የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • scl ገጽ 114-117
  • ጽናት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጽናት
  • ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
scl ገጽ 114-117

ጽናት

የይሖዋ አገልጋዮች ጽናት ያስፈልጋቸዋል?

1ቆሮ 13:4, 7፤ 1ጢሞ 6:11፤ 2ጴጥ 1:5, 6

አንዳንዶች ለምንሰብከው መልእክት ግድየለሽ እንደሚሆኑ ይባስ ብሎም እንደሚቃወሙን መጠበቅ ያለብን ለምንድን ነው?

ማቴ 10:22፤ ዮሐ 15:18, 19፤ 2ቆሮ 6:4, 5

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ጴጥ 2:5፤ ዘፍ 7:23፤ ማቴ 24:37-39 —ኖኅ “የጽድቅ ሰባኪ” ሰባኪ ቢሆንም አብዛኞቹ ሰዎች አልሰሙትም፤ ከጥፋት ውኃው የተረፉት እሱና ቤተሰቡ ብቻ ናቸው

    • 2ጢሞ 3:10-14—ሐዋርያው ጳውሎስ የራሱን ምሳሌ በመጥቀስ ጢሞቴዎስን እንዲጸና አበረታቶታል

የቤተሰባችን አባላት እንኳ ሊቃወሙን እንደሚችሉ መጠበቅ ያለብን ለምንድን ነው?

ማቴ 10:22, 36-38፤ ሉቃስ 21:16-19

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 4:3-11፤ 1ዮሐ 3:11, 12—ቃየን የእሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ የአቤል ሥራ ግን ጽድቅ ስለነበረ ወንድሙን ገድሎታል

    • ዘፍ 37:5-8, 18-28—ዮሴፍ በወንድሞቹ ጥቃት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ለባርነት ሸጠውታል፤ ለዚህ አንዱ ምክንያት ከይሖዋ የተገለጠለትን ሕልም መናገሩ ነው

ስደት ሲደርስብን ሞትን መፍራት የሌለብን ለምንድን ነው?

ማቴ 10:28፤ 2ጢሞ 4:6, 7

በተጨማሪም ራእይ 2:10⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዳን 3:1-6, 13-18—ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ አቋማቸውን አላልተው ጣዖት ከማምለክ ይልቅ ሞትን መርጠዋል

    • ሥራ 5:27-29, 33, 40-42—ሐዋርያቱ የግድያ ዛቻ ቢሰነዘርባቸውም በስብከቱ ሥራ ጸንተዋል

ተግሣጽ በሚሰጠን ጊዜም እንኳ ለይሖዋ ታማኝ ሆነን ለመጽናት ምን ሊረዳን ይችላል?

ምሳሌ 3:11, 12፤ ዕብ 12:5-7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘኁ 20:9-12፤ ዘዳ 3:23-28፤ 31:7, 8—የይሖዋ ተግሣጽ ነቢዩ ሙሴን አሳዝኖታል፤ ሆኖም እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ጸንቷል

    • 2ነገ 20:12-18፤ 2ዜና 32:24-26—ንጉሥ ሕዝቅያስ ኃጢአት በመሥራቱ እርማት ተሰጠው፤ ሆኖም ራሱን ዝቅ ያደረገ ከመሆኑም ሌላ በቀረው ሕይወቱ በታማኝነት ጸንቷል

የሌሎች ታማኝ አለመሆን መጽናት ከባድ እንዲሆንብን ሊያደርግ የሚችለው እንዴት ነው?

ኤር 1:16-19፤ ዕን 1:2-4

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 73:2-24—መዝሙራዊው፣ ክፉዎች በሰላምና በብልጽግና እንደሚኖሩ ሲያይ ይሖዋን በጽናት ማገልገሉ ያለውን ጥቅም እስከመጠራጠር ደርሷል

    • ዮሐ 6:60-62, 66-68—ሐዋርያው ጴጥሮስ ብዙዎች ኢየሱስን መከተላቸውን ቢያቆሙም እንኳ በእምነቱ ለመጽናት ቆርጧል

ለመጽናት ምን ይረዳናል?

ከይሖዋ ጋር መጣበቅ

ዘዳ 30:19, 20፤ ሮም 15:5, 6፤ 1ቆሮ 10:13

የአምላክን ቃል በማጥናትና በማሰላሰል እውቀት ማግኘት

መክ 7:12፤ ሮም 15:4፤ ቆላ 1:10, 11፤ 2ጴጥ 3:15-18

ለይሖዋ አዘውትሮ ከልብ የመነጨ ጸሎት ማቅረብ

ሮም 12:12፤ ቆላ 4:2፤ 1ጴጥ 4:7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዳን 6:4-11—ነቢዩ ዳንኤል ሕይወቱን ለማጥፋት ሴራ እንደተጠነሰሰበት ቢያውቅም በይፋ አዘውትሮ መጸለዩን ቀጥሏል

    • ማቴ 26:36-46፤ ዕብ 5:7—ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው የመጨረሻ ምሽት አጥብቆ ጸልዮአል፤ ሌሎችም እንዲህ እንዲያደርጉ አሳስቧል

ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ይሖዋን ለማምለክ አዘውትረን መሰብሰብ

ሮም 1:11, 12፤ ዕብ 10:23-25

አእምሯችን ይሖዋ ቃል በገባልን ሽልማት ላይ እንዲያተኩር ማድረግ

ሮም 8:25፤ 1ተሰ 1:3፤ ዕብ 11:6፤ 12:1, 2

ለይሖዋ፣ ለክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም ለጽድቅ ያለንን ፍቅር ማጠናከር

ማቴ 6:33፤ 1ቆሮ 13:4-7፤ 1ተሰ 3:12, 13፤ 1ዮሐ 4:18, 19

እምነታችንን ማጠናከር

ኤፌ 6:16፤ 1ዮሐ 5:4፤ ይሁዳ 20, 21

ለችግሮቻችን ትክክለኛውን አመለካከት ማዳበር

ሥራ 5:40, 41፤ ያዕ 1:2-4፤ 1ጴጥ 3:14፤ 4:14, 16

በታማኝነት መጽናት ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው?

ይሖዋ አምላክን እናስከብራለን

ምሳሌ 27:11፤ ዮሐ 15:7, 8፤ 1ጴጥ 1:6, 7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢዮብ 1:6-12፤ 2:3-5—ሰይጣን በኢዮብ ንጹሕ አቋም ጠባቂነት ላይ በይሖዋ ፊት ጥያቄ አነሳ፤ ጥያቄው መልስ ማግኘት የሚችለው ኢዮብ በታማኝነት ከጸና ብቻ ነው

    • ሮም 5:19፤ 1ጴጥ 1:20, 21—ከአዳም በተቃራኒ ኢየሱስ በታማኝነት ጸንቷል፤ ይህም ‘አንድ ፍጹም ሰው እስከ መጨረሻው ቢፈተን ንጹሕ አቋሙን መጠበቅ ይችላል?’ ለሚለው ወሳኝ ጥያቄ መልስ አስገኝቷል

ሌሎችም እንዲጸኑ እናበረታታለን

ፊልጵ 1:13, 14፤ ያዕ 5:10, 11

ጽናት አገልግሎታችን ፍሬያማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደርጋል

መክ 11:6፤ ሉቃስ 8:15፤ 2ጴጥ 1:5-8

በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት እንዲሁም ቃል የተገቡልንን ሽልማቶች እናገኛለን

ማቴ 24:13፤ ሉቃስ 21:19፤ 1ቆሮ 15:58፤ ዕብ 10:36

በተጨማሪም ሮም 2:6, 7፤ ያዕ 1:12⁠ን ተመልከት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ