የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 5/12 ገጽ 32
  • “ያለፉት ነገሮች . . . አይታወሱም”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ያለፉት ነገሮች . . . አይታወሱም”
  • ንቁ!—2012
ንቁ!—2012
g 5/12 ገጽ 32

“ያለፉት ነገሮች . . . አይታወሱም”

ፈጣሪያችን መላውን የሰው ዘር የሚነካ አንድ አስደናቂ ትንቢት አስነግሯል። እንዲህ ብሏል፦

“እነሆ፤ እኔ፣ አዲስ ሰማያትንና አዲስ ምድርን እፈጥራለሁ፤ ያለፉት ነገሮች አይታሰቡም፤ አይታወሱም።”​—ኢሳይያስ 65:17

“አይታወሱም” የተባሉት “ያለፉት ነገሮች” ምንድን ናቸው? በጥቅሱ ዙሪያ ካለው ሐሳብ መረዳት እንደምንችለው የሰው ልጆች ሕይወት አስጨናቂ እንዲሆን የሚያደርጉትን እንደ ፍትሕ መጓደል፣ በሽታ፣ መከራ እና ያሉ ነገሮች ያመለክታሉ። ይሁንና እነዚህ አስጨናቂ ነገሮች የሚወገዱት እንዴት ነው? በትንቢቱ ላይ የተጠቀሱትን “አዲስ ሰማያት” እና “አዲስ ምድር” የሚሉትን አገላለጾች በመመርመር ለዚህ ጥያቄ መልስ ማግኘት እንችላለን።

“ያለፉት ነገሮች . . . አይታወሱም” በሚለው የሕዝብ ንግግር ላይ እነዚህ ትኩረት የሚስቡ አገላለጾች ያላቸው ትርጉም ይብራራል። ይህ ንግግር የሚቀርበው በግንቦት ወር በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚጀምረውና ከዚያም በኋላ በሌሎች የዓለም ክፍሎች በሚካሄደው “ልብህን ጠብቅ!” በተሰኘው የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ ላይ ነው።”

እርስዎም በአቅራቢያዎ በሚደረገው የአውራጃ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ጋብዘንዎታል። ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እባክዎ በአካባቢዎ ያሉትን የይሖዋ ምሥክሮች ያነጋግሩ፤ አሊያም ለዚህ መጽሔት አዘጋጆች ይጻፉ። በተጨማሪም ስብሰባው በተለያዩ አገሮች መቼና የት እንደሚካሄድ የሚገልጽ ፕሮግራም www.jw.org በሚለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ