የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bsi08-2 ገጽ 21-22
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 61—2 ጴጥሮስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 61—2 ጴጥሮስ
  • “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 17
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት
“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 17
bsi08-2 ገጽ 21-22

የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 61​—⁠2 ጴጥሮስ

ጸሐፊው:- ጴጥሮስ

የተጻፈበት ቦታ:- ባቢሎን (?)

ተጽፎ ያለቀው:- በ64 ከክ.ል.በኋላ ገደማ

ጴጥሮስ ሁለተኛውን ደብዳቤ በጻፈበት ወቅት የሚሞትበት ጊዜ እንደተቃረበ ተገንዝቦ ነበር። በመሆኑም የእምነት ባልንጀሮቹ በክርስቲያናዊ አገልግሎታቸው ጸንተው መቀጠል እንዲችሉ ለማድረግ ሲል የትክክለኛ እውቀትን አስፈላጊነት ሊያስገነዝባቸው ጓጉቷል። በስሙ የሚጠራውን ሁለተኛ መልእክት የጻፈው ሐዋርያው ጴጥሮስ ስለመሆኑ የምንጠራጠርበት ምክንያት ይኖራል? መልእክቱ ራሱ፣ ስለ ጸሐፊው ማንነት የሚነሳውን ማንኛውንም ዓይነት ጥርጣሬ ያስወግድልናል። ጸሐፊው፣ “የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ [የሆነው] ስምዖን ጴጥሮስ” መሆኑን ገልጿል። (2 ጴጥ. 1:1) ከዚህም በላይ “አሁን የምጽፍላችሁ ሁለተኛው መልእክት ነው” ብሏል። (3:1) ጸሐፊው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በተዓምራዊ ሁኔታ በተለወጠ ጊዜ በቦታው እንደነበረ የገለጸ ከመሆኑም ሌላ ስለ ሁኔታው የጻፈውም የዓይን ምሥክር እንደሆነ በሚያሳይ መንገድ ነው። ይህ ክንውን በተፈጸመበት ወቅት ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ሆኖ በስፍራው የመገኘት መብት ያገኘው ደግሞ ሐዋርያው ጴጥሮስ ነው። (1:16-21) በተጨማሪም ጸሐፊው፣ ኢየሱስ የእሱን ሞት በሚመለከት አስቀድሞ መናገሩን ገልጿል።—2 ጴጥ. 1:14፤ ዮሐ. 21:18, 19

2 ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ ተቺዎች ሁለተኛውን መልእክት የጻፈው ጴጥሮስ አይደለም ለማለት በሁለቱ መልእክቶች መካከል ያለውን የአጻጻፍ ስልት ልዩነት እንደ ምክንያት ይጠቅሳሉ። ነገር ግን የሁለቱ መልእክቶች ርዕሰ ጉዳይም ሆነ የተጻፉበት ዓላማ ስለሚለያይ ይህ እንደ አጥጋቢ ምክንያት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም። ከዚህም በተጨማሪ፣ ጴጥሮስ የመጀመሪያ መልእክቱን የጻፈው ‘በታማኙ ወንድም በስልዋኖስ አማካይነት’ ነበር። በወቅቱ ስልዋኖስ ዓረፍተ ነገሮቹን በራሱ አባባል እንዲያዋቅር የተወሰነ ነፃነት ተሰጥቶት ከነበረ፣ በሁለቱ መልእክቶች መካከል የአጻጻፍ ልዩነት እንዲንጸባረቅ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም ሁለተኛው መልእክት በተጻፈበት ወቅት ስልዋኖስ ምንም ዓይነት ተሳትፎ አልነበረውም። (1 ጴጥ. 5:12) በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶች “አበው እውነተኝነቱን በሚገባ አላረጋገጡም” በማለት መልእክቱ የቅዱሳን መጻሕፍት ክፍል ስለመሆኑ ጥያቄ ያነሳሉ። ይሁን እንጂ ሁለተኛ ጴጥሮስ ከሦስተኛው የካርቴጅ ምክር ቤት በፊት በነበሩ በርካታ ምሑራንም ዘንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተደርጎ ይታይ ነበር።

3 ሁለተኛው የጴጥሮስ መልእክት የተጻፈው መቼ ነው? መልእክቱ የተጻፈው፣ አንደኛው መልእክት ከተጻፈ ብዙም ሳይቆይ በ64 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ገደማ በባቢሎን ወይም በአቅራቢያው ሳይሆን አይቀርም። ያም ሆኖ ግን በተለይ የተጻፈበትን ቦታ በሚመለከት ቀጥተኛ ማስረጃ አልተገኘም። ይህ መልእክት በተጻፈበት ወቅት፣ አብዛኞቹ የጳውሎስ ደብዳቤዎች በክርስቲያን ጉባኤዎች ውስጥ በስፋት ተሠራጭተው የነበረ ሲሆን እነዚህን መልእክቶች በሚገባ የሚያውቃቸው ጴጥሮስም በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፉና ‘ከሌሎቹ ቅዱሳት መጻሕፍት’ መካከል እንደሆኑ አድርጎ ይመለከታቸው ነበር። ጴጥሮስ ሁለተኛ መልእክቱን የጻፈው ‘[እነሱ] እንደተቀበሉት ዓይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉት’ ሲሆን ይህም የመጀመሪያ መልእክቱን የላከላቸውን እንዲሁም እሱ የሰበከላቸውን ሌሎች ሰዎችን ይጨምራል። የመጀመሪያው መልእክቱ በተለያዩ አካባቢዎች እንደተዳረሰ ሁሉ ሁለተኛው መልእክቱም ለሁሉም ጉባኤዎች የሚጠቅም ሐሳብ ይዞ ነበር።—2 ጴጥ. 3:15, 16፤ 1:1፤ 3:1፤ 1 ጴጥ. 1:1

ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት

8 ትክክለኛ እውቀት ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው! ጴጥሮስ ራሱ ነጥቦቹን ያቀረበው ከዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ካካበተው ትክክለኛ እውቀት ጋር በማጣመር ነበር። የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት መጻፋቸውን ሲገልጽ እንዲህ ብሏል:- “ትንቢት ከእግዚአብሔር የተላኩ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናገሩት እንጂ ከቶ በሰው ፈቃድ የመጣ አይደለም።” ጴጥሮስ፣ ጳውሎስም ቢሆን የጻፈው ‘በተሰጠው’ ጥበብ መሠረት መሆኑን አመልክቷል። (1:21፤ 3:15) እነዚህን ቅዱሳን መጻሕፍት መመርመራችንና ትክክለኛውን እውቀት የሙጥኝ ብለን መያዛችን ትልቅ ጥቅም ያስገኝልናል። እንዲህ ካደረግን ጴጥሮስ፣ “ከፍጥረት መጀመሪያ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ሁሉም ነገር እንዳለ ይኖራል” ይላሉ እንዳላቸው ቸልተኛ ሰዎች አንሆንም። (3:4) ወይም ደግሞ ጴጥሮስ በምዕራፍ 2 ላይ እንደጠቀሳቸው ሰዎች፣ በሐሰት አስተማሪዎች ወጥመድ አንወድቅም። ከዚህ ይልቅ ጴጥሮስም ሆነ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች በሰጡት ማሳሰቢያ ላይ ዘወትር እናሰላስላለን። ይህም ‘በእውነት እንድንጸና’ የሚረዳን ከመሆኑም ሌላ “በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት” የማያቋርጥ ዕድገት እንድናደርግ ያስችለናል።—1:12፤ 3:18

9 ጴጥሮስ፣ ‘ስለ አምላክና ስለ ጌታችን ኢየሱስ [‘የምንቀስመው ትክክለኛ፣’ NW] እውቀት’ እያደገ እንዲሄድ ከፈለግን በምዕራፍ 1 ከቁጥር 5 እስከ 7 ድረስ የተጠቀሱትን ክርስቲያናዊ ባሕርያት ለማፍራት ያልተቆጠበ ጥረት ማድረግ እንዳለብን ተናግሯል። ከዚያም ቁጥር 8 ላይ እንዲህ አለ:- “እነዚህ ባሕርያት ተትረፍርፈው ቢኖሯችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን [‘በትክክል፣’ NW] በማወቅ ዳተኞችና ፍሬ ቢሶች ከመሆን ይጠብቋችኋል።” በአስጨናቂ ጊዜ ውስጥ የምንኖር የአምላክ አገልጋዮች እንደመሆናችን መጠን ይህ የጴጥሮስ ምክር ለሥራ የሚያንቀሳቅስ ግሩም ማበረታቻ እንደሚሆንልን ጥርጥር የለውም!—1:2

10 አንድ ሰው፣ ይሖዋ አምላክ የሰጠውን ‘እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነ ተስፋ’ ለመውረስ ከፍተኛ ትጋት ማሳየቱ በጣም አስፈላጊ ነው! ጴጥሮስ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን ዓይናቸው በመንግሥቱ ላይ እንዲያተኩር የመከራቸውም ለዚህ ነው። እንዲህ ብሏቸዋል:- “መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማጽናት ከፊት ይልቅ ትጉ፤ ምክንያቱም እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም፤ በዚህም ወደ ጌታችንና አዳኛችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል።” ከዚያም ጴጥሮስ፣ ኢየሱስ በተአምራዊ ሁኔታ በተለወጠ ጊዜ ስላየው ስለ መንግሥቱ ክብርና ግርማ ከገለጸ በኋላ “ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል” ብሏል። ዕጹብ ድንቅ ስለሆነው የይሖዋ መንግሥት የተነገረው እያንዳንዱ ትንቢት ፍጻሜውን እንደሚያገኝ ምንም ጥርጥር የለውም። በመሆኑም እኛም በኢሳይያስ ትንቢት ውስጥ የሚገኘውንና ጴጥሮስ እንደሚከተለው ሲል የተናገረውን ሐሳብ በሙሉ ትምክህት እናውጃለን:- “ጽድቅ የሚኖርበትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በተስፋ ቃሉ መሠረት እንጠባበቃለን።”—2 ጴጥ. 1:4, 10, 11, 19፤ 3:13፤ ኢሳ. 65:17, 18

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ