሥራበት፤ የመንጋህንም በኩር አትሸልት። 20 አንተም ሆንክ ቤተሰብህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በየዓመቱ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ብሉት።+ 21 ይሁንና እንስሳው እንከን ካለበት ይኸውም አንካሳ ወይም ዕውር ከሆነ አሊያም ሌላ ዓይነት ከባድ ጉድለት ካለበት ለአምላክህ ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርበው።+ 22 በከተሞችህ* ውስጥ ብላው፤ እንደ ሜዳ ፍየል ወይም እንደ ርኤም* ሁሉ ንጹሕ ያልሆነውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል።+ 23 ሆኖም ደሙን አትብላ፤+ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍስሰው።+
16 “አምላክህ ይሖዋ ከግብፅ በሌሊት ያወጣህ በአቢብ* ወር ስለሆነ የአቢብን ወር አስብ፤+ እንዲሁም ለአምላክህ ለይሖዋ ፋሲካን* አክብር።+ 2 ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በመረጠው ስፍራ+ ከመንጋህና ከከብትህ+ ለአምላክህ ለይሖዋ የፋሲካን መባ ሠዋ።+ 3 ከእሱም ጋር እርሾ የገባበት ምንም ነገር አትብላ፤+ ከግብፅ ምድር የወጣኸው በጥድፊያ ስለነበር+ ለሰባት ቀን ቂጣ* ይኸውም የመከራ ቂጣ ብላ። ይህን የምታደርገው ከግብፅ ምድር የወጣህበትን ዕለት በሕይወት ዘመንህ ሁሉ እንድታስታውስ ነው።+ 4 ለሰባት ቀን በግዛትህ ሁሉ እርሾ አይገኝ፤+ በመጀመሪያው ቀን ምሽት ላይ ከምታቀርበው መሥዋዕት ላይም ቢሆን ምንም ሥጋ ማደር የለበትም።+ 5 የፋሲካውን መባ አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ከተሞች አንተ በፈለግከው በአንዱ ውስጥ መሠዋት አይገባህም። 6 ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ መቅረብ ይኖርበታል። የፋሲካውን መባ ምሽት ላይ ፀሐይ እንደጠለቀች፣+ ከግብፅ በወጣህበት በዚያው ጊዜ ሠዋው። 7 አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ቦታ+ አብስለህ ብላው፤+ ሲነጋም ተመልሰህ ወደ ድንኳንህ መሄድ ትችላለህ። 8 ለስድስት ቀን ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለይሖዋ የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ሥራ አትሥራ።+
9 “ሰባት ሳምንት ቁጠር። ሰባቱን ሳምንት መቁጠር መጀመር ያለብህ በማሳህ ላይ ያለውን እህል ለማጨድ ማጭድህን ካነሳህበት ጊዜ አንስቶ ነው።+ 10 ከዚያም አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን+ በምታቀርበው የፈቃደኝነት መባ አማካኝነት ለአምላክህ ለይሖዋ የሳምንታት በዓልን ታከብራለህ።+ 11 በአምላክህ በይሖዋ ፊት ደስ ይበልህ፤ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ* የሚኖር ሌዋዊ፣ በመካከልህ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው* ልጅና መበለቲቱ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በመረጠው ስፍራ ደስ ይበላችሁ።+ 12 አንተም በግብፅ ባሪያ እንደነበርክ አስታውስ፤+ እነዚህንም ሥርዓቶች ጠብቅ እንዲሁም ፈጽም።
13 “እህልህን ከአውድማህ፣ ዘይትህንና የወይን ጠጅህን ከመጭመቂያህ በምታስገባበት ጊዜ የዳስ* በዓልን+ ለሰባት ቀን አክብር። 14 በዓልህን በምታከብርበት ወቅት ደስ ይበልህ፤+ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖር ሌዋዊ፣ የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው ልጅና መበለቲቱ ደስ ይበላችሁ። 15 አምላክህ ይሖዋ ምርትህንና የእጅህን ሥራ ሁሉ ስለሚባርክልህ+ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለይሖዋ ሰባት ቀን በዓሉን ታከብራለህ፤+ አንተም እጅግ ትደሰታለህ።+
16 “በመካከልህ ያሉ ወንዶች ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ ይኸውም በቂጣ በዓል+ ቀን፣ በሳምንታት በዓል+ ቀን እንዲሁም በዳስ* በዓል+ ቀን አምላክህ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ፊቱ ይቅረቡ፤ ማናቸውም ባዶ እጃቸውን ይሖዋ ፊት አይቅረቡ። 17 እያንዳንዱ ሰው የሚያመጣው ስጦታ አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን መሆን አለበት።+
18 “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለእያንዳንዱ ነገድ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤+ እነሱም ለሕዝቡ የጽድቅ ፍርድ ይፍረዱ። 19 ፍርድን አታዛባ፤+ አድልዎ አትፈጽም+ ወይም ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራል፤+ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማል። 20 በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ ይሖዋ የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ ፍትሕን፣ አዎ ፍትሕን ተከታተል።+
21 “ለአምላክህ ለይሖዋ በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የማምለኪያ ግንድ*+ እንዲሆን ማንኛውንም ዓይነት ዛፍ አትትከል።
22 “አምላክህ ይሖዋ አጥብቆ የሚጠላውን የማምለኪያ ዓምድ ለራስህ አታቁም።+
17 “እንከን ወይም ማንኛውም ዓይነት ጉድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለይሖዋ አትሠዋ፤ ምክንያቱም ይህ ለአምላክህ ለይሖዋ አስጸያፊ ነው።+
2 “አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዱ ውስጥ በአምላክህ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር የሚፈጽምና ቃል ኪዳኑን የሚያፈርስ ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ+ 3 እሱም ሄዶ ሌሎች አማልክትን በማምለክ እንዲሁም ለእነሱ ወይም ለፀሐይ አሊያም ለጨረቃ ወይም ደግሞ ለሰማይ ሠራዊት በሙሉ በመስገድ+ እኔ ያላዘዝኩትን ነገር ቢያደርግ+ 4 አንተም ይህ ነገር ቢነገርህ ወይም ሁኔታውን ብትሰማ ጉዳዩን በጥንቃቄ አጣራ። ይህ አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ውስጥ መፈጸሙ እውነት እንደሆነ ቢረጋገጥ+ 5 እንዲህ ያለ መጥፎ ድርጊት የፈጸመውን ያንን ሰው ወይም ያቺን ሴት ወደ ከተማዋ በር አውጣቸው፤ ከዚያም ሰውየው ወይም ሴትየዋ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ይወገሩ።+ 6 ሞት የሚገባው ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በሚሰጡት ምሥክርነት*+ ይገደል። አንድ ምሥክር በሚሰጠው ቃል ብቻ መገደል የለበትም።+ 7 እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጃቸውን የሚያነሱት ምሥክሮቹ መሆን ይኖርባቸዋል፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ያንሳበት። ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+
8 “ከከተሞችህ በአንዱ ውስጥ ለመዳኘት አስቸጋሪ የሆነ ክርክር ቢነሳ ለምሳሌ፣ ጉዳዩ ደም ማፍሰስን+ የሚመለከትም ይሁን ለሕግ አቤቱታ ማቅረብን ወይም የዓመፅ ድርጊትን አሊያም ሌሎች አለመግባባቶችን የሚመለከት ቢሆን ተነስተህ አምላክህ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ውጣ።+ 9 ወደ ሌዋውያን ካህናትና በዚያን ጊዜ ዳኛ ሆኖ ወደሚያገለግለው ሰው+ ሄደህ ጠይቅ፤ እነሱም ውሳኔውን ይነግሩሃል።+ 10 አንተም እነዚህ ሰዎች ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ ሆነው በነገሩህ ውሳኔ መሠረት እርምጃ ውሰድ። የሰጡህንም መመሪያ በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም። 11 በሚሰጡህ ሕግና በሚነግሩህ ውሳኔ መሠረት እርምጃ ውሰድ።+ እነሱ ካሳለፉት ውሳኔ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል።+ 12 አምላክህን ይሖዋን የሚያገለግለውን ካህን ወይም ዳኛውን ባለመስማት እብሪተኛ የሚሆን ሰው ካለ ይገደል።+ ክፉ የሆነውን ከእስራኤል መካከል አስወግድ።+ 13 ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲሰማ ይፈራል፤ ከእንግዲህም የእብሪት ድርጊት አይፈጽምም።+
14 “አምላክህ ይሖዋ የሚሰጥህን ምድር ገብተህ ከወረስካት በኋላ በዚያ መኖር ስትጀምር ‘በዙሪያዬ እንዳሉት ብሔራት ሁሉ እኔም በላዬ ላይ ንጉሥ ላንግሥ’ ብትል+ 15 አምላክህ ይሖዋ የሚመርጠውን ንጉሥ ታነግሣለህ። የምታነግሠውም ንጉሥ ከወንድሞችህ መካከል መሆን ይኖርበታል።+ ወንድምህ ያልሆነን ባዕድ ሰው በላይህ ላይ ማንገሥ አይገባህም። 16 ይሁን እንጂ ንጉሡ ለራሱ ፈረሶች ማብዛት+ ወይም የፈረሶቹን ቁጥር ለመጨመር ሲል ሕዝቡ ወደ ግብፅ እንዲመለስ ማድረግ የለበትም፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ‘በዚህ መንገድ ፈጽሞ ዳግመኛ እንዳትመለሱ’ ብሏችኋል። 17 ልቡ ከትክክለኛው መንገድ ዞር እንዳይል ለራሱ ሚስቶች አያብዛ፤+ ለራሱም ብርና ወርቅ አያከማች።+ 18 በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ በሌዋውያን ካህናት እጅ ካለው ላይ ወስዶ የዚህን ሕግ ቅጂ ለራሱ በመጽሐፍ* ላይ ይጻፍ።+
19 “አምላኩን ይሖዋን መፍራትን እንዲማር እንዲሁም በዚህ ሕግና በእነዚህ ሥርዓቶች ላይ የሰፈሩትን ቃላት በሙሉ በመፈጸም እንዲጠብቃቸው ይህ መጽሐፍ ከእሱ ጋር ይሁን፤+ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ያንብበው።+ 20 ይህን ካደረገ ልቡ በወንድሞቹ ላይ አይታበይም፤ ከትእዛዛቱም ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አይልም፤ ይህም እሱም ሆነ ልጆቹ በእስራኤል መካከል በመንግሥቱ ላይ ረጅም ዘመን እንዲቆዩ ያስችላቸዋል።
18 “ሌዋውያኑ ካህናት አልፎ ተርፎም መላው የሌዊ ነገድ ከእስራኤል ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ አይሰጣቸውም። የእሱ ድርሻ የሆኑትን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርቡትን መባዎች ይበላሉ።+ 2 በመሆኑም በወንድሞቻቸው መካከል ውርሻ ሊኖራቸው አይገባም። አስቀድሞ በነገራቸው መሠረት ውርሻቸው ይሖዋ ነው።
3 “ካህናት ከሕዝቡ ሊያገኙ የሚገባቸው ድርሻ የሚከተለው ይሆናል፦ በሬም ሆነ በግ መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው የእንስሳውን ወርች፣ መንገጭላውንና ሆድ ዕቃውን ለካህኑ ይስጥ። 4 የእህልህን በኩር፣ አዲስ የወይን ጠጅህንና ዘይትህን እንዲሁም ከመንጋህ በመጀመሪያ የተሸለተውን ፀጉር ስጠው።+ 5 አምላክህ ይሖዋ ከነገዶችህ ሁሉ መካከል በይሖዋ ስም ሁልጊዜ እንዲያገለግል የመረጠው እሱንና ወንዶች ልጆቹን ነው።+
6 “ሆኖም አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት በእስራኤል ከሚገኙ ከተሞችህ+ ከአንዱ ወጥቶ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ*+ መሄድ ቢፈልግ* 7 በይሖዋ ፊት ቆመው እንደሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ ሁሉ እሱም በዚያ በአምላኩ በይሖዋ ስም ሊያገለግል ይችላል።+ 8 የአባቶቹን ርስት በመሸጥ ከሚያገኘው ገንዘብ በተጨማሪ ከእነሱ እኩል ምግብ ይሰጠዋል።+
9 “አምላክህ ይሖዋ ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ በዚያ የሚገኙ ብሔራት የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ነገሮች አታድርግ።+ 10 ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፣+ ሟርተኛ፣+ አስማተኛ፣+ ሞራ ገላጭ፣+ ምትሃተኛ፣+ 11 ድግምተኛ፣ መናፍስት ጠሪ፣+ ጠንቋይ+ ወይም ሙታን አነጋጋሪ+ በመካከልህ አይገኝ። 12 ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው፤ አምላክህ ይሖዋም እነሱን ከፊትህ የሚያባርራቸው በእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች የተነሳ ነው። 13 በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንከን የለሽ ሆነህ መገኘት አለብህ።+
14 “አንተ ከምድራቸው የምታስለቅቃቸው እነዚህ ብሔራት አስማተኞችንና+ ሟርተኞችን+ ይሰማሉ፤ አንተ ግን እንዲህ እንድታደርግ አምላክህ ይሖዋ አልፈቀደልህም። 15 አምላክህ ይሖዋ ከወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል። እናንተም እሱን ማዳመጥ ይኖርባችኋል።+ 16 ይህም የሚሆነው በኮሬብ ተሰብስባችሁ+ በነበረበት ዕለት ‘እንዳልሞት የአምላኬን የይሖዋን ድምፅ ከእንግዲህ አልስማ ወይም ይህን ታላቅ እሳት ከእንግዲህ አልይ’+ በማለት አምላካችሁን ይሖዋን በጠየቃችሁት መሠረት ነው። 17 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘የተናገሩት ነገር መልካም ነው። 18 ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሳላቸዋለሁ፤+ ቃሌንም በአፉ ላይ አደርጋለሁ፤+ እሱም እኔ የማዘውን ሁሉ ይነግራቸዋል።+ 19 በእኔ ስም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው በእርግጥ ተጠያቂ አደርገዋለሁ።+
20 “‘እኔ እንዲናገር ያላዘዝኩትን ቃል በእብሪት ተነሳስቶ በስሜ የሚናገር ወይም በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ካለ ያ ነቢይ ይገደል።+ 21 ሆኖም አንተ በልብህ “ታዲያ ቃሉን ይሖዋ እንዳልተናገረው እንዴት እናውቃለን?” ብለህ ታስብ ይሆናል። 22 ነቢዩ በይሖዋ ስም ቢናገርና የተናገረው ቃል ባይፈጸም ወይም እውነት ሆኖ ባይገኝ ይህን ቃል የተናገረው ይሖዋ አይደለም። ይህ ቃል ነቢዩ በእብሪት ተነሳስቶ የተናገረው ነው። እሱን ልትፈራው አይገባም።’
19 “አምላክህ ይሖዋ ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥህን ብሔራት፣ ይሖዋ በሚያጠፋቸውና አንተም እነሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው መኖር በምትጀምርበት ጊዜ+ 2 አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ሦስት ከተሞችን ለይ።+ 3 አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት የሚሰጥህን ምድር ሦስት ቦታ ከፋፍላት፤ እንዲሁም ነፍስ ያጠፋ ማንኛውም ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ መሸሽ እንዲችል መንገድ አዘጋጅ።
4 “እዚያ ለመኖር ሸሽቶ የሄደን፣ ነፍስ ያጠፋ ሰው በተመለከተ መደረግ ያለበት ነገር ይህ ነው፦ ለባልንጀራው የቆየ ጥላቻ የሌለው አንድ ሰው ሳያስበው ባልንጀራውን መትቶ ቢገድለው፣+ 5 ለምሳሌ ከባልንጀራው ጋር እንጨት ለመቁረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፣ ዛፉንም ለመቁረጥ መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ላይ ወልቆ ባልንጀራውን ቢመታውና ቢገድለው ነፍሰ ገዳዩ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።+ 6 አለዚያ በንዴት የበገነው* ደም ተበቃይ+ ከተማዋ ሩቅ ከመሆኗ የተነሳ ነፍሰ ገዳዩን አሳዶ ሊደርስበትና ሊገድለው ይችላል። ይሁን እንጂ ይህ ሰው ለባልንጀራው የቆየ ጥላቻ ስለሌለው መሞት አይገባውም።+ 7 ‘ሦስት ከተሞችን ለይ’ በማለት ያዘዝኩህ ለዚህ ነው።
8 “አምላክህ ይሖዋ ለአባቶችህ በማለላቸው መሠረት ግዛትህን ሲያሰፋልህና+ ለእነሱ ለመስጠት ቃል የገባላቸውን ምድር በሙሉ ሲሰጥህ+ 9 ይኸውም አምላክህን ይሖዋን እንድትወድና ዘወትር በመንገዶቹ እንድትሄድ እኔ ዛሬ የማዝህን ይህን ትእዛዝ ሁሉ በመጠበቅህ+ ግዛትህን ሲያሰፋልህ ከእነዚህ ሦስት ከተሞች በተጨማሪ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትለያለህ።+ 10 ይህም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ንጹሕ ደም እንዳይፈስና+ በደም ዕዳ ተጠያቂ እንዳትሆን ነው።+
11 “ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፣+ አድብቶም ለሞት የሚያበቃ ጉዳት ቢያደርስበትና ሰውየው ቢሞት፣ ገዳዩም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ ቢሸሽ 12 የሚኖርበት ከተማ ሽማግሌዎች ሰውየውን ከዚያ በማስመጣት ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት፤ ይህ ሰው ሞት ይገባዋል።+ 13 አትዘንለት፤* መልካም እንዲሆንልህ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የሚመጣን በደል ከእስራኤል አስወግድ።+
14 “አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ርስትህን በምትቀበልበት ጊዜ የቀድሞ አባቶችህ የከለሉትን ወሰን በማለፍ የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንካ።+
15 “አንድ ሰው የትኛውንም ስህተት ወይም የትኛውንም ኃጢአት ቢፈጽም ግለሰቡን ጥፋተኛ ለማድረግ አንድ ምሥክር አይበቃም።+ ጉዳዩ የሚጸናው ሁለት ምሥክሮች ወይም ሦስት ምሥክሮች በሚሰጡት የምሥክርነት ቃል* ነው።+ 16 ተንኮል ያሰበ አንድ ምሥክር አንድን ግለሰብ የሆነ በደል ፈጽሟል በማለት ቢመሠክርበት+ 17 ክርክር የገጠሙት ሁለቱ ሰዎች በይሖዋ ፊት፣ በካህናቱና በዚያን ጊዜ ዳኛ ሆነው በሚያገለግሉት ሰዎች ፊት ይቆማሉ።+ 18 ዳኞቹም ጉዳዩን በጥንቃቄ ይመረምራሉ፤+ ምሥክሩ ሐሰተኛ ምሥክር ከሆነና ወንድሙን የወነጀለው በሐሰት ከሆነ 19 በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያቀደውን ነገር በራሱ ላይ አድርጉበት፤+ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+ 20 ሌሎችም ይህን ሲሰሙ ይፈራሉ፤ በመካከልህም እንዲህ ያለ መጥፎ ነገር ፈጽሞ ዳግመኛ አያደርጉም።+ 21 አዘኔታ አታሳይ፤+ ሕይወት* ስለ ሕይወት፣* ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፣ እጅ ስለ እጅ እንዲሁም እግር ስለ እግር ይሁን።+
20 “ከጠላቶችህ ጋር ጦርነት ለመግጠም ብትሄድና ፈረሶቻቸው፣ ሠረገሎቻቸውና ሠራዊታቸው ከአንተ ይልቅ እጅግ ብዙ መሆናቸውን ብታይ አትፍራቸው፤ ምክንያቱም ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ነው።+ 2 ወደ ውጊያው ለመግባት በምትቀርቡበትም ጊዜ ካህኑ መጥቶ ሕዝቡን ማነጋገር አለበት።+ 3 እንዲህም ይበላቸው፦ ‘እስራኤላውያን ሆይ፣ ስሙ፤ እንግዲህ ዛሬ ከጠላቶቻችሁ ጋር ጦርነት ልትገጥሙ ነው። ልባችሁ አይራድ። በእነሱ ምክንያት አትፍሩ፣ አትሸበሩ ወይም አትንቀጥቀጡ፤ 4 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ ጠላቶቻችሁን ሊዋጋላችሁና ሊያድናችሁ አብሯችሁ ይወጣል።’+
5 “አለቆቹም ሕዝቡን እንዲህ ይበሉ፦ ‘ከመካከላችሁ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለ? ወደ ቤቱ ይመለስ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ቤቱን ሌላ ሰው ሊያስመርቀው ይችላል። 6 ወይን ተክሎ ገና ከዚያ ያልበላ አለ? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ሌላ ሰው ሊበላው ይችላል። 7 አንዲት ሴት አጭቶ ገና ያላገባት ሰው አለ? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።+ አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ሌላ ሰው ሊያገባት ይችላል።’ 8 በተጨማሪም አለቆቹ ለሕዝቡ እንዲህ በማለት ይናገሩ፦ ‘ከመካከላችሁ የፈራና ልቡ የራደ አለ?+ ልክ እንደ ራሱ ልብ የወንድሞቹንም ልብ እንዳያቀልጥ+ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።’ 9 አለቆቹም ለሕዝቡ ተናግረው ሲጨርሱ ሕዝቡን እንዲመሩ የሠራዊቱን አለቆች ይሹሙ።
10 “አንዲትን ከተማ ለመውጋት ወደ እሷ ስትቀርብ ለከተማዋ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ።+ 11 ከተማዋ የሰላም ጥሪህን ከተቀበለችና በሯን ከከፈተችልህ ነዋሪዎቿ ሁሉ የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሕዝቦች ይሆኑልሃል፤ አንተንም ያገለግሉሃል።+ 12 ይሁን እንጂ የሰላም ጥሪህን ካልተቀበለችና ከአንተ ጋር ውጊያ ለመግጠም ከተነሳች ከተማዋን ክበባት፤ 13 አምላክህ ይሖዋ ከተማዋን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አንተም በውስጧ የሚኖሩትን ወንዶች ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው። 14 ሆኖም ሴቶቹን፣ ትናንሽ ልጆቹን፣ እንስሳቱንና በከተማዋ ውስጥ የተገኘውን ነገር ሁሉ ማርከህ ለራስህ መውሰድ ትችላለህ፤+ አምላክህ ይሖዋ በእጅህ አሳልፎ የሰጠህን ከጠላቶችህ ያገኘኸውን ምርኮም ትበላለህ።+
15 “በአቅራቢያህ በሚገኙ በእነዚህ ብሔራት ከተሞች ላይ ሳይሆን ከአንተ ርቀው በሚገኙት ከተሞች ሁሉ ላይ የምታደርገው ይህንኑ ነው። 16 አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ እነዚህ ሕዝቦች በሚኖሩባቸው ከተሞች ውስጥ ግን እስትንፋስ ያለውን ማንኛውንም ነገር በሕይወት አታስቀር።+ 17 ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ሂታውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ሙሉ በሙሉ አጥፋ፤+ 18 ይህን የምታደርጉት ለአማልክታቸው የሚያደርጓቸውን አስጸያፊ ነገሮች በሙሉ እንዳያስተምሯችሁና በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እንድትሠሩ እንዳያደርጓችሁ ነው።+
19 “አንዲትን ከተማ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ብትከባትና ለብዙ ቀናት ብትወጋት ዛፎቿን በመጥረቢያ አትጨፍጭፍ። ፍሬያቸውን ልትበላ ትችላለህ፤ ሆኖም አትቁረጣቸው።+ ደግሞስ ሰው ይመስል የሜዳን ዛፍ ከበህ ማጥፋት አለብህ? 20 ለምግብነት እንደማይሆን የምታውቀውን ዛፍ ብቻ ማጥፋት ትችላለህ። ዛፉንም ቆርጠህ ከአንተ ጋር ውጊያ የገጠመችው ከተማ እስክትወድቅ ድረስ ዙሪያዋን ልታጥርበት ትችላለህ።
21 “አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር አንድ ሰው ሜዳ ላይ ተገድሎ ቢገኝና ማን እንደገደለው ባይታወቅ 2 ሽማግሌዎችህና ዳኞችህ+ ወጥተው የሞተው ሰው ከተገኘበት ስፍራ አንስቶ በዙሪያው እስከሚገኙት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ። 3 ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ምንም ሥራ ያልተሠራባትንና ቀንበር ተጭኖባት የማያውቅን ጊደር ከከብቶች መካከል ይውሰዱ፤ 4 የከተማዋም ሽማግሌዎች ጊደሯን ከዚህ ቀደም ታርሶ ወይም ዘር ተዘርቶበት ወደማያውቅ ወራጅ ውኃ ወዳለበት ሸለቆ* ይውሰዷት፤ በሸለቆውም ውስጥ የጊደሯን አንገት ይስበሩ።+
5 “ሌዋውያኑ ካህናት ይቅረቡ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ እሱን እንዲያገለግሉና በይሖዋ ስም እንዲባርኩ+ የመረጠው እነሱን ነው።+ ደግሞም የኃይል ጥቃትን በተመለከተ ለሚነሳ ለማንኛውም ክርክር እልባት የሚሰጡት እነሱ ናቸው።+ 6 ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆኑት የከተማዋ ሽማግሌዎች በሙሉ በሸለቆው ውስጥ አንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤+ 7 እንዲህ ብለውም ይናገሩ፦ ‘እጆቻችን ይህን ደም አላፈሰሱም፤ ዓይኖቻችንም ይህ ደም ሲፈስ አላዩም። 8 ይሖዋ ሆይ፣ የታደግከውን+ ሕዝብህን እስራኤልን በዚህ ድርጊት ተጠያቂ አታድርገው፤ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመ በደልም በሕዝብህ በእስራኤል መካከል እንዲኖር አትፍቀድ።’+ እነሱም በደም ዕዳው ተጠያቂ አይሆኑም። 9 በዚህ መንገድ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመን በደል ከመካከልህ በማስወገድ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ።
10 “ከጠላቶችህ ጋር ብትዋጋ፣ አምላክህ ይሖዋም እነሱን በእጅህ አሳልፎ ቢሰጥህ፣ አንተም ምርኮኛ አድርገህ ብትወስዳቸውና+ 11 ከምርኮኞቹ መካከል አንዲት የምታምር ሴት አይተህ ብትወዳት፣ ሚስትህም ልታደርጋት ብትፈልግ 12 ወደ ቤትህ ልትወስዳት ትችላለህ። እሷም ፀጉሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቁረጥ፤ 13 የምርኮኛነት ልብሷን ታውልቅ፤ በቤትህም ትቀመጥ። ለአባቷና ለእናቷ አንድ ወር ሙሉ ታልቅስ፤+ ከዚህ በኋላ ከእሷ ጋር ግንኙነት መፈጸም ትችላለህ፤ አንተ ባሏ ትሆናለህ፤ እሷም ሚስትህ ትሆናለች። 14 በእሷ ካልተደሰትክ ግን ወደፈለገችበት* እንድትሄድ አሰናብታት።+ ሆኖም ለውርደት ስለዳረግካት በገንዘብ ልትሸጣት ወይም ግፍ ልትፈጽምባት አይገባም።
15 “አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩትና አንደኛዋን ከሌላኛዋ አስበልጦ የሚወዳት ቢሆን፣* ሁለቱም ወንዶች ልጆች ቢወልዱለትና በኩሩ የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ+ ቢሆን 16 ውርሱን ለወንዶች ልጆቹ በሚያስተላልፍበት ቀን ከማይወዳት ሚስቱ የተወለደውን በኩር የሆነውን ወንድ ልጅ ትቶ ከሚወዳት ሚስቱ የተወለደውን ወንድ ልጅ እንደ በኩር ልጁ አድርጎ መቁጠር የለበትም። 17 ከዚህ ይልቅ ከማይወዳት ሚስቱ ለተወለደው ወንድ ልጅ፣ ካለው ከማንኛውም ነገር ላይ ሁለት እጥፍ በመስጠት የልጁን ብኩርና መቀበል ይኖርበታል፤ ምክንያቱም የጎልማሳነቱ ብርታት መጀመሪያ ይህ ልጅ ነው። የብኩርና መብቱ የእሱ ነው።+
18 “አንድ ሰው እልኸኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው ልጁም አባቱንም ሆነ እናቱን ለመታዘዝ አሻፈረኝ ቢል፣+ እነሱም እርማት ሊሰጡት ቢሞክሩና እሱ ግን ሊሰማቸው ፈቃደኛ ባይሆን+ 19 አባትና እናቱ እሱ ባለበት ከተማ በር ላይ ወዳሉት ሽማግሌዎች ያምጡት፤ 20 ሽማግሌዎቹንም ‘ይህ ልጃችን እልኸኛና ዓመፀኛ ነው፤ ሊታዘዘንም ፈቃደኛ አይደለም። ሆዳምና+ ሰካራም+ ነው’ ይበሏቸው። 21 ከዚያም የከተማዋ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ።+
22 “አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ሠርቶ ቢገደልና+ በእንጨት ላይ ብትሰቅለው+ 23 በድኑ በእንጨቱ ላይ አይደር።+ ከዚህ ይልቅ በዚያው ዕለት ቅበረው፤ ምክንያቱም እንጨት ላይ የሚሰቀለው፣ አምላክ የረገመው ነው፤+ አንተም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር አታርክስ።+
22 “የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ካየህ እንዳላየ ሆነህ አትለፍ።+ ከዚህ ይልቅ ወደ ወንድምህ መልሰህ ልትወስደው ይገባል። 2 ሆኖም ወንድምህ በአቅራቢያህ የማይኖር ወይም እሱን የማታውቀው ከሆነ እንስሳውን ወደ ቤትህ አምጣው፤ ወንድምህ እሱን ፈልጎ እስኪመጣም ድረስ አንተ ጋ ይቆይ። ከዚያም መልስለት።+ 3 አህያውንም ሆነ ልብሱን ወይም ወንድምህ ጠፍቶበት ያገኘኸውን ማንኛውንም ነገር በተመለከተ እንዲሁ ማድረግ ይኖርብሃል። አይተህ ዝም ብለህ ማለፍ የለብህም።
4 “የወንድምህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታይ እንዳላየ ሆነህ አትለፍ። ከዚህ ይልቅ እንስሳው ተነስቶ እንዲቆም በማድረግ ሰውየውን ልትረዳው ይገባል።+
5 “ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድ ደግሞ የሴት ልብስ አይልበስ። ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው።
6 “መንገድ ላይ ስትሄድ ጫጩቶች ወይም እንቁላሎች ያሉበት የወፍ ጎጆ፣ ዛፍ ላይ ወይም መሬት ላይ ብታገኝና እናትየው ጫጩቶቹን ወይም እንቁላሎቹን ታቅፋ ቢሆን እናትየውን ከጫጩቶቿ ጋር አብረህ አትውሰድ።+ 7 እናትየውን ልቀቃት፤ ጫጩቶቹን ግን መውሰድ ትችላለህ። ይህን የምታደርገው መልካም እንዲሆንልህና ዕድሜህ እንዲረዝም ነው።
8 “አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ አንድ ሰው ከጣሪያህ ላይ ወድቆ በቤትህ ላይ የደም ዕዳ እንዳታመጣ በጣሪያህ ዙሪያ መከታ ሥራ።+
9 “በወይን እርሻህ ላይ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ።+ እንዲህ ካደረግክ ከዘራኸው ዘር የሚገኘው ምርትም ሆነ የወይን እርሻህ ምርት በሙሉ ተወርሶ ለቤተ መቅደሱ ገቢ ይደረጋል።
10 “በሬና አህያ አንድ ላይ ጠምደህ አትረስ።+
11 “ከሱፍና ከበፍታ ተቀላቅሎ የተሠራ ልብስ አትልበስ።+
12 “በምትለብሰው ልብስ ላይ በአራቱም ማዕዘን ዘርፍ አድርግ።+
13 “አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ከእሷ ጋር ግንኙነት ከፈጸመ በኋላ ቢጠላት፣ 14 መጥፎ ምግባር እንዳላት አድርጎ ቢከሳትና ‘ይህችን ሴት አግብቼ ነበር፤ ሆኖም ከእሷ ጋር ግንኙነት ስፈጽም የድንግልናዋን ማስረጃ አላገኘሁም’ በማለት መጥፎ ስም ቢሰጣት 15 የልጅቷ አባትና እናት ድንግልናዋን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው በከተማዋ በር ወደሚገኙት ሽማግሌዎች ይምጡ። 16 የልጅቷም አባት ሽማግሌዎቹን እንዲህ ይበላቸው፦ ‘ልጄን ለዚህ ሰው ድሬለት ነበር፤ እሱ ግን ጠላት፤ 17 እንዲሁም “ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም” በማለት መጥፎ ምግባር እንዳላት አድርጎ እየከሰሳት ነው። እንግዲህ የልጄ የድንግልና ማስረጃ ይኸውላችሁ።’ እነሱም ልብሱን በከተማዋ ሽማግሌዎች ፊት ይዘርጉት። 18 የዚያች ከተማ ሽማግሌዎችም+ ሰውየውን ወስደው ይቅጡት።+ 19 እነሱም 100 የብር ሰቅል* ያስከፍሉታል፤ ከዚያም ገንዘቡን ለልጅቷ አባት ይስጡት፤ ምክንያቱም ይህ ሰው የአንዲትን እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቷል፤+ እሷም ሚስቱ ሆና ትኖራለች። በሕይወት ዘመኑም ሁሉ እንዲፈታት አይፈቀድለትም።
20 “ሆኖም ክሱ እውነት ከሆነና ልጅቷ ድንግል እንደነበረች የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካልተገኘ 21 ልጅቷን ወደ አባቷ ቤት ደጃፍ ያውጧት፤ በአባቷ ቤት የፆታ ብልግና በመፈጸም በእስራኤል ውስጥ አስነዋሪ ድርጊት ስለፈጸመች+ የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት።+ በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+
22 “አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ ከሴትየዋ ጋር የተኛው ሰውም ሆነ ሴትየዋ ሁለቱም ይገደሉ።+ በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከእስራኤል መካከል አስወግድ።
23 “አንድ ሰው ለሌላ ሰው የታጨችን አንዲት ድንግል ከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእሷ ጋር ቢተኛ 24 ልጅቷ በከተማው ውስጥ ስላልጮኸች፣ ሰውየው ደግሞ የባልንጀራውን ሚስት ስላዋረደ ሁለቱንም ወደ ከተማዋ በር አውጥታችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው።+ በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።
25 “ይሁንና ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ያገኛት ሜዳ ላይ ቢሆንና በጉልበት አስገድዶ አብሯት ቢተኛ እሱ ብቻ ይገደል፤ 26 በልጅቷ ላይ ምንም አታድርግ። ልጅቷ ሞት የሚገባው ኃጢአት አልሠራችም። ይህ ጉዳይ በባልንጀራው ላይ ጥቃት ሰንዝሮ ከሚገድል* ሰው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ ነው።+ 27 ምክንያቱም ሰውየው ልጅቷን ያገኛት ሜዳ ላይ ሲሆን የታጨችው ልጅ ብትጮኽም እንኳ ማንም አልደረሰላትም።
28 “አንድ ሰው ያልታጨችን አንዲት ድንግል አግኝቶ ቢይዛትና አብሯት ቢተኛ፣ በኋላም ቢጋለጡ+ 29 ሰውየው ለልጅቷ አባት 50 የብር ሰቅል ይስጥ፤ እሷም ሚስቱ ትሆናለች።+ ስላዋረዳትም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እንዲፈታት አይፈቀድለትም።
30 “ማንም ሰው አባቱን እንዳያዋርድ* የአባቱን ሚስት አያግባ።+
23 “የዘር ፍሬው ተቀጥቅጦ የተኮላሸ ወይም ብልቱ የተቆረጠ ማንኛውም ሰው ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግባ።+
2 “ዲቃላ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግባ።+ ሌላው ቀርቶ እስከ አሥረኛ ትውልድ ድረስ ዘሮቹ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ።
3 “አሞናውያንም ሆኑ ሞዓባውያን ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ።+ ሌላው ቀርቶ እስከ አሥረኛ ትውልድ ድረስ ዘሮቻቸው ፈጽሞ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ፤ 4 ምክንያቱም እነሱ ከግብፅ ወጥታችሁ እየተጓዛችሁ በነበረበት ጊዜ ምግብና ውኃ በመስጠት አልረዷችሁም፤+ ደግሞም በሜሶጶጣሚያ በምትገኘው በጰቶር የሚኖረው የቢዖር ልጅ በለዓም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ቀጥረውት ነበር።+ 5 አምላክህ ይሖዋ ግን በለዓምን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም።+ ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ሲል እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው፤+ ይህን ያደረገው አምላክህ ይሖዋ ስለወደደህ ነው።+ 6 በዘመንህ ሁሉ መቼም ቢሆን ለእነሱ ሰላምን ወይም ብልጽግናን አትመኝ።+
“የባዕድ አገር ሰው ሆነህ በአገሩ ትኖር ስለነበር ግብፃዊውን አትጥላው።+ 8 ለእነሱ የሚወለዱላቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ ይሖዋ ጉባኤ መግባት ይችላሉ።
9 “ጠላትህን ለመውጋት ወጥተህ በምትሰፍርበት ጊዜ ከማንኛውም መጥፎ* ነገር መራቅ ይኖርብሃል።+ 10 አንድ ሰው ዘሩ በመፍሰሱ ምክንያት ቢረክስ+ ከሰፈሩ ውጭ ይውጣ፤ ወደ ሰፈሩም ተመልሶ አይግባ። 11 አመሻሹ ላይ በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ወደ ሰፈሩ ተመልሶ መግባት ይችላል።+ 12 ለመጸዳጃ የሚሆን ቦታ ከሰፈሩ ውጭ አዘጋጅ፤ አንተም መሄድ ያለብህ ወደዚያ ነው። 13 ከመሣሪያዎችህም ጋር መቆፈሪያ ያዝ። ውጭ በምትጸዳዳበትም ጊዜ በመቆፈሪያው ጉድጓድ ቆፍር፤ ከዚያም በዓይነ ምድርህ ላይ አፈሩን መልስበት። 14 ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሊታደግህና ጠላቶችህን በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈሩ ውስጥ ይዘዋወራል፤+ በመሆኑም ነውር የሆነ ምንም ነገር እንዳያይብህና ከአንተ ጋር መሄዱን እንዳይተው ሰፈርህ ቅዱስ መሆን አለበት።+
15 “አንድ ባሪያ ከጌታው አምልጦ ወደ አንተ ቢመጣ መልሰህ ለጌታው አትስጠው። 16 ከከተሞችህ መካከል በመረጠውና ደስ ባለው ቦታ አብሮህ ሊኖር ይችላል። በደል አትፈጽምበት።+
17 “ከእስራኤል ሴቶች ልጆች መካከል የትኛዋም የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ አትሁን፤+ ከእስራኤል ወንዶች ልጆችም መካከል የትኛውም የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ አይሁን።+ 18 ለሴት ዝሙት አዳሪ የተከፈለን ዋጋም ሆነ ለወንድ ዝሙት አዳሪ* የተከፈለን ዋጋ* አንድን ስእለት ለመፈጸም ስትል ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አታምጣ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሁለቱንም ይጸየፋቸዋል።
19 “ወንድምህን ወለድ አታስከፍለው፤+ ከገንዘብም ሆነ ከእህል ወይም ወለድ ሊያስከፍል ከሚችል ከማንኛውም ነገር ወለድ አታስከፍለው። 20 ከባዕድ አገር ሰው ወለድ መጠየቅ ትችላለህ፤+ ሆኖም አምላክህ ይሖዋ ገብተህ በምትወርሳት ምድር በሥራህ ሁሉ እንዲባርክህ+ ወንድምህን ወለድ አታስከፍለው።+
21 “ለአምላክህ ለይሖዋ ስእለት ከተሳልክ+ ለመፈጸም አትዘግይ።+ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በእርግጥ ከአንተ ይፈልገዋል፤ አለዚያ ኃጢአት ይሆንብሃል።+ 22 ሳትሳል ከቀረህ ግን ኃጢአት አይሆንብህም።+ 23 ከአፍህ የወጣውን ቃል ጠብቅ፤+ ለአምላክህ ለይሖዋ የፈቃደኝነት መባ አድርገህ ለማቅረብ በገዛ አንደበትህ የተሳልከውን ፈጽም።+
24 “ወደ ባልንጀራህ የወይን እርሻ ከገባህ እስክትጠግብ* ድረስ ወይን መብላት ትችላለህ፤ በዕቃህ ግን ምንም ይዘህ አትሂድ።+
25 “ወደ ባልንጀራህ የእህል ማሳ ከገባህ እሸት ቀጥፈህ መብላት ትችላለህ፤ ሆኖም የባልንጀራህን እህል በማጭድ ማጨድ የለብህም።+
24 “አንድ ሰው አንዲት ሴት ቢያገባ ሆኖም ነውር የሆነ ነገር አግኝቶባት ቅር ቢሰኝ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት+ ከቤቱ ያሰናብታት።+ 2 እሷም ከእሱ ቤት ከወጣች በኋላ የሌላ ሰው ሚስት መሆን ትችላለች።+ 3 በኋላ ያገባትም ሰው ቢጠላትና የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ቢያሰናብታት ወይም አግብቷት የነበረው ሁለተኛው ሰው ቢሞት 4 ከቤቱ አሰናብቷት የነበረው የመጀመሪያው ባለቤቷ ከረከሰች በኋላ እንደገና ሚስቱ አድርጎ እንዲወስዳት አይፈቀድለትም፤ ምክንያቱም ይህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ።
5 “አንድ ሰው አዲስ ሙሽራ ከሆነ በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የለበትም፤ ወይም ምንም ዓይነት ሌላ ሥራ ሊሰጠው አይገባም። ለአንድ ዓመት ያህል ከምንም ነገር ነፃ ሆኖ ይቆይ፤ በቤቱም ተቀምጦ ሚስቱን ያስደስታት።+
6 “ማንም ሰው ወፍጮን ወይም መጅን የብድር መያዣ አድርጎ መውሰድ የለበትም፤ ምክንያቱም የሰውየውን መተዳደሪያ* መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆንበታል።+
7 “አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ መካከል አንዱን አፍኖ በመውሰድ በደል ሲፈጽምበትና ሲሸጠው+ ቢገኝ አፍኖ የወሰደው ሰው ይገደል።+ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+
8 “የሥጋ ደዌ* ቢከሰት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጧችሁን መመሪያዎች ሁሉ በጥንቃቄ ተከተሉ።+ እኔ የሰጠኋቸውንም ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽሙ። 9 ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ መንገድ ላይ ሳላችሁ አምላካችሁ ይሖዋ በሚርያም ላይ ያደረገውን አስታውሱ።+
10 “ለባልንጀራህ ማንኛውንም ነገር ብታበድር+ መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ነገር ለመውሰድ ወደ ቤቱ አትግባ። 11 ውጭ ቆመህ ጠብቅ፤ ያበደርከውም ሰው መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ነገር ውጭ ድረስ ያምጣልህ። 12 ሰውየው ከተቸገረ መያዣ አድርጎ የሰጠህን ነገር አንተ ጋ አታሳድር።+ 13 ልክ ፀሐይ ስትጠልቅ መያዣውን ልትመልስለት ይገባል፤ እሱም ለብሶት ይተኛል፤+ ደግሞም ይባርክሃል፤ በአምላክህም በይሖዋ ፊት እንደ ጽድቅ ይቆጠርልሃል።
14 “ከወንድሞችህም ሆነ በምድርህ ይኸውም በከተሞችህ* ውስጥ ከሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች መካከል የተቸገረውንና ድሃ የሆነውን ቅጥር ሠራተኛ አታታል።+ 15 ደሞዙን በዕለቱ ስጠው፤+ ችግረኛ በመሆኑና ሕይወቱ* የተመካው በደሞዙ ላይ ስለሆነ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ስጠው። አለዚያ በአንተ የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻል፤ አንተም በኃጢአት ትጠየቃለህ።+
16 “አባቶች ልጆቻቸው በሠሩት ነገር መገደል የለባቸውም፤ ልጆችም አባቶቻቸው በሠሩት ነገር መገደል የለባቸውም።+ አንድ ሰው መገደል ያለበት በገዛ ኃጢአቱ ብቻ ነው።+
17 “የባዕድ አገሩን ሰው ወይም አባት የሌለውን* ልጅ ፍርድ አታዛባ፤+ የመበለቲቱን ልብስ የብድር መያዣ አድርገህ አትውሰድ።+ 18 አንተም በግብፅ ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ ከዚያ እንደተቤዠህ አስታውስ።+ እኔም ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው።
19 “በማሳህ ላይ ያለውን እህል በምታጭድበት ጊዜ በማሳው ላይ ነዶ ብትረሳ ያን ለመውሰድ አትመለስ። አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ+ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ እንዲሆን እዚያው ተወው።+
20 “የወይራ ዛፍህን በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ሙልጭ አድርገህ አታራግፈው። የቀረው ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ ይሁን።+
21 “ከወይን እርሻህ ላይ የወይን ፍሬህን በምትሰበስብበት ጊዜ ተመልሰህ ቃርሚያውን አትልቀም። ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ መተው አለበት። 22 አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክ አስታውስ። እኔም ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው።
25 “በሰዎች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ሰዎቹ ዳኞች ፊት መቅረብ ይችላሉ፤+ እነሱም ይዳኟቸዋል፤ ጻድቅ የሆነውን ንጹሕ፣ ጥፋተኛ የሆነውን ደግሞ በደለኛ ይሉታል።+ 2 ጥፋተኛው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ+ ዳኛው መሬት ላይ እንዲያስተኙትና እሱ ባለበት እንዲገረፍ ያደርጋል። የግርፋቱም ቁጥር ከሠራው ጥፋት ጋር የሚመጣጠን ይሁን። 3 እስከ 40 ግርፋት ሊገርፈው ይችላል፤+ ከዚያ ማስበለጥ ግን የለበትም። ከዚህ የበለጠ ብዙ ግርፋት ከገረፈው ግን ወንድምህ በፊትህ ይዋረዳል።
4 “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር።+
5 “ወንድማማቾች አንድ ላይ ሲኖሩ ቆይተው ከመካከላቸው አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት የሟቹ ሚስት ከቤተሰቡ ውጭ የሆነ ሰው ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ወደ እሷ በመሄድ ሚስቱ አድርጎ ይውሰዳት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።+ 6 መጀመሪያ የምትወልደው ልጅ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራል፤+ ይህ የሚሆነው የሟቹ ስም ከእስራኤል መካከል እንዳይጠፋ ነው።+
7 “ሰውየው የሟች ወንድሙን ሚስት ለማግባት ፈቃደኛ ካልሆነ መበለት የሆነችው ሴት በከተማዋ በር ወደሚገኙት ሽማግሌዎች ሄዳ ‘የባሌ ወንድም የወንድሙ ስም ከእስራኤል መካከል እንዳይጠፋ ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነም። የዋርሳነት ግዴታውን ሊፈጽምልኝ አልተስማማም’ ትበላቸው። 8 የከተማዋ ሽማግሌዎችም ጠርተው ያናግሩት። እሱም ‘እኔ እሷን ማግባት አልፈልግም’ ብሎ በሐሳቡ ከጸና 9 የወንድሙ ሚስት በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እሱ ቀርባ ጫማውን ከእግሩ ላይ ታውልቅ፤+ ከዚያም ፊቱ ላይ ትትፋበትና ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ የሚደረግበት እንዲህ ነው’ ትበል። 10 ከዚያ በኋላ የዚያ ሰው ቤተሰብ ስም* በእስራኤል ውስጥ ‘ጫማው የወለቀበት ሰው ቤት’ ይባላል።
11 “ሁለት ሰዎች ቢደባደቡና የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል ስትል እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዝ 12 እጇን ቁረጠው። ልታዝንላት አይገባም።*
13 “በከረጢትህ ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት ዓይነት የሚዛን ድንጋዮች አይኑሩህ።+ 14 በቤትህም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት ዓይነት መስፈሪያዎች* አይኑሩህ።+ 15 አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም ትክክለኛና ሐቀኛ ሚዛን እንዲሁም ትክክለኛና ሐቀኛ መስፈሪያ ይኑርህ።+ 16 ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ነገሮችን በማድረግ ፍትሕ የጎደለው ድርጊት የሚፈጽም ሰው ሁሉ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው።+
17 “ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ መንገድ ላይ ሳላችሁ አማሌቃውያን ያደረጉባችሁን ነገር አስታውሱ፤+ 18 በጉዞ ላይ ሳለህ ደክመህና ዝለህ በነበረበት ጊዜ አግኝተውህ ከኋላ ከኋላህ እያዘገሙ በነበሩት ሁሉ ላይ እንዴት ጥቃት እንደሰነዘሩ አስታውስ። አምላክንም አልፈሩም። 19 አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ላይ አምላክህ ይሖዋ በዙሪያህ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ በሚያሳርፍህ ጊዜ+ አማሌቃውያንን ከሰማይ በታች ጨርሶ እንዳይታወሱ አድርገህ ጠራርገህ አጥፋቸው።+ ይህን አትርሳ።
26 “አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር ገብተህ ስትወርስና በዚያ መኖር ስትጀምር 2 አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ይኸውም ምድሪቱ ከምታፈራው ፍሬ ሁሉ በኩር የሆነውን ወስደህ በቅርጫት ውስጥ በማድረግ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።+ 3 በወቅቱ ወደሚያገለግለው ካህን ሄደህ ‘ይሖዋ ለእኛ ለመስጠት ለአባቶቻችን ወደማለላቸው ምድር መግባቴን ዛሬ ለአምላክህ ለይሖዋ አሳውቃለሁ’ በለው።+
4 “ከዚያም ካህኑ ቅርጫቱን ከእጅህ ላይ ወስዶ በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ፊት ያስቀምጠዋል። 5 አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘አባቴ ዘላን* አራማዊ+ ነበር፤ እሱም ወደ ግብፅ ወርዶ+ በቁጥር አነስተኛ ከሆነው ቤተሰቡ+ ጋር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ መኖር ጀመረ። ሆኖም በዚያ ሲኖር ኃያልና ቁጥሩ የበዛ ታላቅ ብሔር ሆነ።+ 6 ግብፃውያንም ክፉኛ ያንገላቱንና ይጨቁኑን እንዲሁም በላያችን ላይ ከባድ የባርነት ቀንበር ይጭኑብን ነበር።+ 7 እኛም ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ ይሖዋ ጮኽን፤ ይሖዋም ጩኸታችንን ሰማ፤ ጉስቁልናችንን፣ መከራችንንና የደረሰብንን ጭቆናም ተመለከተ።+ 8 በመጨረሻም ይሖዋ በኃያል እጅና በተዘረጋ ክንድ፣+ አስፈሪ ነገሮችን በማድረግ እንዲሁም ድንቅ ምልክቶችን በማሳየትና ተአምራትን በመፈጸም ከግብፅ አወጣን።+ 9 ከዚያም ወደዚህ ስፍራ አምጥቶ ይህችን ምድር ይኸውም ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ሰጠን።+ 10 ይኸው አሁን ይሖዋ የሰጠኝ ምድር ካፈራችው ፍሬ በኩር የሆነውን አምጥቻለሁ።’+
“ይህን በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስቀምጠው፤ አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት ስገድ። 11 ከዚያም አንተ፣ ሌዋዊውና በመካከልህ የሚኖረው የባዕድ አገር ሰው አምላክህ ይሖዋ ለአንተና ለቤተሰብህ በሰጠው መልካም ነገር ሁሉ ትደሰታላችሁ።+
12 “የአሥራት ዓመት በሆነው በሦስተኛው ዓመት የምርትህን አንድ አሥረኛ አሥራት+ እንዲሆን ለይተህ ካስቀመጥክ በኋላ ለሌዋዊው፣ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው* ልጅና ለመበለቲቱ ትሰጣለህ፤ እነሱም በከተሞችህ* ውስጥ እስኪጠግቡ ድረስ ይበሉታል።+ 13 ከዚያም በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንዲህ ትላለህ፦ ‘በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ቅዱስ የሆነውን ነገር ከቤት አውጥቼ ለሌዋዊው፣ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ+ ሰጥቻለሁ። ትእዛዛትህን አልጣስኩም ወይም ችላ አላልኩም። 14 ሐዘን ላይ በተቀመጥኩበት ጊዜ ከእሱ አልበላሁም፤ ወይም ረክሼ ባለሁበት ጊዜ ከእሱ ላይ ምንም ነገር አላነሳሁም፤ አሊያም ለሞተ ሰው ከእሱ ላይ ምንም ነገር አልሰጠሁም። የአምላኬን የይሖዋን ቃል ታዝዣለሁ፤ ያዘዝከኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ። 15 እንግዲህ አሁን ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማያት ሆነህ ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በማልክላቸው መሠረት+ የሰጠኸንን ምድር ይኸውም ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ባርክ።’+
16 “አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እንድትጠብቅ ዛሬ ያዝሃል። አንተም በሙሉ ልብህና+ በሙሉ ነፍስህ* ፈጽማቸው፤ ጠብቃቸውም። 17 ይሖዋ በመንገዶቹ ከሄድክ እንዲሁም ሥርዓቶቹን፣+ ትእዛዛቱንና+ ድንጋጌዎቹን+ ከጠበቅክና ቃሉን ከሰማህ አምላክህ እንደሚሆን ዛሬ ነግሮሃል። 18 አንተም ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት ሕዝቡ ማለትም ልዩ ንብረቱ*+ እንደምትሆንና ትእዛዛቱን በሙሉ እንደምትጠብቅ የተናገርከውን ቃል በዛሬው ዕለት ሰምቷል፤ 19 አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ+ ሆነህ ስትገኝ እሱ ደግሞ በገባው ቃል መሠረት ውዳሴ፣ ዝናና ክብር በማጎናጸፍ፣ ከፈጠራቸው ሌሎች ብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።”+
27 ከዚያም ሙሴ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “እኔ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ። 2 አምላካችሁ ይሖዋ ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በምትሻገሩበት ቀን ትላልቅ ድንጋዮችን አቁማችሁ ለስኗቸው።*+ 3 ከዚያም የአባቶችህ አምላክ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት አምላክህ ይሖዋ ወደሚሰጥህ ምድር ይኸውም ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ ለመግባት በምትሻገርበት ጊዜ የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ ጻፍባቸው። 4 ዮርዳኖስን ስትሻገሩ ዛሬ በሰጠኋችሁ ትእዛዝ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በኤባል ተራራ+ ላይ አቁሟቸው፤ ደግሞም ለስኗቸው።* 5 በዚያም ለአምላክህ ለይሖዋ መሠዊያ ይኸውም የድንጋይ መሠዊያ ሥራ። ድንጋዮቹንም የብረት መሣሪያ አታስነካቸው።+ 6 የአምላክህን የይሖዋን መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥራ፤ በላዩም ላይ ለአምላክህ ለይሖዋ የሚቃጠሉ መባዎችን አቅርብ። 7 የኅብረት መሥዋዕቶችንም አቅርብ፤+ መሥዋዕቶቹንም እዚያው ብላቸው፤+ አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት ደስ ይልሃል።+ 8 በድንጋዮቹም ላይ የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በግልጽ ጻፍባቸው።”+
9 ከዚያም ሙሴና ሌዋውያኑ ካህናት እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አሏቸው፦ “እስራኤል ሆይ፣ ጸጥ ብለህ አዳምጥ። በዛሬው ቀን አንተ የአምላክህ የይሖዋ ሕዝብ ሆነሃል።+ 10 የአምላክህን የይሖዋን ቃል ስማ፤ እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ሥርዓቶች ፈጽም።”+
11 ሙሴም በዚያ ቀን ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፦ 12 “ዮርዳኖስን በምትሻገሩበት ጊዜ በገሪዛን ተራራ+ ላይ ቆመው ሕዝቡን የሚባርኩት ነገዶች ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዮሴፍ እና ቢንያም ናቸው። 13 እርግማኑን ለማሰማት በኤባል ተራራ+ ላይ የሚቆሙት ደግሞ ሮቤል፣ ጋድ፣ አሴር፣ ዛብሎን፣ ዳን እና ንፍታሌም ናቸው። 14 ሌዋውያኑም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ለእያንዳንዱ እስራኤላዊ እንዲህ ብለው ይናገራሉ፦+
15 “‘ይሖዋ የሚጠላውን አስጸያፊ ነገር+ ይኸውም የአንድ የእጅ ጥበብ ባለሙያ* የእጅ ሥራ ውጤት የሆነውን የተቀረጸ ምስል+ ወይም ከብረት የተሠራ ሐውልት*+ የሚሠራና በስውር የሚያስቀምጥ ሰው የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’* ብሎ ይመልሳል።)
16 “‘አባቱን ወይም እናቱን የሚንቅ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
17 “‘የጎረቤቱን የወሰን ምልክት የሚገፋ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
18 “‘ዓይነ ስውሩን መንገድ የሚያሳስት የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
19 “‘የባዕድ አገሩን ሰው፣ አባት የሌለውን* ልጅ ወይም የመበለቲቱን ፍርድ የሚያዛባ+ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
20 “‘ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ አባቱን ስላዋረደ* የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
21 “‘ከማንኛውም ዓይነት እንስሳ ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
22 “‘የአባቱ ልጅ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው ከእህቱ ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
23 “‘ከሚስቱ እናት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
24 “‘ጎረቤቱን አድብቶ በመጠበቅ የሚገድል የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
25 “‘ንጹሑን ሰው* ለመግደል ሲል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
26 “‘የዚህን ሕግ ቃል ተግባራዊ በማድረግ የማይጠብቅ ሰው የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
28 “እኔ ዛሬ የማዝህን የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ሁሉ በጥንቃቄ በመፈጸም ቃሉን በእርግጥ ብትሰማ አምላክህ ይሖዋ በምድር ላይ ካሉ ብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።+ 2 የአምላክህን የይሖዋን ቃል ከሰማህ እነዚህ ሁሉ በረከቶች ይወርዱልሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል፦+
3 “በከተማ የተባረክ ትሆናለህ፤ በእርሻም የተባረክ ትሆናለህ።+
4 “የሆድህ ፍሬ፣+ የመሬትህ ፍሬ፣ የቤት እንስሳህ ግልገል፣ ጥጃህና የበግህ ግልገል የተባረከ ይሆናል።+
6 “ስትገባ የተባረክ ትሆናለህ፤ ስትወጣም የተባረክ ትሆናለህ።
7 “ይሖዋ በአንተ ላይ የሚነሱ ጠላቶችህ በፊትህ ድል እንዲሆኑ ያደርጋል።+ ከአንድ አቅጣጫ ጥቃት ይሰነዝሩብሃል፤ ሆኖም በሰባት አቅጣጫ ከፊትህ ይሸሻሉ።+ 8 ይሖዋ በጎተራህና በምታከናውነው ሥራ ሁሉ ላይ በረከት እንዲፈስልህ ያዛል፤+ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል። 9 የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ከጠበቅክና በመንገዶቹ ከሄድክ ይሖዋ በማለልህ መሠረት+ ለእሱ ቅዱስ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል።+ 10 የምድር ሕዝቦች ሁሉ የይሖዋ ስም በአንተ አማካኝነት እንደሚጠራ ያያሉ፤+ እነሱም ይፈሩሃል።+
11 “ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር+ ላይ ይሖዋ የሆድህ ፍሬ እንዲበዛ፣ የቤት እንስሶችህ እንዲረቡና መሬትህ ፍሬያማ እንዲሆን+ በማድረግ ያበለጽግሃል። 12 ይሖዋ በምድርህ ላይ በወቅቱ ዝናብን ለማዝነብና የእጅህን ሥራ ሁሉ ለመባረክ ሲል መልካም የሆነውን ጎተራውን ይኸውም ሰማይን ይከፍትልሃል።+ አንተም ለብዙ ብሔራት ታበድራለህ፤ አንተ ግን አትበደርም።+ 13 ይሖዋ ራስ እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ትጠብቃቸውና ትፈጽማቸው ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝህን የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ከፈጸምክ መቼም ቢሆን ከላይ+ እንጂ ከታች አትሆንም። 14 ሌሎች አማልክትን ለማገልገል+ ብላችሁ እነሱን በመከተል እኔ ዛሬ ከምሰጣችሁ ትእዛዛት ሁሉ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበሉ።+
15 “እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች በሙሉ በጥንቃቄ የማትፈጽምና የአምላክህን የይሖዋን ቃል የማትሰማ ከሆነ ግን እነዚህ ሁሉ እርግማኖች ይወርዱብሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል፦+
16 “በከተማ የተረገምክ ትሆናለህ፤ በእርሻም የተረገምክ ትሆናለህ።+
18 “የሆድህ ፍሬ፣+ የመሬትህ ፍሬ፣ ጥጃህና የበግህ ግልገል የተረገመ ይሆናል።+
19 “ስትገባ የተረገምክ ትሆናለህ፤ ስትወጣም የተረገምክ ትሆናለህ።
20 “ይሖዋ በፈጸምካቸው መጥፎ ድርጊቶችና እኔን በመተውህ የተነሳ ፈጥነህ እስክትደመሰስ እንዲሁም እስክትጠፋ ድረስ፣ በምታከናውነው በማንኛውም ሥራ ላይ እርግማንን፣ ግራ መጋባትንና ቅጣትን ያመጣብሃል።+ 21 ይሖዋ ከምትወርሳት ምድር ላይ ጨርሶ እስኪያጠፋህ ድረስ በሽታ እንዲጣበቅብህ ያደርጋል።+ 22 ይሖዋ በሳንባ በሽታ፣ በኃይለኛ ትኩሳት፣+ ሰውነትን በሚያስቆጣ በሽታ፣ በሚያነድ ትኩሳት፣ በሰይፍ፣+ ሰብል በሚለበልብ ነፋስና በዋግ+ ይመታሃል፤ እነሱም እስክትጠፋ ድረስ ያሳድዱሃል። 23 ከራስህ በላይ ያለው ሰማይ መዳብ፣ ከበታችህ ያለውም ምድር ብረት ይሆንብሃል።+ 24 ይሖዋ በምድርህ ላይ የሚዘንበውን ዝናብ ትቢያና አቧራ ያደርገዋል፤ ይህም እስክትጠፋ ድረስ ከሰማይ ይወርድብሃል። 25 ይሖዋ በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል።+ በአንድ አቅጣጫ ጥቃት ትሰነዝርባቸዋለህ፤ ሆኖም በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ የምድርም መንግሥታት ሁሉ በአንተ ላይ የደረሰውን ሲያዩ በፍርሃት ይርዳሉ።+ 26 ሬሳህ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ምግብ ይሆናል፤ አስፈራርቶ የሚያባርራቸውም አይኖርም።+
27 “ይሖዋ ፈውስ ልታገኝ በማትችልበት የግብፅ እባጭ፣ ኪንታሮት፣ ችፌና ሽፍታ ይመታሃል። 28 ይሖዋ በእብደት፣ በዕውርነትና+ በግራ መጋባት ይመታሃል። 29 ጨለማ የዋጠው ዓይነ ስውር በዳበሳ እንደሚሄድ ሁሉ አንተም በእኩለ ቀን በዳበሳ ትሄዳለህ፤+ የምታደርገው ነገር ሁሉ አይሳካልህም፤ ሁልጊዜ ትጭበረበራለህ፤ እንዲሁም ትዘረፋለህ፤ የሚያስጥልህም የለም።+ 30 አንዲትን ሴት ታጫለህ፤ ሆኖም ሌላ ሰው ይደፍራታል። ቤት ትሠራለህ፤ ሆኖም አትኖርበትም።+ ወይን ትተክላለህ፤ ግን አትበላውም።+ 31 በሬህ ዓይንህ እያየ ይታረዳል፤ ሆኖም ከእሱ ላይ ምንም አትቀምስም። አህያህም ከፊትህ ተዘርፎ ይወሰዳል፤ ሆኖም አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚደርስልህ ግን የለም። 32 ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ዓይንህ እያየ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤+ አንተም ሁልጊዜ የእነሱን መመለስ ትናፍቃለህ፤ ሆኖም እጆችህ ምንም ኃይል አይኖራቸውም። 33 የምድርህን ፍሬና ያመረትከውን ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል፤+ አንተም ሁልጊዜ ትጭበረበራለህ፤ ደግሞም ትረገጣለህ። 34 ዓይንህ የሚያየውም ነገር ያሳብድሃል።
35 “ይሖዋ በሚያሠቃይና ሊድን በማይችል እባጭ ጉልበቶችህንና እግሮችህን ይመታል፤ እባጩም ከእግር ጥፍርህ እስከ ራስ ቅልህ ድረስ ይወርስሃል። 36 ይሖዋ አንተንና በላይህ ያነገሥከውን ንጉሥ፣ አንተም ሆንክ አባቶችህ ወደማታውቁት ብሔር ይወስዳችኋል፤+ እዚያም ሌሎች አማልክትን ይኸውም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክትን ታገለግላለህ።+ 37 ይሖዋ በሚያስገባህ ሕዝብ ሁሉ መካከል ማስፈራሪያ፣ መቀለጃና* መሳለቂያ ትሆናለህ።+
38 “ወደ እርሻህ ብዙ ዘር ይዘህ ትወጣለህ፤ የምትሰበስበው ግን ጥቂት ይሆናል፤+ ምክንያቱም አንበጦች ያወድሙታል። 39 ወይን ትተክላለህ፤ ታለማለህም፤ ይሁንና ምንም የወይን ጠጅ አትጠጣም፤ እንዲሁም አንዳች አትሰበስብም፤+ ምክንያቱም ትል ይበላዋል። 40 በግዛትህ ሁሉ የወይራ ዛፍ ይኖርሃል፤ ሰውነትህን የምትቀባው ዘይት ግን አይኖርህም፤ ምክንያቱም የወይራ ፍሬዎችህ ይረግፋሉ። 41 ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ትወልዳለህ፤ ሆኖም በምርኮ ስለሚወሰዱ የአንተ አይሆኑም።+ 42 ዛፎችህንና የምድርህን ፍሬ ሁሉ የሚርመሰመሱ ነፍሳት ይወሩታል። 43 አንተ ዝቅ ዝቅ እያልክ ስትሄድ በመካከልህ የሚኖረው የባዕድ አገር ሰው ግን በአንተ ላይ ከፍ ከፍ እያለ ይሄዳል። 44 እሱ ያበድርሃል እንጂ አንተ አታበድረውም።+ እሱ ራስ ይሆናል፤ አንተ ግን ጅራት ትሆናለህ።+
45 “አምላክህ ይሖዋ ያዘዘህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች ባለመጠበቅ ቃሉን ስላልሰማህ እነዚህ እርግማኖች ሁሉ+ እስክትጠፋ ድረስ ይወርዱብሃል፤+ ያሳድዱሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል።+ 46 እነሱም በአንተና በልጆችህ ላይ ለዘላለም ምልክትና ማስጠንቀቂያ ይሆናሉ፤+ 47 ምክንያቱም ሁሉም ነገር ተትረፍርፎልህ ሳለ አምላክህን ይሖዋን በደስታና በሐሴት አላገለገልከውም።+ 48 ይሖዋ ጠላቶችህን በአንተ ላይ ያስነሳቸዋል፤ አንተም ተርበህ፣+ ተጠምተህ፣ ተራቁተህና ሁሉን ነገር አጥተህ እያለ ታገለግላቸዋለህ።+ እሱም እስኪያጠፋህ ድረስ በአንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭንብሃል።
49 “ይሖዋ ቋንቋውን የማትረዳውን+ በሩቅ ያለን አንድ ብሔር ከምድር ጫፍ አስነስቶ ያመጣብሃል፤+ እሱም እንደ ንስር ተምዘግዝጎ ይወርድብሃል፤+ 50 ይህ ብሔር ለሽማግሌ የማያዝን ወይም ለወጣት የማይራራ ፊቱ የሚያስፈራ ብሔር ነው።+ 51 እስክትጠፋም ድረስ የእንስሶችህን ግልገልና የምድርህን ፍሬ ይበላሉ። አንተንም እስኪያጠፉህ ድረስ ምንም እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅም ሆነ ዘይት፣ ጥጃም ሆነ የበግ ግልገል አያስተርፉልህም።+ 52 የምትተማመንባቸው ረጃጅምና የተመሸጉ ቅጥሮችህ እስኪወድቁም ድረስ በከተሞችህ* ውስጥ እንዳለህ ዘግተውብህ ይከቡሃል። አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህም ምድር ሁሉ ላይ በከተሞችህ ውስጥ እንዳለህ ይከቡሃል።+ 53 ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በአንተ ላይ ከሚያደርሰው ሥቃይ የተነሳ አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን የሆድህን ፍሬ ይኸውም የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።+
54 “ሌላው ቀርቶ በመካከልህ ያለ በምቾትና በቅምጥልነት ይኖር የነበረ ሰው እንኳ በወንድሙ፣ በሚወዳት ሚስቱ ወይም በተረፉት ልጆቹ ላይ ይጨክናል፤ 55 ከሚበላው የልጆቹ ሥጋ ላይ ምንም ነገር አያካፍላቸውም፤ ምክንያቱም ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በከተሞችህ ላይ ከሚያመጣው ሥቃይ የተነሳ የሚተርፈው ምንም ነገር አይኖረውም።+ 56 ከቅምጥልነቷ የተነሳ መሬት ለመርገጥ እንኳ ትጸየፍ የነበረች+ በመካከልህ ያለች ቅምጥልና በምቾት የምትኖር ሴትም በምትወደው ባሏ፣ በወንድ ልጇ ወይም በሴት ልጇ ላይ ትጨክናለች፤ 57 ሌላው ቀርቶ ከወሊድ በኋላ ከእግሮቿ መካከል በሚወጣው ነገር ሁሉና በምትወልዳቸው ልጆች ላይ ትጨክናለች፤ ምክንያቱም ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በከተሞችህ ላይ ከሚያመጣው ሥቃይ የተነሳ በድብቅ ትበላቸዋለች።
58 “በዚህ መጽሐፍ ላይ የተጻፈውን የዚህን ሕግ+ ቃላት ሁሉ በጥንቃቄ የማትጠብቅ እንዲሁም ክብራማና አስፈሪ የሆነውን የአምላክህን የይሖዋን ስም+ የማትፈራ ከሆነ 59 ይሖዋ በአንተና በልጆችህ ላይ ከባድ የሆኑ መቅሰፍቶችን ይኸውም ታላቅና ለረጅም ጊዜ የሚዘልቁ መቅሰፍቶችን እንዲሁም አስከፊና ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ በሽታዎችን+ ያመጣል። 60 ትፈራቸው የነበሩትን የግብፅ በሽታዎች ሁሉ መልሶ ያመጣብሃል፤ እነሱም በአንተ ላይ ይጣበቃሉ። 61 በተጨማሪም ይሖዋ በዚህ የሕግ መጽሐፍ ውስጥ ያልተጻፉ በሽታዎችን ወይም መቅሰፍቶችን ሁሉ እስክትጠፋ ድረስ በአንተ ላይ ያመጣብሃል። 62 ብዛታችሁ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት+ የነበረ ቢሆንም የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ስላልሰማችሁ የምትቀሩት በጣም ጥቂት ትሆናላችሁ።+
63 “ይሖዋ እናንተን በማበልጸግና በማብዛት እጅግ ይደሰት እንደነበረው ሁሉ ይሖዋ እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስም እጅግ ይደሰታል፤ ገብታችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ።
64 “ይሖዋ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ በብሔራት ሁሉ መካከል ይበትንሃል፤+ እዚያም አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክት ታገለግላለህ።+ 65 በእነዚያም ብሔራት መካከል ሰላም አይኖርህም፤+ ወይም ለእግርህ ማሳረፊያ የሚሆን ቦታ አታገኝም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ በዚያ ልብህ እንዲሸበር፣+ ዓይንህ እንዲፈዝና በተስፋ መቁረጥ እንድትዋጥ ያደርጋል።*+ 66 ሕይወትህ ለከፍተኛ አደጋ ይጋለጣል፤ ሌሊትና ቀንም በፍርሃት ትዋጣለህ፤ ለሕይወትህም ዋስትና ታጣለህ። 67 በልብህ ውስጥ ካለው ፍርሃትና በዓይንህ ከምታየው ነገር የተነሳ ጠዋት ላይ ‘ምነው በመሸ!’ ትላለህ፤ ምሽት ላይ ደግሞ ‘ምነው በነጋ!’ ትላለህ። 68 ‘ዳግመኛ አታያትም’ ባልኩህ መንገድ ይሖዋ ወደ ግብፅ በመርከቦች ይመልስሃል፤ በዚያም ራሳችሁን ለጠላቶቻችሁ ወንድ ባሪያዎችና ሴት ባሪያዎች አድርጋችሁ ለመሸጥ ትገደዳላችሁ፤ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።”
29 ይሖዋ በኮሬብ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ ሙሴ በሞዓብ ምድር ከእነሱ ጋር እንዲገባ ያዘዘው ቃል ኪዳን ቃላት እነዚህ ናቸው።+
2 ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን በሙሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ በግብፅ ምድር በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ እንዲሁም በመላ ምድሩ ላይ ያደረገውን ነገር ሁሉ በገዛ ዓይናችሁ ተመልክታችኋል፤+ 3 ደግሞም እነዚያን ታላላቅ የፍርድ እርምጃዎች፣* ድንቅ ምልክቶችና ተአምራት+ በዓይናችሁ አይታችኋል። 4 ሆኖም ይሖዋ እስከ ዛሬ ድረስ የሚያስተውል ልብ፣ የሚያይ ዓይንና የሚሰማ ጆሮ አልሰጣችሁም።+ 5 ‘በምድረ በዳ ለ40 ዓመታት+ በመራኋችሁ ጊዜ ልብሳችሁ ላያችሁ ላይ አላለቀም፤ ጫማችሁም እግራችሁ ላይ አላለቀም።+ 6 እኔ አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን ታውቁ ዘንድ ዳቦ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም።’ 7 በኋላም ወደዚህ ስፍራ መጣችሁ፤ የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን+ እና የባሳን ንጉሥ ኦግ+ ሊወጉን ወጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው።+ 8 ከዚያም ምድራቸውን ወስደን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠናቸው።+ 9 በመሆኑም የምታደርጉት ነገር ሁሉ መልካም እንዲሆንላችሁ የዚህን ቃል ኪዳን ቃላት ጠብቁ፤ ደግሞም ታዘዙ።+
10 “እናንተ ሁላችሁ ይኸውም የየነገዶቻችሁ መሪዎች፣ ሽማግሌዎቻችሁ፣ አለቆቻችሁና በእስራኤል ያለ ወንድ ሁሉ በዛሬው ዕለት በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ቆማችኋል፤ 11 እንዲሁም ልጆቻችሁ፣ ሚስቶቻችሁና+ ከእንጨት ለቃሚዎቻችሁ አንስቶ እስከ ውኃ ቀጂዎቻችሁ ድረስ፣ በሰፈራችሁ የሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች+ ሁሉ በፊቱ ቆመዋል። 12 አሁን እዚህ የተገኘኸው አምላክህ ይሖዋ በዛሬው ዕለት ከአንተ ጋር ወደሚገባው ይኸውም በመሐላ ወደሚያጸናው ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቃል ኪዳን እንድትገባ ነው፤+ 13 ይህም ለአንተ ቃል በገባውና ለአባቶችህ ለአብርሃም፣+ ለይስሐቅና+ ለያዕቆብ+ በማለላቸው መሠረት በዛሬው ዕለት አንተን ሕዝቡ አድርጎ+ ያጸናህ እንዲሁም አምላክህ ይሆን ዘንድ+ ነው።
14 “እኔ አሁን ይህን ቃል ኪዳን የምገባውም ሆነ ይህን መሐላ የምምለው ለእናንተ ብቻ አይደለም፤ 15 ከዚህ ይልቅ በዛሬው ዕለት በይሖዋ ፊት አብረውን ለቆሙትና በዚህ ዕለት ከእኛ ጋር ለሌሉት ጭምር ነው። 16 (በግብፅ እንዴት እንኖር እንደነበረና በጉዟችንም ላይ የተለያዩ ብሔራትን እንዴት አቋርጠን እንዳለፍን በሚገባ ታውቃላችሁና።+ 17 በመካከላቸው የነበሩትን የሚያስጠሉ ነገሮች እንዲሁም ከእንጨት፣ ከድንጋይ፣ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውንም*+ አይታችኋል።) 18 የእነዚያን ብሔራት አማልክት ለማገልገል ከአምላካችን ከይሖዋ ልቡ የሚሸፍት+ ወንድ ወይም ሴት ወይም ቤተሰብ አሊያም ነገድ በዛሬው ዕለት በመካከላችሁ እንዳይገኝ እንዲሁም መርዛማና መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ።+
19 “አንድ ሰው ይህን የመሐላ ቃል ቢሰማና በመንገዱ ላይ ያገኘውን ሁሉ* ጠራርጎ ለማጥፋት በማሰብ ‘እንዳሻኝ ብሆን እንኳ በሰላም እኖራለሁ’ እያለ በልቡ ቢኩራራ 20 ይሖዋ ይቅር ሊለው ፈቃደኛ አይሆንም።+ ከዚህ ይልቅ የይሖዋ ታላቅ ቁጣ በዚያ ሰው ላይ ይነድዳል፤ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉት እርግማኖች በሙሉ ይወርዱበታል፤+ ይሖዋም የዚህን ሰው ስም ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል። 21 ከዚያም በዚህ የሕግ መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው በቃል ኪዳኑ እርግማን ሁሉ መሠረት ይሖዋ ከሌሎቹ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ እሱን ለጥፋት ይለየዋል።
22 “መጪው የልጆቻችሁ ትውልድና ከሩቅ ምድር የሚመጡት የባዕድ አገር ሰዎች በምድሪቱ ላይ የወረዱትን መቅሰፍቶች ይኸውም ይሖዋ በላይዋ ላይ ያመጣውን በሽታ 23 እንዲሁም ይሖዋ በቁጣውና በመዓቱ ሰዶምንና ገሞራን፣+ አድማህንና ጸቦይምን+ እንደገለባበጠ ሁሉ መላዋ ምድር እንዳይዘራባት፣ እንዳታቆጠቁጥ ወይም ምንም ዓይነት ተክል እንዳታበቅል የላከውን ድኝ፣ ጨውና እሳት ሲመለከቱ 24 እነሱም ሆኑ ሁሉም ብሔራት ‘ይሖዋ በዚህች ምድር ላይ እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው?+ ይህን ታላቅ ቁጣስ ምን አመጣው?’ ይላሉ። 25 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ከግብፅ ምድር ባወጣቸው+ ጊዜ ከእነሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን በማፍረሳቸው ነው።+ 26 ሄደውም ሌሎችን አማልክት ይኸውም የማያውቋቸውንና እሱ እንዲያመልኳቸው ያልፈቀደላቸውን* አማልክት አገለገሉ፤ ደግሞም ሰገዱላቸው።+ 27 ይሖዋም በዚህ መጽሐፍ ላይ የተጻፉትን እርግማኖች በሙሉ እስኪያመጣባት ድረስ ቁጣው በምድሪቱ ላይ ነደደ።+ 28 በመሆኑም ይሖዋ በታላቅ ቁጣውና በኃይለኛው ንዴቱ ከምድራቸው ላይ ነቅሎ+ አሁን ወዳሉበት ሌላ ምድር አፈለሳቸው።’+
29 “የተሰወሩት ነገሮች የአምላካችን የይሖዋ ናቸው፤+ የተገለጡት ነገሮች ግን በዚህ ሕግ ውስጥ ያሉትን ቃላት በሙሉ እንፈጽም ዘንድ ለዘላለም የእኛና የዘሮቻችን ናቸው።+
30 “ይህ ቃል ሁሉ ይኸውም በፊትህ ያስቀመጥኩት በረከትና እርግማን+ በአንተ ላይ በሚመጣበትና አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ባደረገህ ብሔራት ምድር+ ሆነህ ይህን ቃል ሁሉ በምታስታውስበት* ጊዜ+ 2 እንዲሁም አንተም ሆንክ ልጆችህ እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ በምትመለሱበትና ቃሉን በምትሰሙበት ጊዜ+ 3 አምላክህ ይሖዋ ተማርከው የተወሰዱብህን ይመልስልሃል፤+ ምሕረትም ያሳይሃል፤+ እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ካደረገህ ሕዝቦች ምድር ሁሉ መልሶ ይሰበስብሃል።+ 4 ሕዝብህ እስከ ሰማያት ዳርቻ ድረስ ቢበተን እንኳ አምላክህ ይሖዋ ከዚያ ይሰበስብሃል፤ ከዚያም መልሶ ያመጣሃል።+ 5 አምላክህ ይሖዋ አባቶችህ ወርሰዋት ወደነበሩት ምድር ያስገባሃል፤ አንተም ትወርሳታለህ፤ እሱም ከአባቶችህ ይበልጥ ያበለጽግሃል፤ እንዲሁም ያበዛሃል።+ 6 በሕይወትም ትኖር ዘንድ አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ* እንድትወደው+ አምላክህ ይሖዋ ልብህን እንዲሁም የልጆችህን ልብ ያነጻል።*+ 7 ከዚያም አምላክህ ይሖዋ እነዚህን እርግማኖች ሁሉ በሚጠሉህና በሚያሳድዱህ ጠላቶችህ ላይ ያመጣል።+
8 “አንተም ተመልሰህ የይሖዋን ቃል ትሰማለህ፤ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዛቱን ሁሉ ትፈጽማለህ። 9 አምላክህ ይሖዋ በአባቶችህ ደስ እንደተሰኘ+ ሁሉ ይሖዋ አንተንም በማበልጸግ ስለሚደሰት የሆድህን ፍሬ፣ እንስሶችህንና የምድርህን ፍሬ በማብዛት በእጅህ ሥራ ሁሉ እጅግ እንድትበለጽግ ያደርግሃል።+ 10 ይህም የሚሆነው የአምላክህን የይሖዋን ቃል ስለምትሰማ፣ በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዛቱንና ደንቦቹን ስለምትጠብቅ እንዲሁም በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ* ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ስለምትመለስ ነው።+
11 “እኔ ዛሬ የማዝህ ይህ ትእዛዝ ለአንተ ያን ያህል ከባድ አይደለም፤ ከአንተም የራቀ አይደለም።+ 12 ‘ሰምተን እንድንፈጽመው ወደ ሰማይ ወጥቶ ማን ያምጣልን?’ እንዳትል ትእዛዙ ያለው በሰማይ አይደለም።+ 13 ደግሞም ‘ሰምተን እንድንፈጽመው ባሕሩን ተሻግሮ ማን ያምጣልን?’ እንዳትል ትእዛዙ ያለው ከባሕሩ ማዶ አይደለም። 14 ቃሉ ትፈጽመው ዘንድ+ ለአንተ በጣም ቅርብ ነውና፤ ደግሞም በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው።+
15 “እንግዲህ እኔ ዛሬ ሕይወትንና መልካም ነገርን እንዲሁም ሞትንና መጥፎ ነገርን በፊትህ አስቀምጫለሁ።+ 16 አምላክህን ይሖዋን በመውደድ፣+ በመንገዶቹ በመሄድ እንዲሁም ትእዛዛቱን፣ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን በመጠበቅ እኔ ዛሬ የማዝህን የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ብትሰማ በሕይወት ትኖራለህ፤+ ደግሞም ትበዛለህ፤ አምላክህ ይሖዋም በምትወርሳት ምድር ውስጥ ይባርክሃል።+
17 “ሆኖም ልብህ ቢሸፍትና+ ለመስማት ፈቃደኛ ባትሆን እንዲሁም ተታለህ ለሌሎች አማልክት ብትሰግድና ብታገለግላቸው+ 18 በእርግጥ እንደምትጠፉ+ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ። ደግሞም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁ ያጥራል። 19 ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና እርግማንን በፊታችሁ እንዳስቀመጥኩ+ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምሥክሮች አድርጌ እጠራባችኋለሁ፤ እንግዲህ አንተም ሆንክ ዘሮችህ+ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤+ 20 ይህን የምታደርገው አምላክህን ይሖዋን በመውደድ፣+ ቃሉን በመስማትና ከእሱ ጋር በመጣበቅ ነው፤+ ምክንያቱም እሱ ሕይወትህ ነው፤ ይሖዋ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በማለላቸው ምድር ረጅም ዕድሜ የምትኖረውም በእሱ ነው።”+
31 ከዚያም ሙሴ ወጥቶ እነዚህን ቃላት ለመላው እስራኤል ተናገረ፤ 2 እንዲህም አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ አሁን 120 ዓመት ሆኖኛል።+ ይሖዋ ‘የዮርዳኖስን ወንዝ አትሻገርም’+ ስላለኝ ከእንግዲህ ልመራችሁ* አልችልም። 3 ከፊትህ የሚሻገረው አምላክህ ይሖዋ ነው፤ እሱ ራሱም እነዚህን ብሔራት ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ታባርራቸዋለህ።+ ልክ ይሖዋ በተናገረውም መሠረት እየመራ የሚያሻግርህ ኢያሱ ነው።+ 4 ይሖዋ የአሞራውያንን ነገሥታት ሲሖንን+ እና ኦግን+ እንዲሁም ምድራቸውን ባጠፋ ጊዜ በእነሱ ላይ እንዳደረገው ሁሉ በእነዚህም ብሔራት ላይ እንዲሁ ያደርግባቸዋል።+ 5 ይሖዋ እነሱን ድል ያደርግላችኋል፤ እናንተም እኔ በሰጠኋችሁ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት ታደርጉባቸዋላችሁ።+ 6 ደፋርና ብርቱ ሁኑ።+ ከእናንተ ጋር የሚሄደው አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው ወይም በፊታቸው አትሸበሩ።+ እሱ አይጥላችሁም ወይም አይተዋችሁም።”+
7 ከዚያም ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በመላው እስራኤል ፊት እንዲህ አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤+ ምክንያቱም ይህን ሕዝብ ይሖዋ ለአባቶቻቸው ሊሰጣቸው ወደማለላቸው ምድር የምታስገባው አንተ ነህ፤ ደግሞም ይህን ምድር ርስት አድርገህ ትሰጣቸዋለህ።+ 8 በፊትህ የሚሄደው ይሖዋ ነው፤ እሱ ምንጊዜም ከአንተ ጋር ይሆናል።+ አይጥልህም ወይም አይተውህም። አትፍራ ወይም አትሸበር።”+
9 ከዚያም ሙሴ ይህን ሕግ ጽፎ+ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ለሚሸከሙት ሌዋውያን ካህናትና ለእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ሰጣቸው። 10 ሙሴ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “በየሰባት ዓመቱ መጨረሻ፣ በዓመቱ ውስጥ ዕዳ በሚሰረዝበት+ በተወሰነው ጊዜ ላይ ማለትም የዳስ* በዓል+ ሲከበር 11 መላው እስራኤል አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በፊቱ በሚሰበሰብበት+ ጊዜ ይህን ሕግ እስራኤላውያን በሙሉ እንዲሰሙት አንብብላቸው።+ 12 ስለ አምላካችሁ ስለ ይሖዋ ይሰሙና ይማሩ እንዲሁም እሱን ይፈሩ ዘንድ ብሎም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ እንዲፈጽሙ ሕዝቡን ማለትም ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ልጆችንና* በከተሞችህ ውስጥ* የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው ሰብስብ።+ 13 ከዚያም ይህን ሕግ የማያውቁት ልጆቻቸው ይሰማሉ፤+ እንዲሁም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ አምላካችሁን ይሖዋን መፍራት ይማራሉ።”+
14 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ የምትሞትበት ጊዜ ቀርቧል።+ ኢያሱን ጥራውና መሪ አድርጌ እንድሾመው በመገናኛ ድንኳኑ ተገኙ።”*+ በመሆኑም ሙሴና ኢያሱ ሄደው በመገናኛ ድንኳኑ ተገኙ። 15 ከዚያም ይሖዋ በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ በድንኳኑ ላይ ተገለጠ፤ የደመናውም ዓምድ በድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆመ።+
16 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ መሞትህ ነው፤* ይህም ሕዝብ በሚሄድበት ምድር በዙሪያው ካሉ ባዕዳን አማልክት ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ይፈጽማል።+ እኔንም ይተዉኛል፤+ ከእነሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።+ 17 በዚያን ጊዜ ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል፤+ እኔም እተዋቸዋለሁ፤+ ሙሉ በሙሉ እስኪደመሰሱም ድረስ ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ።+ ከዚያም ብዙ መከራና ችግር ይደርስባቸዋል፤+ እነሱም ‘ይህ ሁሉ መከራ የደረሰብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደል?’+ ይላሉ። 18 ሆኖም ወደ ሌሎች አማልክት ዞር በማለት ከፈጸሙት መጥፎ ድርጊት ሁሉ የተነሳ በዚያ ቀን ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ።+
19 “እንግዲህ አሁን ይህን መዝሙር ለራሳችሁ ጻፉ፤+ ለእስራኤላውያንም አስተምሯቸው።+ ይህ መዝሙር በእስራኤል ሕዝብ ላይ ምሥክሬ ሆኖ ያገለግል ዘንድ እንዲማሩት አድርጉ።*+ 20 ምክንያቱም ለአባቶቻቸው ወደማልኩላቸው+ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ በማስገባቸው ጊዜ በልተው ሲጠግቡና ሲበለጽጉ*+ ወደ ሌሎች አማልክት ዞር ይላሉ፤ እንዲሁም እነሱን ያገለግላሉ፤ እኔንም ይንቁኛል፤ ቃል ኪዳኔንም ያፈርሳሉ።+ 21 ብዙ መከራና ችግር በሚደርስባቸው ጊዜ+ ይህ መዝሙር ምሥክር ይሆንባቸዋል፤ (ምክንያቱም ዘሮቻቸው ይህን መዝሙር ሊዘነጉት አይገባም፤) እኔ እንደሆነ ወደማልኩላቸው ምድር ገና ሳላስገባቸው ምን ዓይነት ዝንባሌ እንዳዳበሩ አውቄአለሁ።”+
22 ስለዚህ ሙሴ ይህን መዝሙር በዚያን ቀን ጻፈው፤ እስራኤላውያንንም አስተማራቸው።
23 እሱም* የነዌን ልጅ ኢያሱን ሾመው፤+ እንዲህም አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤+ ምክንያቱም እስራኤላውያንን ወደማልኩላቸው ምድር የምታስገባቸው አንተ ነህ፤+ እኔም ምንጊዜም ከአንተ ጋር እሆናለሁ።”
24 ሙሴም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በመጽሐፍ ላይ ጽፎ+ እንደጨረሰ 25 የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያኑን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 26 “ይህን የሕግ መጽሐፍ+ ወስዳችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት+ አጠገብ አስቀምጡት፤ ይህም በዚያ በእናንተ ላይ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል። 27 ምክንያቱም እናንተ ዓመፀኛና+ ግትር*+ መሆናችሁን በሚገባ አውቃለሁ። እኔ ዛሬ ከእናንተ ጋር በሕይወት እያለሁ በይሖዋ ላይ እንዲህ ካመፃችሁ ከሞትኩ በኋላማ ምን ያህል ታምፁ! 28 የነገዶቻችሁን ሽማግሌዎችና አለቆቻችሁን በሙሉ ሰብስቡልኝ፤ እኔም ጆሯቸው እየሰማ እነዚህን ቃላት ልናገር፤ ሰማይንና ምድርንም በእነሱ ላይ ምሥክሮች አድርጌ ልጥራ።+ 29 ምክንያቱም እኔ ከሞትኩ በኋላ ክፉ ድርጊት እንደምትፈጽሙና ካዘዝኳችሁ መንገድ ዞር እንደምትሉ በሚገባ አውቃለሁ።+ በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ስለምትፈጽሙና በእጆቻችሁ ሥራ ስለምታስቆጡት ወደፊት መከራ ይደርስባችኋል።”+
30 ከዚያም ሙሴ መላው የእስራኤል ጉባኤ እየሰማ የዚህን መዝሙር ቃላት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንዲህ ሲል ተናገረ፦+
32 “ሰማያት ሆይ፣ ጆሯችሁን ስጡኝ፤ እኔም እናገራለሁ፤
ምድርም የአፌን ቃል ትስማ።
ስለ አምላካችን ታላቅነት ተናገሩ!+
5 ምግባረ ብልሹ የሆኑት እነሱ ናቸው።+
ልጆቹ አይደሉም፤ ጉድለቱ የራሳቸው ነው።+
ጠማማና ወልጋዳ ትውልድ ናቸው!+
ወደ ሕልውና ያመጣህ አባትህ እሱ አይደለም?+
የሠራህና አጽንቶ ያቆመህስ እሱ አይደለም?
7 የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤
ያለፉት ትውልዶች የኖሩባቸውን ዓመታት መለስ ብለህ አስብ።
አባትህን ጠይቅ፤ ሊነግርህ ይችላል፤+
ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ይነግሩሃል።
11 ንስር ጎጆዋን እንደምትነቀንቅና
ከጫጩቶቿ በላይ እንደምታንዣብብ፣
ክንፎቿን ዘርግታ እንደምትይዛቸው፣
በላባዎቿም እንደምትሸከማቸው ሁሉ+
ከእሱም ጋር ምንም ባዕድ አምላክ አልነበረም።+
ከዓለት ማር አበላው፤
ከባልጩትም ዘይት መገበው፤
14 የላሞቹን ቅቤና የመንጋውን ወተት
ምርጥ ከሆነው በግ* ጋር ሰጠው፤
የባሳንን አውራ በጎችና አውራ ፍየሎች
አንተም ከወይን ፍሬው ደም* የወይን ጠጅ ጠጣህ።
ሰባህ፤ ፈረጠምክ፤ ደለብክ።+
ስለሆነም የሠራውን አምላክ ተወ፤+
አዳኝ የሆነለትን ዓለት ናቀ።
19 ይሖዋ ይህን ሲያይ ተዋቸው፤+
ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ አሳዝነውት ነበርና።
20 ስለዚህ እንዲህ አለ፦ ‘ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ፤+
ምን እንደሚሆኑም አያለሁ።
23 መከራቸውን አበዛዋለሁ፤
ቀስቶቼን በእነሱ ላይ እጨርሳለሁ።
የአራዊትን ጥርስ፣
በምድር ላይ የሚሳቡ እንስሳትንም መርዝ እልክባቸዋለሁ።+
26 እኔም “እበትናቸዋለሁ፤
መታሰቢያቸውም ከሰዎች ዘንድ እንዲጠፋ አደርጋለሁ” ባልኩ ነበር፤
“ክንዳችን የበላይ ሆነ፤+
ይህን ሁሉ ያደረገው ይሖዋ አይደለም” ሊሉ ይችላሉ።
29 ምነው ጥበበኛ በሆኑ ኖሮ!+ ይህን ሁሉ ያሰላስሉ ነበር።+
የሚደርስባቸውንም ያስቡ ነበር።+
30 ዓለታቸው ካልሸጣቸውና+
ይሖዋ ለምርኮ ካልዳረጋቸው በስተቀር
አንድ ሰው 1,000 ሊያሳድድ፣
ሁለት ሰው ደግሞ 10,000 ሊያባርር እንዴት ይችላል?+
32 ወይናቸው ከሰዶም የወይን ተክልና
ከገሞራ የእርሻ ቦታ የተገኘ ነው።+
የወይን ፍሬያቸው መርዛማ የወይን ፍሬ ነው፤
ዘለላቸው መራራ ነው።+
33 የወይን ጠጃቸው የእባቦች መርዝ፣
የጉበናም* ምሕረት የለሽ መርዝ ነው።
34 ይህ እኔ ጋ ያለ፣
በግምጃ ቤቴ ውስጥ ማኅተም ታትሞበት የተቀመጠ አይደለም?+
37 ከዚያም እንዲህ ይላል፦ ‘አማልክታቸው የት አሉ?+
መሸሸጊያ እንዲሆናቸው የተጠጉት ዓለትስ የት አለ?
38 የመሥዋዕቶቻቸውን ስብ* ይበላ፣
የመጠጥ መባዎቻቸውንም የወይን ጠጅ ይጠጣ የነበረው የት አለ?+
እስቲ ተነስተው ይርዷችሁ።
እስቲ መሸሸጊያ ስፍራ ይሁኑላችሁ።
እኔ እገድላለሁ፤ እኔ ሕያው አደርጋለሁ።+
40 እጄን ወደ ሰማይ አንስቼ፣
“በዘላለማዊ ሕያውነቴ” ብዬ እምላለሁ፤+
42 በታረዱና በተማረኩ ሰዎች ደም፣
በጠላት መሪዎች ራስ፣
ቀስቶቼን በደም አሰክራለሁ፤
ሰይፌም ሥጋ ይበላል።’
44 ሙሴም ከነዌ ልጅ ከሆሺአ*+ ጋር መጥቶ የዚህን መዝሙር ቃላት በሙሉ ሕዝቡ እየሰማ ተናገረ።+ 45 ሙሴ እነዚህን ቃላት በሙሉ ለመላው እስራኤል ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ 46 እንዲህ አላቸው፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዟቸው+ እኔ በዛሬው ዕለት እናንተን ለማስጠንቀቅ የምነግራችሁን ቃል ሁሉ ልብ በሉ።+ 47 ይህ ቃል ለእናንተ ሕይወታችሁ እንጂ እንዲሁ ባዶ ቃል አይደለም፤+ ይህ ቃል ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁን ሊያረዝምላችሁ ይችላል።”
48 ይሖዋ በዚያው ዕለት ሙሴን እንዲህ አለው፦ 49 “በኢያሪኮ ትይዩ በሞዓብ ምድር ወደሚገኘው ወደዚህ የአባሪም ተራራ+ ይኸውም ወደ ነቦ ተራራ+ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነአንን ምድር ተመልከት።+ 50 ወንድምህ አሮን በሆር ተራራ ላይ ሞቶ+ ወደ ወገኖቹ እንደተሰበሰበ* ሁሉ አንተም በምትወጣበት በዚህ ተራራ ላይ ትሞታለህ፤ ወደ ወገኖችህም ትሰበሰባለህ፤ 51 ምክንያቱም ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ በሚገኘው በቃዴስ፣ በመሪባ ውኃዎች+ አጠገብ በእስራኤላውያን መካከል ለእኔ ታማኝ ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ እንዲሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት እኔን አልቀደሳችሁኝም።+ 52 ምድሪቱን ከሩቅ ታያታለህ፤ ሆኖም ለእስራኤል ሕዝብ ወደምሰጣት ምድር አትገባም።”+
33 የእውነተኛው አምላክ ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት እስራኤላውያንን የባረካቸው በረከት ይህ ነው።+ 2 እንዲህ አለ፦
“ይሖዋ ከሲና መጣ፤+
ከሴይርም ሆኖ አበራባቸው።
7 ይሁዳንም እንዲህ ሲል ባረከው፦+
“ይሖዋ ሆይ፣ የይሁዳን ድምፅ ስማ፤+
ወደ ሕዝቦቹም መልሰህ አምጣው።
8 ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦+
በመሪባ ውኃዎች አጠገብ ተጣላኸው፤+
9 ሰውየው አባቱንና እናቱን በተመለከተ ‘ስለ እነሱ ግድ የለኝም’ አለ።
ሌላው ቀርቶ ወንድሞቹን እንኳ አልተቀበለም፤+
የገዛ ልጆቹንም ችላ አለ።
ቃልህን ታዘዋልና፤
ቃል ኪዳንህንም ጠብቀዋል።+
11 ይሖዋ ሆይ፣ ጉልበቱን ባርክለት፤
በእጆቹም ሥራ ደስ ይበልህ።
እሱን የሚጠሉት ዳግመኛ እንዳያንሰራሩ
በእሱ ላይ የሚነሱትን እግራቸውን* አድቅቅ።”
12 ስለ ቢንያም እንዲህ አለ፦+
“ይሖዋ የወደደው ያለስጋት አብሮት ይኑር፤
ቀኑን ሙሉ ይከልለዋልና፤
በትከሻዎቹም መካከል ይኖራል።”
13 ስለ ዮሴፍ እንዲህ አለ፦+
“ይሖዋ ከሰማይ በሚወርዱ ምርጥ ነገሮች፣
በጤዛና ከታች በሚመነጩ ውኃዎች+
ምድሩን ይባርክ፤+
14 እንዲሁም ፀሐይ በምታስገኛቸው ምርጥ ነገሮች፣
በየወሩ በሚገኝ ምርጥ ፍሬ፣+
15 ጥንታዊ ከሆኑ ተራሮች* በሚገኙ ምርጥ ነገሮች፣+
ጸንተው ከሚኖሩት ኮረብቶች በሚገኙ ምርጥ ነገሮች፣
16 ከምድር በሚገኙ ምርጥ ነገሮችና ምድርን በሞሉ ምርጥ ነገሮች፣+
በቁጥቋጦው ውስጥ በተገለጠው በእሱ ሞገስ ይባርክ።+
እነዚህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ፣
ከወንድሞቹ መካከል ተነጥሎ በወጣው አናት ላይ ይውረዱ።+
17 ግርማው እንደ በኩር በሬ ነው፤
ቀንዶቹም የዱር በሬ ቀንድ ናቸው።
በእነሱም ሰዎችን፣
ሕዝቦችን ሁሉ እስከ ምድር ዳርቻ ይገፋል።*
እነሱ የኤፍሬም አሥር ሺዎች ናቸው፤+
የምናሴም ሺዎች ናቸው።”
18 ስለ ዛብሎን እንዲህ አለ፦+
“ዛብሎን ሆይ፣ በመውጣትህ ደስ ይበልህ፤
አንተም ይሳኮር፣ በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ።+
19 ሰዎችን ወደ ተራራው ይጠራሉ።
በዚያም የጽድቅ መሥዋዕቶችን ያቀርባሉ።
ምክንያቱም በባሕሮች ውስጥ ካለው የተትረፈረፈ ሀብት፣
በአሸዋም ውስጥ ተሰውሮ ከተከማቸው ነገር* ዝቀው ያወጣሉ።”
20 ስለ ጋድ እንዲህ አለ፦+
“የጋድን ድንበሮች የሚያሰፋ የተባረከ ነው።+
በዚያ እንደ አንበሳ ይተኛል፤
ክንድን፣ አዎ አናትን ለመዘነጣጠል ተዘጋጅቶ ይጠብቃል።
የሕዝቡ መሪዎች አንድ ላይ ይሰበሰባሉ።
የይሖዋን ጽድቅና ድንጋጌዎች፣
በእስራኤል ያስፈጽማል።”
22 ስለ ዳን እንዲህ አለ፦+
“ዳን የአንበሳ ደቦል ነው።+
ከባሳን ዘሎ ይወጣል።”+
23 ስለ ንፍታሌም እንዲህ አለ፦+
“ንፍታሌም በይሖዋ ሞገስ ረክቷል፤
በእሱም በረከት ተሞልቷል።
ምዕራቡንና ደቡቡን ውረስ።”
24 ስለ አሴር እንዲህ አለ፦+
“አሴር በልጆች የተባረከ ነው።
በወንድሞቹ ፊት ሞገስ ያግኝ፤
እግሩንም ዘይት ውስጥ ይንከር።*
29 እስራኤል ሆይ፣ ደስተኛ ነህ!+
34 ከዚያም ሙሴ ከሞዓብ በረሃማ ሜዳ ተነስቶ ወደ ነቦ ተራራ+ ይኸውም በኢያሪኮ+ ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ጲስጋ አናት+ ወጣ። ይሖዋም ምድሪቱን በሙሉ አሳየው፤ ይኸውም ከጊልያድ እስከ ዳን፣+ 2 ንፍታሌምን በሙሉ፣ የኤፍሬምንና የምናሴን ምድር፣ በስተ ምዕራብ በኩል እስካለው ባሕር* ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር በሙሉ፣+ 3 ኔጌብን፣+ የዮርዳኖስን አውራጃ+ እንዲሁም የዘንባባ ዛፍ ከተማ በሆነችው በኢያሪኮ ካለው ሸለቋማ ሜዳ አንስቶ እስከ ዞአር+ ድረስ አሳየው።
4 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’+ በማለት የማልኩላቸው ምድር ይህች ናት። በዓይንህ እንድታያት አድርጌሃለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም።”+
5 የይሖዋ አገልጋይ ሙሴም ልክ ይሖዋ እንደተናገረው በዚያው በሞዓብ ምድር ሞተ።+ 6 እሱም ከቤትጰኦር ትይዩ በሞዓብ ምድር በሚገኘው ሸለቆ ቀበረው፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃብሩ የት እንደሚገኝ የሚያውቅ የለም።+ 7 ሙሴ በሞተ ጊዜ ዕድሜው 120 ዓመት ነበር።+ ዓይኖቹ አልፈዘዙም፤ ጉልበቱም አልደከመም ነበር። 8 እስራኤላውያንም በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ለሙሴ 30 ቀን አለቀሱለት።+ በመጨረሻም ለሙሴ የሚለቀስበትና የሚታዘንበት ጊዜ አበቃ።
9 የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴ እጁን ስለጫነበት+ የጥበብ መንፈስ ተሞልቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም እሱን ይሰሙት ጀመር፤ እንዲሁም ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።+ 10 ሆኖም ይሖዋ ፊት ለፊት እንዳወቀው+ እንደ ሙሴ ያለ ሌላ ነቢይ እስካሁን በእስራኤል ተነስቶ አያውቅም።+ 11 ይሖዋ በግብፅ ምድር በፈርዖን፣ በአገልጋዮቹ ሁሉና በምድሩ ሁሉ ፊት እንዲፈጽም የላከውን ምልክቶችና ተአምራት በሙሉ ፈጸመ፤+ 12 ከዚህም በተጨማሪ ሙሴ በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት በኃያል ክንድ ታላቅና አስፈሪ ድርጊት ፈጸመ።+
ቃል በቃል “ለእስራኤል ወንዶች ልጆች።”
ወይም “በአስታሮት እና በኤድራይ ይኖር የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ኦግን።”
የሊባኖስን የተራራ ሰንሰለት እንደሚያመለክት ከሁኔታው መረዳት ይቻላል።
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
“አምላክ እሱን ብርቱ አድርጎታል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “እነሱን አትተንኩሷቸው።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ቀርጤስን ያመለክታል።
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
“የጥቁር ባልጩት” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በድንጋይ የተሠራ የሬሳ ሣጥን፤ የሬሳ ሣጥን።”
አንድ ክንድ 44.5 ሴንቲ ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
“የያኢር የድንኳን መንደሮች” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ሙት ባሕርን ያመለክታል።
ወይም “ለነፍሳችሁም ከፍተኛ ትኩረት ስጡ።”
ቃል በቃል “እስከ ሰማያት ልብ ድረስ።”
ቃል በቃል “ቃላት።”
ወይም “ለነፍሳችሁም ከፍተኛ ትኩረት ስጡ።”
ወይም “ውርሻው።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “በፈተናዎች።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ጨው ባሕርን ወይም ሙት ባሕርን ያመለክታል።
ወይም “እኔን የሚቀናቀኑ።”
ወይም “ፍቅራዊ ደግነት።”
ቃል በቃል “በደጅህ።”
ቃል በቃል “ቃላት።”
ወይም “ከሰው ዘር።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ለልጆችህ ደጋግመህ ንገራቸው፤ በልጆችህ ላይ አትማቸው።”
ቃል በቃል “በዓይኖችህም መካከል።”
ቃል በቃል “በአምላካችን በይሖዋ ፊት።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ውድ ሀብቱ።”
ቃል በቃል “ዓይንህ አይዘንላቸው።”
ወይም “ፈተናዎች።”
“ድንጋጤ፤ ሽብር” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ደረቅ ወንዞች።”
ቃል በቃል “ከባልጩት ድንጋይ።”
ወይም “ታስለቅቃቸውና።”
ቃል በቃል “አንገተ ደንዳና።”
ወይም “ቀልጦ የተሠራ ሐውልትም።”
ቃል በቃል “አንገተ ደንዳና።”
ወይም “ቀልጦ የተሠራ።”
ወይም “ውርሻህ።”
ወይም “ውርሻህ።”
ወይም “ሣጥንም።”
ቃል በቃል “አሥርቱን ቃላት።”
ወይም “ደረቅ ወንዞች።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “እጅግ ከፍ ያሉት ሰማያት።”
ቃል በቃል “የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ።”
ቃል በቃል “አንገታችሁን አታደንድኑ።”
ወይም “ወላጅ አልባ ለሆነው።”
ወይም “70 ነፍስ።”
ወይም “እስከዚህ ቀን ድረስ።”
ወይም “በእግርህ ታጠጣት።” በእግር ተጠቅሞ በውኃ ኃይል የሚሽከረከርን መንኮራኩር በማንቀሳቀስም ሆነ የውኃ መውረጃ ቦዮችን በመሥራትና በመክፈት ውኃ ማጠጣትን ያመለክታል።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “በዓይኖቻችሁም መካከል።”
ታላቁን ባሕር፣ ሜድትራንያንን ያመለክታል።
ወይም “ትሰጣላችሁ።”
ወይም “በፀሐይ መግቢያ።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “በደጆቻችሁ።”
ቃል በቃል “በደጆችህ ሁሉ ውስጥ።”
ወይም “ነፍስህ ባሰኛት።”
ቅርንጫፍ የሚመስሉ ቀንዶች ያሉት አጥቢ እንስሳ፤ ከአጋዘን ጋር ይመሳሰላል።
ቃል በቃል “በደጆችህ።”
ቃል በቃል “በደጆችህ።”
ወይም “ነፍስህ ሥጋ መብላት ፈልጋ።”
ወይም “ነፍስህ ባሰኛት።”
ወይም “ነፍስህ ባሰኛት።”
ቃል በቃል “በደጆችህ።”
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “ነፍስን።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “እንደ ገዛ ነፍስህ የሆነው ጓደኛህ።”
ወይም “ድምፁን ስማ።”
ቃል በቃል “በዓይኖቻችሁ መካከል ያለውን ቦታ።” ግንባርን ሊጨምር ይችላል።
ወይም “ውድ ሀብቱ።”
ወይም “ነፍሳት።”
ቃል በቃል “በደጆችህ።”
ወይም “አሥራት።”
ወይም “ነፍስህ የምትሻውን።”
ወይም “ነፍስህ የምትጠይቅህን።”
ወይም “ወላጅ አልባ የሆኑ።”
ወይም “በመያዣ ታበድራለህ።”
ወይም “በመያዣ አበድረው።”
ቃል በቃል “በበሬህ።”
ቃል በቃል “በደጆችህ።”
ቅርንጫፍ የሚመስሉ ቀንዶች ያሉት አጥቢ እንስሳ፤ ከአጋዘን ጋር ይመሳሰላል።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ15ን ተመልከት።
ወይም “የማለፍን በዓል።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “በደጆችህ ውስጥ።”
ወይም “ወላጅ አልባ የሆነው።”
ወይም “የጊዜያዊ መጠለያ።”
ወይም “በጊዜያዊ መጠለያ።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች አፍ።”
ወይም “በጥቅልል።”
ይሖዋ የአምልኮ ማዕከል አድርጎ የሚመርጠውን ስፍራ ያመለክታል።
ወይም “ነፍሱ መሄድ ብትፈልግ።”
ቃል በቃል “ልቡ የነደደው።”
ቃል በቃል “ዓይንህ አይዘንለት።”
ቃል በቃል “በሁለት ምሥክሮች ወይም በሦስት ምሥክሮች አፍ።”
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “ነፍስ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ነፍሷ ወዳሻት።”
ቃል በቃል “አንደኛዋ የምትወደድ፣ ሌላኛዋ የምትጠላ ብትሆን።”
አንድ ሰቅል 11.4 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ነፍስ ከሚገድል።”
ቃል በቃል “የአባቱን ቀሚስ እንዳይገልጥ።”
ወይም “የሚያረክስ።”
ቃል በቃል “ለውሻ።”
ወይም “ወንድ ዝሙት አዳሪ የሚያገኘውን ገቢ።”
ወይም “ነፍስህ እስክትረካ።”
ወይም “የሰውየውን ሕይወት፤ የሰውየውን ነፍስ።”
“የሥጋ ደዌ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ሰፊ ትርጉም ያለው ሲሆን የተለያዩ ተላላፊ የቆዳ በሽታዎችን ሊያመለክት ይችላል። ልብስንና ቤትን የሚበክሉ አንዳንድ በሽታዎችንም ሊጨምር ይችላል።
ቃል በቃል “በደጆችህ።”
ወይም “ነፍሱ።”
ወይም “ወላጅ አልባ የሆነውን።”
ቃል በቃል “የዚያ ሰው ስም።”
ቃል በቃል “ዓይንህ ሊያዝንላት አይገባም።”
ቃል በቃል “በቤትህ ውስጥ አንድ ኢፍና አንድ ኢፍ።” ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
“ሊጠፋ የሚችል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ወላጅ አልባ ለሆነው።”
ቃል በቃል “በደጆችህ።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ውድ ሀብቱ።”
ወይም “ኖራ ቀቧቸው።”
ወይም “ኖራ ቀቧቸው።”
ወይም “የእንጨትና የብረት ሠራተኛ።”
ወይም “ቀልጦ የተሠራ ሐውልት።”
ወይም “ይሁን!”
ወይም “ወላጅ አልባ የሆነውን።”
ቃል በቃል “የአባቱን ቀሚስ ስለገለጠ።”
ወይም “የንጹሑን ደም ነፍስ።”
ቃል በቃል “መተረቻና።”
ቃል በቃል “በደጆችህ።”
ወይም “ተስፋ የቆረጠ ነፍስ ይሰጥሃል።”
ወይም “ፈተናዎች።”
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።
ቃል በቃል “ውኃ የጠገበውን ውኃ ከተጠማው ጋር።”
ቃል በቃል “እሱ ያልመደበላቸውን።”
ቃል በቃል “ወደ ልብህ መልሰህ በምታመጣበት።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ይገርዛል።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ልወጣና ልገባ።”
ወይም “የጊዜያዊ መጠለያ።”
ቃል በቃል “ሕፃናትንና።”
ቃል በቃል “በደጆችህ ውስጥ።”
ወይም “ቦታችሁን ያዙ።”
ቃል በቃል “ከአባቶችህ ጋር ትተኛለህ።”
ቃል በቃል “በአፋቸው ውስጥ አድርጉት።”
ቃል በቃል “ሲወፍሩ።”
አምላክን እንደሚያመለክት ከሁኔታው መረዳት ይቻላል።
ቃል በቃል “አንገተ ደንዳና።”
“የሰው ዘርን” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ያዕቆብን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ከበጉ ስብ።”
ቃል በቃል “ከስንዴው ኩላሊት ስብ።”
ወይም “ጭማቂ።”
“ቅን የሆነው” የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ለእስራኤል የተሰጠ የማዕረግ ስም ነው።
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
“ምክር የማይሰማ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
በእስያና በአፍሪካ የሚገኝ እጅግ መርዘኛ የሆነ እባብ፤ ኮብራ።
ወይም “በእነሱ ይጸጸታል።”
ወይም “ምርጥ የሆኑ መሥዋዕቶቻቸውን።”
ወይም “የሕዝቡንም ምድር ያነጻል።”
የኢያሱ ዋነኛው ስም ነው። ሆሺአ የሆሻያህ አጭር አጠራር ሲሆን “ያህ ያዳነው፤ ያህ አድኗል” የሚል ትርጉም አለው።
ይህ ሞትን የሚያመለክት ቅኔያዊ አነጋገር ነው።
ወይም “በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ቅዱሳን።”
“ቅን የሆነው” የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ለእስራኤል የተሰጠ የማዕረግ ስም ነው።
ወይም “ይታገላሉ።”
እዚህ ጥቅስ ላይ ያሉት “የአንተ” እና “ለአንተ” የሚሉት ቃላት አምላክን ያመለክታሉ።
ወይም “ወገባቸውን።”
“ከምሥራቅ ተራሮች” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ይወጋል።”
ወይም “የከበረ ሀብት።”
ወይም “ይታጠብ።”
ቃል በቃል “ብርታትህም እንደ ዘመንህ ይሆናል።”
“በከፍታ ቦታዎቻቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ታላቁን ባሕር፣ ሜድትራንያንን ያመለክታል።