የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • scl ገጽ 43-45
  • ራስን መወሰን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ራስን መወሰን
  • ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
scl ገጽ 43-45

ራስን መወሰን

ራሳችንን ለይሖዋ አምላክ ለመወሰን ሊያነሳሳን የሚገባው ትክክለኛው የልብ ዝንባሌ ምንድን ነው?

ዘዳ 6:5፤ ሉቃስ 10:25-28፤ ራእይ 4:11

በተጨማሪም ዘፀ 20:5⁠ን ተመልከት

አምላክን ማገልገል የምንፈልግ ከሆነ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት ሊኖረን ይገባል?

መዝ 119:105፤ 1ተሰ 2:13፤ 2ጢሞ 3:16

በተጨማሪም ዮሐ 17:17፤ ዕብ 4:12⁠ን ተመልከት

አምላክ እኛን ከኃጢአት ነፃ ስለሚያወጣበት መንገድ ምን አምነን መቀበል ይኖርብናል?

ዮሐ 14:6፤ ሥራ 4:12፤ ሮም 3:23፤ ገላ 1:4፤ ኤፌ 1:7

በቀድሞ ሕይወታችን ለፈጸምናቸው መጥፎ ነገሮች ንስሐ መግባት ምን ማድረግ ይጠይቃል?

ሥራ 3:19፤ 26:20

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 19:1-10—የቀረጥ ሰብሳቢዎች አለቃ የሆነው ዘኬዎስ ቀደም ሲል ይፈጽም ከነበረው የማጭበርበር ድርጊት ንስሐ ገብቷል፤ ቀምቶ ለወሰደውም ካሳ ከፍሏል

    • 1ጢሞ 1:12-16—ሐዋርያው ጳውሎስ የቀድሞ መጥፎ አኗኗሩን ሙሉ በሙሉ እንደተወ እንዲሁም በአምላክና በክርስቶስ ምሕረት ይቅርታ እንዳገኘ ተናግሯል

መጥፎ ነገር ማድረጋችንን ከመተው በተጨማሪ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?

ሮም 12:1, 2፤ ኤፌ 4:17, 18, 22-24፤ 1ተሰ 1:9

አምላክን ተቀባይነት ባለው መንገድ ለማምለክ የትኞቹን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መታዘዝ ይኖርብናል?

1ቆሮ 6:9-11፤ ቆላ 3:5-9፤ 1ጴጥ 1:14, 15፤ 4:3, 4

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ቆሮ 5:1-13—ሐዋርያው ጳውሎስ በጉባኤው ውስጥ ዓይን ያወጣ ብልግና የፈጸመን አንድ ሰው ከመካከላቸው እንዲያስወጡት ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች መመሪያ ሰጥቷል

    • 2ጢሞ 2:16-19—ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተመረዘ ቁስል ከሚሰራጨው የከሃዲዎች ንግግር እንዲርቅ ጢሞቴዎስን አሳስቦታል

የአምላክ አገልጋዮች ከዚህ ዓለም ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ምን አቋም ሊኖራቸው ይገባል?

ኢሳ 2:3, 4፤ ዮሐ 15:19

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዮሐ 6:10-15—ኢየሱስ በተአምር ብዙ ሕዝብ ከመገበ በኋላ ሕዝቡ ሊያነግሡት ፈለጉ፤ ኢየሱስ ግን ትቷቸው ሄደ

    • ዮሐ 18:33-36—ኢየሱስ መንግሥቱ ከዚህ ዓለም ፖለቲካዊ ጉዳዮች ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ተናግሯል

መንፈስ ቅዱስ አምላክን ለማገልገል የሚረዳን እንዴት ነው?

ዮሐ 16:13፤ ገላ 5:22, 23

በተጨማሪም ሥራ 20:28፤ ኤፌ 5:18⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 15:28, 29—በኢየሩሳሌም ያለው የበላይ አካል ከግርዘት ጋር የተያያዘ ትልቅ ውሳኔ ባደረገበት ወቅት የመንፈስ ቅዱስን አመራር አግኝቷል

ራሳችንን ወስነን ለአምላክ በምናቀርበው አገልግሎት ኢየሱስን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?

ማቴ 22:37፤ ዮሐ 4:34፤ 6:38፤ ዕብ 10:8, 9

ራሳቸውን የወሰኑ ክርስቲያኖች መጠመቅ ያለባቸው ለምንድን ነው?

ማቴ 28:19, 20፤ ሥራ 2:40, 41፤ 8:12፤ 1ጴጥ 3:21

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 3:13-17—ኢየሱስ የአባቱን ፈቃድ ለማድረግ ራሱን አቅርቧል፤ ይህንንም በጥምቀት አሳይቷል

    • ሥራ 8:26-39—ወደ ይሁዲነት የተለወጠ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነቱን ሲማር ለመጠመቅ ወሰነ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ