ገጽ ሁለት
የትዳር ጓደኛ ሲከዳ 3-12
ጉዳዩ በሚመለከታቸው ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ምንድን ነው? ምንዝር ከፈጸመ የትዳር ጓደኛ ጋር እርቅ ለመፍጠር መጣር ይገባልን? ፍቺ የተሻለ አማራጭ ነውን?
ግዞት በሳይቤሪያ! 14
በሳይቤሪያ ለረጅም ዓመታት በግዞት ስለኖረ አንድ ቤተሰብ የሚገልጸውን ታሪክ አንብብ። እንዲሁም በአምላክ ላይ ያሳደሩት እምነት እንዴት ጠብቆ እንዳቆያቸው ተመልከት።
አውዳሚ ከሆነ ዓውሎ ነፋስ የሰዎችን ሕይወት መታደግ! 20
ሚች የተባለው ዓውሎ ነፋስ በዚህ መቶ ዘመን ከተከሰቱት እጅግ አውዳሚ ዓውሎ ነፋሳት አንዱ ሲሆን ክርስቲያኖች በዚህ ዓውሎ ነፋስ የተጎዱ ሰዎችን ለመታደግ ስላደረጉት ጥረት የሚገልጸውን አስደናቂ ታሪክ አንብብ።
[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]
ሽፋን:- Superstock