የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • scl ገጽ 111-114
  • ጸሎት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጸሎት
  • ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
scl ገጽ 111-114

ጸሎት

ይሖዋ ጸሎትን እንደሚሰማና መልስ እንደሚሰጥ በምን እናውቃለን?

መዝ 65:2፤ 145:18፤ 1ዮሐ 5:14

በተጨማሪም መዝ 66:19፤ ሥራ 10:31፤ ዕብ 5:7⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ነገ 18:36-38—ነቢዩ ኤልያስ በቀርሜሎስ ተራራ ላይ የባአል ነቢያትን በተገዳደረበት ወቅት ጸሎት አቅርቧል፤ ይሖዋም ለጸሎቱ አፋጣኝ መልስ ሰጥቶታል

    • ማቴ 7:7-11—ኢየሱስ ደጋግመን እንድንጸልይ አበረታቶናል፤ እንዲሁም አፍቃሪው አባታችን ይሖዋ እንደሚሰማን ዋስትና ሰጥቶናል

ክርስቲያኖች መጸለይ ያለባቸው ወደ ማን ብቻ ነው?

መዝ 5:1, 2፤ 69:13፤ ማቴ 6:9፤ ፊልጵ 4:6

የምንጸልየው በማን ስም ነው?

ዮሐ 15:16፤ 16:23, 24

ይሖዋ የሚሰማው የእነማንን ጸሎት ነው?

ሥራ 10:34, 35፤ 1ጴጥ 3:12፤ 1ዮሐ 3:22፤ 5:14

ይሖዋ የማይሰማው የእነማንን ጸሎት ነው?

ምሳሌ 15:29፤ 28:9፤ ኢሳ 1:15፤ ሚክ 3:4፤ ያዕ 4:3፤ 1ጴጥ 3:7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢያሱ 24:9, 10—በለዓም ከአምላክ ፈቃድ ጋር የሚጋጭ ነገር ስለጠየቀ ይሖዋ አልሰማውም

    • ኢሳ 1:15-17—እስራኤላውያን ግብዞችና የደም ባለዕዳ በመሆናቸው ይሖዋ ጸሎታቸውን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም

ጸሎታችንን መደምደም ያለብን ምን ብለን ነው? ለምንስ?

1ዜና 16:36፤ መዝ 41:13፤ 72:19፤ 89:52፤ 1ቆሮ 14:16

መጽሐፍ ቅዱስ በምንጸልይበት ወቅት አንድ ዓይነት አኳኋን ሊኖረን እንደሚገባ ይናገራል?

1ነገ 8:54፤ ማር 11:25፤ ሉቃስ 22:39, 41፤ ዮሐ 11:41

በተጨማሪም ዮናስ 2:1⁠ን ተመልከት

የይሖዋ አገልጋዮች ለአምልኮ ሲሰበሰቡ ስለ የትኞቹ ጉዳዮች መጸለይ ይችላሉ?

ሥራ 4:23, 24፤ 12:5

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ዜና 29:10-19—ሕዝቡ ለቤተ መቅደሱ ግንባታ በፈቃደኝነት መዋጮ ባመጡበት ወቅት ንጉሥ ዳዊት የተሰበሰበውን የእስራኤል ጉባኤ ወክሎ ጸልዮአል

    • ሥራ 1:12-14—ሐዋርያት፣ የኢየሱስ ወንድሞች፣ የኢየሱስ እናት ማርያምና አንዳንድ ታማኝ ሴቶች በኢየሩሳሌም በሚገኝ ደርብ ላይ ተሰብስበው ጸልየዋል

ጸሎት የሚያቀርብ ሰው ራሱን ከፍ ከፍ ማድረግ ወይም ሌሎችን ለማስደመም መሞከር የሌለበት ለምንድን ነው?

ማቴ 6:5፤ ሉቃስ 18:10-14

በምግብ ሰዓት መጸለይ ተገቢ ነው?

ማቴ 14:19፤ ሥራ 27:35፤ 1ቆሮ 10:25, 26, 30, 31

ለሰማዩ አባታችን አዘውትረን መጸለይ ያለብን ለምንድን ነው?

ሮም 12:12፤ ኤፌ 6:18፤ 1ተሰ 5:17፤ 1ጴጥ 4:7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዳን 6:6-10—ነቢዩ ዳንኤል ሕይወቱን ሊያሳጣው እንደሚችል እያወቀም ቀድሞ ያደርግ እንደነበረው በይፋ መጸለዩን ቀጥሏል

    • ሉቃስ 18:1-8—ኢየሱስ፣ ጻድቅ አባታችን የሆነው ይሖዋ አገልጋዮቹ እርዳታ ለማግኘት በተደጋጋሚ ለሚያቀርቡት ልመና በደስታ ምላሽ እንደሚሰጥ የሚያሳይ ምሳሌ ተናግሯል፤ ምሳሌው አንዲት ሴት ፍትሕ ለማግኘት በተደጋጋሚ ላቀረበችው ጥያቄ ምላሽ ስለሰጠ ጻድቅ ያልሆነ ዳኛ የሚገልጽ ነው

አምላክ፣ ይቅርታ ለማግኘት የምናቀርበውን ጸሎት እንዲሰማን ከፈለግን ምን ዓይነት ዝንባሌ ሊኖረን ይገባል?

2ዜና 7:13, 14

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ነገ 22:11-13, 18-20—ንጉሥ ኢዮስያስ ራሱን ዝቅ አድርጓል፤ ይሖዋን ለማስደሰትም ከልቡ ጥረት አድርጓል፤ በመሆኑም ይሖዋ ታላቅ ምሕረትና ደግነት አሳይቶታል

    • 2ዜና 33:10-13—ንጉሥ ምናሴ በትሕትና ጸልዮአል፤ በመሆኑም ይሖዋ ይቅር ብሎታል፤ ወደ ንግሥናውም መልሶታል

ይሖዋ ይቅር እንዲለን ከፈለግን ምን እንድናደርግ ይጠበቅብናል?

ማቴ 6:14, 15፤ ማር 11:25፤ ሉቃስ 17:3, 4

በጸሎታችን ላይ፣ የይሖዋ ፈቃድ እንዲፈጸም መጠየቅ ያለብን ለምንድን ነው?

ማቴ 6:10፤ ሉቃስ 22:41, 42

ጸሎታችን በሰማዩ አባታችን ላይ ያለንን እምነት ሊያሳይ የሚገባው ለምንድን ነው?

ማር 11:24፤ ዕብ 6:10፤ ያዕ 1:5-7

በጸሎታችን ላይ ልንጠቅሳቸው የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

የአምላክ ስም እንዲቀደስ

ሉቃስ 11:2

የአምላክ መንግሥት እንዲመጣና መላዋን ምድር እንዲገዛ

ማቴ 6:10

የይሖዋ ፈቃድ እንዲፈጸም

ማቴ 6:10፤ 26:42

የሚያስፈልጉን ቁሳዊ ነገሮች እንዲሟሉልን

ሉቃስ 11:3

ኃጢአታችን ይቅር እንዲባል

ዳን 9:19፤ ሉቃስ 11:4

ከፈተና እንድንድን

ማቴ 6:13

ምስጋና

ኤፌ 5:20፤ ፊልጵ 4:6፤ 1ተሰ 5:17, 18

የአምላክን ፈቃድ እንድናውቅ እንዲሁም ማስተዋልና ጥበብ እንድናገኝ

ምሳሌ 2:3-6፤ ፊልጵ 1:9፤ ያዕ 1:5

በተጨማሪም መዝ 119:34⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ነገ 3:11, 12—ይሖዋ፣ ንጉሥ ሰለሞን ጥበብ ለማግኘት ባቀረበው ልመና ተደስቷል፤ ታላቅ ጥበብም ሰጥቶታል

መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጠን

ሉቃስ 11:13፤ ሥራ 8:14, 15

ስደት እየደረሰባቸው ያሉትን ጨምሮ ለእምነት አጋሮቻችን መጸለይ

ሥራ 12:5፤ ሮም 15:30, 31፤ ያዕ 5:16

በተጨማሪም ቆላ 4:12፤ 2ጢሞ 1:3⁠ን ተመልከት

ውዳሴ

መዝ 86:12፤ ኢሳ 25:1፤ ዳን 2:23

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 10:21—ኢየሱስ፣ እንደ ልጆች ትሑት ለሆኑ ሰዎች መንፈሳዊ እውነቶችን በመግለጡ አባቱን በይፋ አወድሶታል

    • ራእይ 4:9-11—በሰማይ ያለው የይሖዋ ቤተሰብ እሱ የሚገባውን ክብርና ግርማ ይሰጠዋል

ሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች አምልኳችንንና የስብከቱን ሥራችንን በሰላም ለማከናወን እንዲፈቅዱልን ይሖዋን ለመለመን

ማቴ 5:44፤ 1ጢሞ 2:1, 2

በተጨማሪም ኤር 29:7⁠ን ተመልከት

ስንጠመቅ ልንጸልይ ይገባል?

ሉቃስ 3:21

በመንፈሳዊ ለታመሙ ሰዎች መጸለይ ተገቢ ነው?

ያዕ 5:14, 15

ወንዶች ሲጸልዩ በአብዛኛው ራሳቸውን የማይሸፍኑት፣ ሴቶች ግን አንዳንድ ጊዜ ራሳቸውን ሸፍነው የሚጸልዩት ለምንድን ነው?

1ቆሮ 11:2-16

ከጸሎታችን ርዝመት ወይም አጽንኦት ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ነገር ምንድን ነው?

ሰቆ 3:41፤ ማቴ 6:7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ነገ 18:25-29, 36-39—የባአል ነቢያት፣ ነቢዩ ኤልያስ በተገዳደራቸው ወቅት ለሰዓታት ወደ አምላካቸው ጮኸዋል፤ የሰማ ግን የለም

    • ሥራ 19:32-41—በኤፌሶን ያሉ ጣዖት አምላኪዎች ለሁለት ሰዓት ያህል ወደ እንስት አምላካቸው ወደ አርጤምስ ጮኸዋል፤ ጩኸታቸው ግን የከተማዋን ዋና ጸሐፊ ወቀሳ እንጂ ሌላ ያተረፈላቸው ነገር የለም

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ