ጥናት 20
ግቡን የሚመታ መደምደሚያ
መክብብ 12:13, 14
ፍሬ ሐሳብ፦ መደምደሚያህ፣ አድማጮችህ ትምህርቱን አምነው እንዲቀበሉና እርምጃ እንዲወስዱ የሚያነሳሳ መሆን ይኖርበታል።
ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
መደምደሚያህ ካነሳኸው ርዕሰ ጉዳይ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ መሆን ይኖርበታል። ስታብራራቸው የነበሩትን ዋና ዋና ነጥቦችና ጭብጡን ደግመህ መናገር አሊያም በሌላ አባባል መጥቀስ ትችላለህ።
አድማጮችህን ለተግባር አነሳሳቸው። አድማጮችህ ሊወስዱት የሚገባው እርምጃ ምን እንደሆነ እንዲሁም ይህን ማድረግ ያለባቸው ለምን እንደሆነ ግለጽ። ትምህርቱ አስፈላጊ እንደሆነ እንዲሁም የምትናገረውን ነገር ከልብህ እንደምታምንበት በሚያሳይ መንገድ ተናገር።
መደምደሚያህ አጭርና ያልተወሳሰበ ይሁን። አዳዲስ ዋና ዋና ነጥቦችን አታንሳ። በተቻለህ መጠን ጥቂት ቃላት ተጠቅመህ አድማጮችህን ለተግባር አነሳሳቸው።