ሊፈርሱ ለተቃረቡ ትዳሮች የሚሆን እርዳታ
በኒው ዚላንድ ደሴት ሰሜናዊ ክፍል የምትኖር ሴት ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ስለተባለው መጽሐፍ እንዲህ ስትል ጽፋለች:- “ይህን መጽሐፍ ማጥናት ስጀምር ትዳሬ ‘ላፈርሰውም ላሳካውም’ በምችልበት ደረጃ ላይ የደረሰ እንደሆነ ተሰማኝ።”
ስለ አስተዳደጓ እንዲህ በማለት ታብራራለች። “እናቴ በጣም አስቸጋሪ የሆኑ ሁለት ትዳሮች አሳልፋለች። በዚህም የተነሣ ከልጅነታችን ጀምሮ ወንዶች ሴቶችን ከመጨቆን በቀር ምንም ፋይዳ እንደሌላቸው ስንማር አድገናል። ስለዚህ ከማንኛውም ጭቅጭቅ ወደኋላ የማልል እልከኛና ሐሳበ ግትር ሴት ሆንኩ።”
ይህች ሴት ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልጋት ተገነዘበች። “ለባለቤቴ ለመገዛት ፈቃደኛ ባለመሆኔና በጣም ትዕቢተኛ በመሆኔ ምክንያት የቤተሰብ ደስታ የማግኘት ዕድል እያመለጠኝ እንዳለ ተገነዘብኩ” ትላለች። ስለዚህም በጣም አስፈላጊ የሆኑ ማስተካከያዎች ማድረግ ጀመረች። “በአሁኑ ጊዜ እኔና ባለቤቴ መጽሐፉን በቤተሰብ ደረጃ በማጥናት ላይ ነን። ክርስቲያን ሚስት መሆን የምችለው እንዴት እንደሆነ እየተማርኩ ነው። አሁን በደረስንበት ደረጃ እንኳን በጣም የተደሰትን ብንሆንም ገና ብዙ ይቀረናል።
“ቤታችን እንደ አሁኑ ፍቅርና ሰላም የሰፈነበት ሆኖ አያውቅም።”
“አምላክን የሚያስደስት የቤተሰብ ሕይወት” የሚለው ትምህርት 8 የሚገኝበትን አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የሚለውን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ.ሣ.ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ወይም በገጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ። በተጨማሪም አንድ የይሖዋ ምሥክር መጥቶ እንዲያነጋግርዎትና መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንዲያስተምርዎ ከፈለጉ ይህንኑ ፍላጎትዎን ይጥቀሱ።