ጽድቅ
ትክክል ወይም ፍትሐዊ የሆነውን ነገር የመወሰን ሥልጣን ያለው ማን ብቻ ነው?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዘፍ 18:23-33—ይሖዋ፣ ጻድቅ ዳኛ መሆኑን ለአብርሃም አሳይቶታል
መዝ 72:1-4, 12-14—በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ይህ መዝሙር፣ የይሖዋን ጽድቅ ፍጹም በሆነ መንገድ የሚያንጸባርቀውን መሲሐዊውን ንጉሥ ያወድሳል
የይሖዋን የጽድቅ መሥፈርቶች አክብረን መኖራችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል?
መዝ 37:25, 29፤ ያዕ 5:16፤ 1ጴጥ 3:12
በተጨማሪም መዝ 35:24፤ ኢሳ 26:9፤ ሮም 1:17ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ኢዮብ 37:22-24—ኤሊሁ፣ ይሖዋን በጽድቁ አወድሶታል፤ የይሖዋ ጽድቅ አገልጋዮቹ ለእሱ ጥልቅ አክብሮት እንዲያድርባቸው ያደርጋል
መዝ 89:13-17—መዝሙራዊው፣ አገዛዙ በጽድቅ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ይሖዋን አወድሶታል
የአምላክን ጽድቅ መፈለግ ሲባል ምን ማለት ነው?
ሌሎችን ለማስደመም ብለን ሳይሆን ለይሖዋ ባለን ፍቅር ተነሳስተን ጻድቅ ለመሆን ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?
ማቴ 6:1፤ 23:27, 28፤ ሉቃስ 16:14, 15፤ ሮም 10:10
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ማቴ 5:20፤ 15:7-9—ኢየሱስ፣ ሕዝቡ ጻድቅ እንዲሆኑ ሆኖም ጽድቃቸው ግብዝ የሆኑት ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ባወጡት መሥፈርት መሠረት እንዳይሆን አስተምሯል
ሉቃስ 18:9-14—ኢየሱስ፣ ራሳቸውን በማመጻደቅ ጻድቅ መስለው ለመታየት የሚሞክሩ ሰዎችን ለማረም አንድ ምሳሌ ተናግሯል
ጥሩነት ከጽድቅም እንኳ የሚበልጠው ለምንድን ነው?
በተጨማሪም ሉቃስ 6:33-36፤ ሥራ 14:16, 17፤ ሮም 12:20, 21፤ 1ተሰ 5:15ን ተመልከት