የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 8/8 ገጽ 32
  • ዓላማ ያለው ጽሑፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዓላማ ያለው ጽሑፍ
  • ንቁ!—1999
ንቁ!—1999
g99 8/8 ገጽ 32

ዓላማ ያለው ጽሑፍ

በቼክ ሪፑብሊክ ፕራግ ውስጥ የሚገኝ የአንድ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ኃላፊ በንቁ! መጽሔት ላይ ያካሄደውን ግምገማ በሁለት ገጽ ወረቀት ላይ አስፍሮ በቤተ መጻሕፍቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ለጠፈው። ከሰጠው አስተያየት መካከል የሚከተለው ይገኝበታል:-

“እኔ የይሖዋ ምሥክር አይደለሁም። የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ተሟጋችም ሆነ አክራሪ ተቃዋሚ አይደለሁም። ሆኖም ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ እያነበብኩት ያለሁትን ንቁ! መጽሔት ለማድነቅ ተገድጃለሁ። ርዕሱን ብቻ እንኳ በቀን አንዴ ብታነቡ በእጅጉ ትጠቀማላችሁ። ይሁን እንጂ ርዕሱ ብቻ ሳይሆን የመጽሔቱ ይዘትም ራሱ ለሌሎች የንግድ መጽሔቶች ጠቃሚ የሆኑ ቁም ነገሮች የያዘ ነው። ...

“ንቁ! ጥልቅ ጥናት የተካሄደባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች ይዞ የሚወጣ መጽሔት ነው። ሌሎች መጽሔቶች በተለያዩ ምክንያቶች ሊያወጧቸው የማይፈልጓቸውን ርዕሶች ይዞ ይወጣል። አቀራረቡ ምክንያታዊ ከመሆኑም በላይ ሰዎች አንድን ነገር አስቀድመው እንዲገነዘቡ ያደርጋል ... ንቁ! እንዲህ ማድረግ አለባችሁ የሚል የውሳኔ ሐሳብ አያስተላልፍም። እውነታዎችንና የባለሙያዎችን አስተያየት ያቀርባል፣ የአንድን ነገር ጥቅምና ጉዳት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፣ በዛሬው ጊዜ ላሉት ችግሮች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመጠቀም ምላሽ ይሰጣል፣ ውሳኔውን ደግሞ ለአንባቢው ይተዋል። ከዚህም ሌላ ንቁ! ጥያቄዎች ያቀርባል፤ አንባቢዎቹም ጥያቄ መጠየቅን እንዲማሩ ያደርጋል።”

በእያንዳንዱ መጽሔት ገጽ 4 ላይ “ንቁ! የሚታተምበት ምክንያት” በሚለው ክፍል ሥር “ከሁሉም በላይ ይህ መጽሔት አሁን ያለውን ክፉና ዓመፀኛ ሥርዓት የሚተካ ሰላም የሰፈነበትና አስተማማኝ አዲስ ዓለም እንደሚመጣ ፈጣሪ በሰጠው ተስፋ ላይ ሰዎች ያላቸውን እምነት እንዲያሳድጉ ያደርጋል” ሲል ይገልጻል።

ይህ አምላክ የሰጠው ተስፋ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? የሚል ርዕስ ባለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር የመጨረሻ ሁለት ክፍሎች ላይ ተብራርቷል። እነዚህ ክፍሎች “የአምላክ ዓላማ በቅርቡ ይፈጸማል” እና “ገነት በሆነች ምድር ላይ ለዘላለም ኑር” የሚሉ ርዕሶችን የያዙ ናቸው። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።

□ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ