የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 5/12 ገጽ 14-31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2012
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
  • ካርድ በመሰብሰብ መማር
  • ሕዝቦችና አገሮች
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ
  • ከሠራው ስህተት ተምሯል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • ከሠራው ስህተት ተምሯል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ዮናስ ስለ ይሖዋ ምሕረት ትምህርት አገኘ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ትሑትና ደፋር የነበረ ሰው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 5/12 ገጽ 14-31

ቤተሰብ የሚወያይበት

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

አንደኛ ዜና መዋዕል 16:1, 2, 4-10⁠ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ነጥቦቹን በመስመር ካገናኘህ በኋላ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

[ሰንጠረዥ]

(ጽሑፉን ተመልከት)

ለውይይት፦

ይሖዋ አምላክ መዝሙርና ሙዚቃ የአምልኮታችን ክፍል ቢሆን ደስ የሚለው ይመስልሃል? እንደዚህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

ፍንጭ፦ ሁለተኛ ዜና መዋዕል 5:13, 14⁠ን እና ኤፌሶን 5:19⁠ን አንብብ። መዝሙር በእውነተኛው አምልኮ ውስጥ ቦታ እንደነበረው የሚያሳዩ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎችን መጥቀስ ትችላለህ?

ፍንጭ፦ ዘፀአት 15:1-20⁠ን፤ ማርቆስ 14:26⁠ን እና የሐዋርያት ሥራ 16:25⁠ን አንብብ። ዓይን አፋር ብትሆንም ወይም ሌሎች ከአንተ የተሻለ እንደሚዘምሩ ቢሰማህም ለይሖዋ መዘመርህን እንድትቀጥል ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖርህ ይገባል?

ፍንጭ፦ መዝሙር 33:1-3⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በጣም የሚወደውን መዝሙር እንዲመርጥ አድርጉ። ከዚያም እነዚህን መዝሙሮች በደንብ እስክትችሏቸው ድረስ በቤተሰብ ሆናችሁ ተለማመዷቸው።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 17 ዮናስ

ጥያቄ

ሀ. ዮናስ ቁጥራቸው ከ ․․․․․ የሚበልጡ ሰዎች ይኖሩባት ወደነበረችው ወደ ․․․․․ ሄዶ እንዲሰብክ ተልኳል።

ለ. ዮናስ የተሰጠውን ተልእኮ ላለመፈጸም ቢኮበልልም ሌሎችን ለማዳን ሲል በኋላ ላይ ምን የድፍረት እርምጃ ወስዷል?

ሐ. የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አሟላ፦ “ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ . . . ”

[ሰንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

840 ዓ.ዓ. ገደማ ዮናስ የኖረበት ዘመን

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

ከጋትሔፌር ወደ ተርሴስ ኮብልሏል

ጋትሔፌር

ተርሴስ

ነነዌ

ዮናስ

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

በዳግማዊ ኢዮርብዓም የግዛት ዘመን ይሖዋን ያገለግል የነበረ ነቢይ ነው። (2 ነገሥት 14:23-25) ዮናስ፣ ስለ ራሱ ብቻ ከማሰብ ይልቅ ሌሎች ለሚያስፈልጋቸው ነገርም ትኩረት እንዲሰጥ ይሖዋ አስተምሮታል። (ዮናስ 4:6-11) ይሖዋ ኃጢአተኛ ከሆኑ የሰው ልጆች ጋር ባለው ግንኙነት ረገድ እጅግ ታጋሽ፣ መሐሪ እንዲሁም ደግ እንደሆነ ከዮናስ ታሪክ መማር እንችላለን።

መልስ

ሀ. 120,000፤ ነነዌ።—ዮናስ 1:1, 2 እና 4:11

ለ. ማዕበሉ ጸጥ እንዲል ሲል ወደ ባሕሩ እንዲወረውሩት በመርከቡ ውስጥ ለነበሩት ሰዎች ነገራቸው።—ዮናስ 1:3, 9-16

ሐ. “ . . . ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አደረ።”—ዮናስ 1:17

ሕዝቦችና አገሮች

4. ሜሊሳ እና ኤዲሎ እንባላለን፤ የ9 እና የ7 ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በኩባ ነው። በኩባ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 51,000፣ 91,000 ወይስ 131,000?

5. የምንኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከኩባ በጣም ይርቃል?

ሀ

ለ

ሐ

መ

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

“ቤተሰብ የሚወያይበት” የሚለውን ዓምድ ተጨማሪ ቅጂ ለማግኘት www.jw.org ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማተም ይቻላል።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 14 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. ታቦቱ ያለበት ድንኳን

2. በገና

3. መለከት

4. 91,000

5. ሐ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ