የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • scl ገጽ 41-43
  • ሥራ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሥራ
  • ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
scl ገጽ 41-43

ሥራ

በሥራ እና በደስታ መካከል ምን ዝምድና አለ?

መክ 2:24፤ 3:13, 22፤ ኢሳ 65:22

ጥራት ያለው ሥራ መሥራትና የተካነ ሠራተኛ መሆን ምን ጥቅሞች አሉት?

ምሳሌ 22:29

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 16:16-23—ወጣቱ ዳዊት የተካነ ሙዚቀኛ ነው የሚል ስም አትርፎ ነበር፤ ይህ ተሰጥኦው ለተረበሸው የእስራኤል ንጉሥ ጠቃሚ አገልግሎት ለመስጠት አስችሎታል

    • 2ዜና 2:13, 14—ኪራምአቢ የተካነ የእጅ ጥበብ ባለሙያ ነበር፤ በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን ባከናወነው ታላቅ የግንባታ ሥራ ጠቃሚ አገልግሎት መስጠት ችሏል

የይሖዋ አገልጋዮች በምን ዓይነት የሥራ ባሕል መታወቅ ይፈልጋሉ?

ኤፌ 4:28፤ ቆላ 3:23

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 24:10-21—ርብቃ የአብርሃም አገልጋይ ከጠየቃት ነገር በላይ አድርጋለች፤ ሌሎችን መርዳት እንደምትፈልግና ታታሪ እንደሆነች አሳይታለች

    • ፊልጵ 2:19-23—ወጣቱ ጢሞቴዎስ በትጋት ለመሥራትና ሌሎችን በትሕትና ለማገልገል ፈቃደኛ ነበር፤ በመሆኑም ሐዋርያው ጳውሎስ ከባድ ኃላፊነት በአደራ ሰጥቶታል

የአምላክ አገልጋዮች ስንፍናን ለማስወገድ የሚጥሩት ለምንድን ነው?

ምሳሌ 13:4፤ 18:9፤ 21:25, 26፤ መክ 10:18

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ምሳሌ 6:6-11—ንጉሥ ሰለሞን ጉንዳንን እንደ ምሳሌ አድርጎ በመጠቀም ተግቶ ስለ መሥራትና ስንፍናን ስለ ማስወገድ ትምህርት ሰጥቷል

ራሳችንን ለማስተዳደር ተግተን መሥራት ያለብን ለምንድን ነው?

2ተሰ 3:10-12፤ 1ጢሞ 5:18

በእኛ ሥር ያሉ የቤተሰባችንን አባላት ለማስተዳደር ተግተን መሥራት ያለብን ለምንድን ነው?

1ጢሞ 5:8

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሩት 1:16, 17፤ 2:2, 3, 6, 7, 17, 18—ወጣቷ መበለት ሩት፣ አማቷን ናኦሚን ለመንከባከብ በትጋት ሠርታለች

    • ማቴ 15:4-9—ኢየሱስ፣ ወላጆቻቸውን የመጦር ኃላፊነታቸውን ላለመወጣት መንፈሳዊ ነገሮችን ሰበብ የሚያደርጉ ሰዎችን አውግዟል

ክርስቲያኖች ተግተው በመሥራት ያገኙትን ነገር ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?

ሮም 12:13፤ 2ቆሮ 8:1-4፤ 9:5, 7, 11፤ 1ጢሞ 6:17, 18

ከሥራችን ለምናገኘው ገቢ ምን ሚዛናዊ አመለካከት ሊኖረን ይገባል?

ምሳሌ 30:8፤ 2ተሰ 3:12፤ 1ጢሞ 6:6-10፤ ዕብ 13:5

ይሖዋ ሥራችንን ጥሩ አድርገን ለማከናወንና በቁሳዊ የሚያስፈልገንን ነገር ለማግኘት እንደሚረዳን እንዴት እናውቃለን?

ማቴ 6:25, 30-32፤ ሉቃስ 11:2, 3፤ 2ቆሮ 9:10

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 31:3-13—ላባ አማቹን ያዕቆብን ቀጥሮ ሲያሠራው አግባብ ያልሆነ ነገር አድርጎበታል፤ ይሖዋን ግን የያዕቆብን ልፋት አይቶ ባርኮታል

    • ዘፍ 39:1-6, 20-23—ዮሴፍ በጶጢፋር ቤት ውስጥ ባሪያ በነበረበት ወቅትም ይሁን ታስሮ ሳለ በትጋት ያከናወነውን ሥራ ይሖዋ ባርኮለታል

ሰብዓዊ ሥራችንን ለአምላክ ከምናቀርበው አገልግሎት ማስቀደም የሌለብን ለምንድን ነው?

መዝ 39:5-7፤ ማቴ 6:33፤ ዮሐ 6:27

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 12:15-21—ኢየሱስ ቁሳዊ ነገሮችን ከመንፈሳዊ ሀብት ማስቀደም ሞኝነት እንደሆነ በምሳሌ አስተምሯል

    • 1ጢሞ 6:17-19—ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ሀብታም የሆኑ ክርስቲያኖች እንዳይታበዩ ከዚህ ይልቅ “በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ” አሳስቧል

ሥራ ስንመርጥ በየትኞቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች ልንመራ ይገባል?

  • ዘፀ 20:4፤ ሥራ 15:29፤ ኤፌ 4:28፤ ራእይ 21:8—ሥራው አምላክ የሚያወግዘውን ነገር እንዳደርግ ይጠይቅብኛል?

  • ዘፀ 21:22-24፤ ኢሳ 2:4፤ 1ቆሮ 6:9, 10፤ 2ቆሮ 7:1—ሥራው አምላክ የሚያወግዘውን ነገር የሚደግፍ ወይም የሚያበረታታ ነው? ይህስ እኔን የኃጢአቱ ተባባሪ ያደርገኝ ይሆን?

  • ሮም 13:1-7፤ ቲቶ 3:1, 2—ሥራው መንግሥት ያወጣውን ሕግ ያስጥሰኛል?

  • 2ቆሮ 6:14-16፤ ራእይ 18:2, 4—ሥራው የሐሰት ሃይማኖት ክፍል ወይም ተባባሪ ያደርገኛል?

ለይሖዋ መሥራት

ክርስቲያኖች የሚሳተፉበት ከሁሉ ይበልጥ አስፈላጊው ሥራ ምንድን ነው?

ማቴ 28:19, 20፤ ሉቃስ 9:2፤ 2ጢሞ 4:2, 5

በይሖዋ አገልግሎት ምርጣችንን ለመስጠት የምንፈልገው ለምንድን ነው?

ሉቃስ 13:24፤ ሮም 12:11፤ 1ቆሮ 15:58፤ ዕብ 6:10-12

በተጨማሪም 1ጢሞ 3:1⁠ን ተመልከት

ሁሉም ሰው በይሖዋ አገልግሎት ተመሳሳይ መጠን ያለው ሥራ እንደሚሠራ መጠበቅ የሌለብን ለምንድን ነው?

ገላ 6:3-5

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 25:14, 15—ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ እንደሚያሳየው ሁሉም ተከታዮቹ ተመሳሳይ መጠን ያለው ሥራ እንዲያከናውኑ አይጠብቅም

    • ሉቃስ 21:2-4—ኢየሱስ፣ አንዲት ድሃ መበለት ያደረገችው አነስተኛ መዋጮ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ተናግሯል

በይሖዋ አገልግሎት የተሰጠንን ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ብርታት ከየት ማግኘት እንችላለን?

2ቆሮ 4:7፤ ኤፌ 3:20, 21፤ ፊልጵ 4:13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ጢሞ 4:17—ሐዋርያው ጳውሎስ ኃይል ባስፈለገው ሰዓት የሚያስፈልገውን ኃይል እንዳገኘ ተናግሯል

በይሖዋ አገልግሎት በትጋት መሥራት ደስታ የሚያስገኘው ለምንድን ነው?

መዝ 40:8፤ ዮሐ 13:17፤ ያዕ 1:25

በተጨማሪም ማቴ 25:23⁠ን ተመልከት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ