“ተከታዬ ሁን”
መንገድ ጠፍቶህ አንድ ሰው አቅጣጫ እንዲጠቁምህ ጠይቀህ ታውቃለህ? ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክ የተሾመ መሪ ሲሆን ሁሉም ሰው የእሱ አመራር ያስፈልገዋል። ኢየሱስ “እኔ ጥሩ እረኛ ነኝ። በጎቼን አውቃቸዋለሁ፤ በጎቼም ያውቁኛል” ብሏል። (ዮሐንስ 10:14) ጥሩውን እረኛ በሚገባ ታውቀዋለህ? ስለ ባሕርያቱ፣ ስላስተማረው ትምህርት፣ ስላከናወነው ሥራ እንዲሁም ስላሳየው ቅንዓትና ፍቅርስ ምን ያህል ታውቃለህ? ይህ መጽሐፍ ኢየሱስን ይበልጥ እንድታውቀውና ፈለጉን በቅርብ እንድትከተል ይረዳሃል።