የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • scl ገጽ 52-54
  • በዓላት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በዓላት
  • ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
scl ገጽ 52-54

በዓላት

ክርስቲያኖች የሚያከብሯቸው በዓላት

ክርስቲያኖች እንዲያከብሩት የታዘዙት ብቸኛው በዓል የቱ ነው?

ሉቃስ 22:19፤ 1ቆሮ 11:23-26

የአምላክ አገልጋዮች ለአምልኮ መሰብሰብ ያስደስታቸዋል

ዘዳ 31:12፤ ዕብ 10:24, 25

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 30:1, 6, 13, 14, 18-27 —ንጉሥ ሕዝቅያስ፣ ፋሲካ በድምቀት እንዲከበር ዝግጅት አደረገ

ክርስቲያኖች የማያከብሯቸው በዓላት

ከሐሰት ሃይማኖት ጋር ንክኪ ያላቸውን በዓላት ማክበር የሌለብን ለምንድን ነው?

1ቆሮ 10:21፤ 2ቆሮ 6:14-18፤ ኤፌ 5:10, 11

በተጨማሪም “ሃይማኖትን መቀላቀል” የሚለውን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፀ 32:1-10—እስራኤላውያን የሐሰት ሃይማኖት ልማዶችን ከእውነተኛው ሃይማኖት ጋር ለመቀላቀል መሞከራቸው ይሖዋን አስቆጥቶታል

    • ዘኁ 25:1-9—ይሖዋ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶች አረማዊ በሆኑ ሃይማኖታዊ በዓላት በመካፈላቸውና የሥነ ምግባር ብልግና በመፈጸማቸው ቀጥቷቸዋል

ገና የክርስቲያኖች በዓል ነው?

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 2:1-5—ኢየሱስ የተወለደው የሕዝብ ቆጠራ በተካሄደበት ወቅት ነው፤ ሮማውያኑ፣ በተደጋጋሚ የሚያምፁባቸውን አይሁዳውያን ለዚህ ዓላማ ረጅም መንገድ እንዲጓዙ ያዘዟቸው በቀዝቃዛና ዝናባማ ወቅት ነው ብሎ ማሰብ የማይመስል ነው

    • ሉቃስ 2:8, 12—ኢየሱስ በተወለደበት ወቅት እረኞች ሜዳ ላይ አድረዋል፤ በቀዝቃዛው የታኅሣሥ ወር ይህን ያደርጋሉ ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ አይደለም

ክርስቲያኖች ልደት ሊያከብሩ ይገባል?

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 40:20-22—ጣዖት አምላኪው ፈርዖን ልደቱን አክብሯል፤ በዕለቱም ሰው አስገድሏል

    • ማቴ 14:6-11—የክርስቶስ ተከታዮች ጠላት የሆነው ክፉው ንጉሥ ሄሮድስ ልደቱን ባከበረበት ዕለት መጥምቁ ዮሐንስ እንዲገደል አድርጓል

የሙሴ ሕግ የሚያዝዛቸው በዓላት

ክርስቲያኖች የሙሴ ሕግ የሚያዝዛቸውን በዓላት እንዲያከብሩ ይጠበቅባቸዋል?

ሮም 10:4፤ ኤፌ 2:15

በተጨማሪም ገላ 4:4, 5, 9-11፤ ዕብ 8:7-13፤ 9:1-3, 9, 10, 24⁠ን ተመልከት

ክርስቲያኖች ሳምንታዊውን ሰንበት እንዲያከብሩ ይጠበቅባቸዋል?

ቆላ 2:16, 17

በተጨማሪም ዘፀ 31:16, 17⁠ን ተመልከት

ብሔራዊ በዓላት

ክርስቲያኖች በአንድ አገር ታሪክ ውስጥ ወሳኝ ፖለቲካዊ ክንውኖች በሚታሰቡባቸው በዓላት ላይ መካፈላቸው ተገቢ ነው?

ዮሐ 15:19፤ 18:36፤ ያዕ 4:4

በተጨማሪም “መንግሥታት—ክርስቲያኖች ገለልተኞች ናቸው” የሚለውን ተመልከት

ክርስቲያኖች በአገራት መካከል የተደረጉ ጦርነቶችን በሚዘክሩ በዓላት ላይ መካፈላቸው ተገቢ ነው?

መዝ 11:5፤ ኢሳ 2:4

በተጨማሪም “መንግሥታት—ክርስቲያኖች ገለልተኞች ናቸው” እና “ጦርነት” የሚለውን ተመልከት

ክርስቲያኖች ለታዋቂ ሰዎች አምልኮ አከል ክብር በሚሰጡ በዓላት ላይ መካፈላቸው ተገቢ ነው?

ዘፀ 20:5፤ ሮም 1:25

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 12:21-23—ቀዳማዊ ንጉሥ ሄሮድስ አግሪጳ ከሕዝቡ የተሰጠውን አምልኮ አከል ክብር በመቀበሉ አምላክ ቀጥቶታል

    • ሥራ 14:11-15—ሐዋርያቱ በርናባስና ጳውሎስ፣ ተገቢ ያልሆነና ከልክ ያለፈ ክብር ሲሰጣቸው ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑም

    • ራእይ 22:8, 9—የይሖዋ መልአክ፣ አምልኮ አከል ክብር ሲሰጠው ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ