ለምድር አቀፉ የሰብል መሰብሰብ ሥራ የሚያገለግሉ ተጨማሪ ሚስዮናውያን
መስከረም ለገበሬዎች የሰብል መሰብሰቢያ ወር ነው፤ ነገር ግን መስከረም 8, 1991 በጣም ብዙ ሰዎች በኒውዮርክ ክፍለ ሀገር ከሁድልስ ወንዝ ማዶ በጀርሲ ከተማ በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ትልቅ ስብሰባ አዳራሽ ከዚህ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ የሰብል ስብሰባ ጉዳይ ስቧቸው ተሰብስበዋል። 91ኛውን የጊልያድ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚመረቁበት ቀን ነበር። 4,263 የቤቴል ቤተሰብ አባሎችና የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተው ነበር። ሌሎች 1,151 በብሩክሊን ዋና መሥሪያ ቤትና በዎልክሂልና ፓተርሰን የእርሻ ቦታ የሚሠሩ ደግሞ በቴሌፎን መሥመር ተገናኝተው ነበር።
ዕድሜው ወደ 98 ዓመት የተጠጋው የጊልያድ ትምህርት ቤት ፕሬዘዳንት ፍሬዴሪክ ደብልዩ ፍራንዝ ፕሮግራሙን በጣም ልብ በሚነካና ጥልቅ አክብሮ በተሞላበት ጸሎት ከፈተ። የአስተዳደር አካሉ አባልና የቀድሞ ሬጅስትራርና የትምህርት ቤቱ አስተማሪ የነበረው አልበርት ዲ ሽሮይደር የምረቃ ፕሮግራሙ ሊቀመንበር በመሆን አገልግሎአል። እሱም አድማጮቹ ስለ መዝሙር 2: 1,2 እና በሕዝብ መካከል ስላለው መናወጥና ማጉረምረም ትንቢት የሚናገሩ ሌሎች ትንቢቶችን አስታወሳቸው።ይህ መናወጥም ለሰብል ስብሰባው ሥራ ብዙ አዳዲስ መስኮች እንዲከፈቱ አስችሏል።
የዕለቱ የመጀመሪያ ንግግር የቀረበው የቤቴል ኮሚቴ አባል በሆነው በጆርጅ ኤም ኮች ነበር። የእርሱ ርዕስ “በረከቶቻችሁን ቁጠሩ” የሚል ነበር። ‘በረከቶቻቸውን የሚቆጥሩበት’ ጊዜ ገና እንዳልደረሰ አድርገው እንዳያስቡ ለጊልያድ ተማሪዎች አሳሰባቸው። ተማሪዎቹ በእርግጥ እንደተባረኩና እነዚህንም በረከቶች ሊያገኙ የቻሉት ከብዙ ከባድ ጥረቶች በኋላ መሆኑን ተናገረ። ያዕቆብም በተመሳሳይ በ97 ዓመት ዕድሜው በረከት ለማግኘት ሌሊቱን በሙሉ ከመልአክ ጋር ሲታገል አድሯል። (ዘፍጥረት 32:24-32) ወንድም ኮች ተማሪዎቹ አፍራሽ አስተሳሰብ እንዳያሳድሩና በጸሎትና በቆራጥነት የአእምሮ ሰላምን በመኮትኮት ለሌሎች በረከት ይሆኑ ዘንድ በጥብቅ አሳሰባቸው።
ቀጥሎ የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ጆን ኢ ባር “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ይኑራችሁ” በሚል ርዕስ ጉዳይ ላይ ንግግር አደረገ። የኢየሱስ ተከታዮች አንዱ ለሌላው ለመሞት ፈቃደኞች ነበሩ። “እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር ከውስጣችሁ ሲፈልቅ ይሰማችኋልን?” በማለት ተማሪዎቹን ጠየቃቸው። “ይህ ዓይነቱ ፍቅር ከሌለን ከንቱ ነን። ሌላ ምንም ሊባል አይችልም” አላቸው። (1 ቆሮንቶስ 13:3) ወንድም ባር ፍቅር የሚገለጽባቸውን አንዳንድ ተግባራዊ መንገዶች ዘረዘረ። ተማሪዎቹን ሌሎች ሚስዮናውያንን በአክብሮት እንዲይዙ፣ በሚናገሩበት ጊዜም ሁልጊዜ በዘዴ እንዲናገሩ አበረታታቸው። 1 ጴጥሮስ 4:8ን ጠቅሶ “ጥቃቅን ግጭቶችን ችላ በሉአቸው” በማለት መከራቸው። ሚስዮናውያኑ ምግብ ለማብሰል ተረኛ የሚሆኑባቸው ቀኖች እንኳ ሥራውን የይድረስ ይድረስ መሠራት እንዳለበት የግዳጅ ሥራ አድርገው ባለመመልከት ፍቅር የሚያሳዩባቸው ወቅቶች እንደሆኑ ገለጸ። “ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን የፍቅር ዕዳችንን መክፈላችንን ፈጽሞ አናቋርጥ” በማለት ተማሪዎቹን አሳሰባቸው። —ሮሜ 13:8
የአገልግሎት ክፍል ኮሚቴ አባል የሆነው ዴቪድ ኤ ኦልሰን ያቀረበው አስደሳች ርዕሰ ትምህርት “ምን ያህል እርግጠኝነት ወይም ትምክህት አላችሁ?” የሚል ነበር። እሱም ሁለት ትምክህት የሚጣልባቸው አለኝታዎችን ማለት ይሖዋንና ድርጅቱን ጎላ አድርጎ ገለጸ። ለዚህም ብዙ ምክንያት አለን። (ምሳሌ 14:6፤ ኤርምያስ 17:8) ሌላው ልንተማመንበት የሚገባን በራሳችን ነው። ሚስዮናውያን በነበራቸው የአገልጋይነት ችሎታና ይሖዋና ድርጅቱ በጣሉባቸው እምነትና በመሳሰሉት ምክንያቶች የተነሣ በራስ የመተማመን ስሜት አላቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ በተመሳሳይ ምክንያቶች እንዲህ ዓይነቱን ትምክህት አሳይቷል። (1 ቆሮንቶስ 16:13፤ ፊልጵስዮስ 4:13) ሆኖም ወንድም ኦልሰን “አዘውትሬ የምጠቅሰው ራሴን ነው፤ ይህም ለጭውውቴ ቅመም ይጨምርለታል” በማለት በገለጻቸው ታዋቂ ጸሐፊ እንደተንጸባረቀው ካለውና ዓለም ከሚያስፋፋው ከልክ በላይ የሆነ በራስ የመተማመን መንፈስ እንዲጠበቁ አስጠነቀቀ። ይሁን እንጂ ትሕትና በታከለበት ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በሌሎችም እንድንተማመን ሊገፋፋን ይችላል። በጳውሎስ ረገድ ይህ በእርግጥ እውነት ነበር። —ፊልጵስዮስ 1:12-14
ቀጥሎ የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ሊማን ኤ ስዊንግል ተማሪዎቹን “እናንተ የጊልያድ ምሩቃን ለመሰብሰብ ወደደረሱት የሰብል ማሣዎች ሂዱ!” በማለት አጥብቆ አሳሰባቸው። ምሩቃኑ ሄደው አብረው የሚሠሩት በ1940ዎቹ ዓመታት በመጀመሪያው፣ በሁለተኛውና በሦስተኛው ኮርስ የተመረቁትን ጥቂቶች ጨምሮ እስከ አሁን በሚስዮናዊነት ሥራ ላይ ከቆዩ በሺዎች ከሚቆጠሩ ቀደም ያሉ ምሩቃን ጋር ስለሆነ ይህ ዕለት ራሱ ለጊልያድ ትምህርት ቤትና ለዓለም አቀፉ ወንድማማችነት ሰብል የመሰበሰብ ቀን መሆኑን ተናገረ። ወንድም ስዊንግል በ1940ዎቹ ዓመታት የሚስዮናዊነቱ ሥራ ለተጨማሪ 50 ዓመታት እንደሚቀጥል ወይም ናዚዝም፣ ፋሺዝምና ለስብከቱ ሥራ እንቅፋት የሚሆኑ መንግሥታዊ መሰናክሎች እንደሚወገዱ ያሰበ እንዳልነበረ ተናገረ። “ይሖዋ ከዚህ በፊት ባደረጋቸው ነገሮች ከተደነቅን ለወደፊቱስ?” በማለት ጠየቀ። ንግግሩንም ለተማሪዎቹ ቀስቃሽ በሆነ “ወደ ማሳው ሂዱ!” በሚል ጥሪ ደመደመ።
ከዚያም ሁለቱ የጊልያድ ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ለ91ኛው ኮርስ ተካፋዮች የመጨረሻ ንግግር አደረጉላቸው። ጃክ ዲ ሬድፎርድ “ጥበብን አግኙ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ንግግር አደረገ። ጊልያድ ትምህርት ቤት እውቀትና ማስተዋል እንደሚያስተምርና እውቀታቸውን በተገቢው መንገድ የመጠቀም ችሎታ የሆነውን ጥበብ ማግኘት እንዳለባቸው ለተማሪዎቹ ነገራቸው። በጊልያድ ትምህርት ቤት ሁሉን ነገር እንዳወቁ የማሰብ የተሳሳተ እምነት እንዳይኖራቸው አጥብቆ አስገነዘባቸው። “ዋጋ ያለው ከትምህርት ቤቱ ከወጣችሁ በኋላ የምትማሩአቸው ነገሮች ናቸው።” ገና ወደፊት መማር ካለባቸው ነገሮች መካከል ከሰዎች ጋር በሰላም አብሮ መሥራት፣ ወይም መኖር፣ ለትዳር ጓደኛ ወይም ለአገልግሎት ጓደኛ ወይም ለመሰል ሚስዮናውያንና በአካባቢው ላሉ ወንድሞችና እህቶች “ይቅርታ አድርጉልኝ” ማለት መቻል፣ የመጀመሪያ ግምታቸውን መጠራጠር፣ ወይም ግምታቸው ትክክል ላይሆን እንደሚችል ማሰብ፣ ማንኛውም ችግር ውስብስብ መሆኑንና የጥበብ ምክር ከመስጠት በፊት ሁኔታዎችን በጥልቅ መረዳት የሚያስፈልግ መሆኑን መገንዘብና የአካባቢው ወንድሞች በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ አልፈው በመዝለቅ ያሳዩትን ችሎታ ማክበርና የመሳሰሉት ሁሉ ይገኙበታል።—ምሳሌ 15:28፤ 16:23፤ ያዕቆብ 1:19
የጊልያድ ትምህርት ቤት ሬጅስትራር የሆነው ዩሊስስ ግላስ ርዕስ ያደርገው ፊልጵስዮስ 3:16ን ነበር። ላደረጉት መሻሻል ተማሪዎቹን አመሰገነና ከዚህ ጥቅስ ጋር ተስማምተው መሻሻላቸውን እንዲቀጥሉ አጥብቆ መከራቸው። ተማሪዎቹ ትክክለኛ ዕውቀት በማግኘት መቀጠል ያለባቸው ሲሆን ሁሉንም ነገር ሊያውቁ እንደማይችሉ ገለጸ። ነጥቡን ለማብራራት የኤሌክትሮኒክ ሰዓት ምሳሌ አቀረበ። ይህ ሰዓት ያለው ሰው ሰዓቱ በእርግጥ የሚሠራው እንዴት እንደሆነ ባውቅም ሰዓቱ ማድረግ ይችላል። በተመሳሳይም ሚስዮናውያን በዕውቀት ጥልቀት ከእነሱ ጋር የማይተካከሉትን ሆኖም አስፈላጊ የሆነውን ይሖዋን መፍራት የሚያውቁትን ሰዎች መናቅ የለባቸውም። (ምሳሌ 1:7) ተማሪዎቹን ‘ጤናማ ወይም ያልተወሳሰበ ዓይን’ እንዲኖራቸው አሳሰባቸው። (ማቴዎስ 6:22) መንፈሳዊው ዓይን እንደ ሥጋዊው ዓይን ሊታመም ወይም እክል ሊገጥመው ይችላል። ለምሳሌ ያህል አንዳንዶች የእይታቸው አድማስ በጣም ጠባብ በመሆኑ ምክንያት በጥቂት ዝርዝር ጉዳዮች ላይ አተኩረው ጠቅላላውን ጉዳይ ማስተዋል የሚያቅታቸው ሲሆን ሌሎች ደግሞ ውጭ ውጭ ያሉትን ነገሮች ብቻ ስለሚመለከቱ አስፈላጊ የሆነውን ቁልፍ ጉዳይ ሳይገነዘቡ ይቀራሉ።
የጧቱ የመጨረሻ ንግግር የቀረበው የአስተዳደር አካል አባል በሆነው በቲዮዶር ጃራዝ ሲሆን ርዕሱ “የይሖዋን ድርጅት ለይቶ ማወቅና አብሮ መሥራት” የሚል ነበር። ወንድም ጃራዝ በዓለም ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ድርጅቶችና ማህበሮች ያሉ መሆናቸውንና ከእነዚህ ሁሉ አንዱ ብቻ ምንጩ ከዚህ ዓለም ያለመሆኑን ተናገረ። ይሖዋን የሚወክለው ድርጅት የሚታወቀው እንዴት ነው? የአምላክ ቃል የሚታወቅበትን ምልክቶች ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ የይሖዋ ሰማያዊ ፍጥረት በከፍተኛ ሁኔታ የተደራጀ መሆኑን ይገልጻል። (መዝሙር 103:20, 21፤ ኢሳይያስ 40:26) የይሖዋ ምድራዊ ድርጅትም ተለይቶ የሚታወቀው በሥርዓታማነቱ፣ እንዲሁም ከዓለም የተለየ በመሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥርዓቶች አጥብቆ በመያዙ፣ በከፍተኛ የሥነ ምግባር ንጽሕና ደረጃውን በአባሎቹ መሃል ባለው ፍቅር ነው። ወንድም ጃራዝ የጊልያድ ተማሪዎች በሚመደቡባቸው አገሮች በቅዱስ ጽሑፉ በመጠቀም በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች የይሖዋን ድርጅት ለይተው እንዲያውቁ እንዲረዱ አጥብቆ አሳሰባቸው። ከዚህ ጋር አያይዞ የጊልያድ ትምህርት ቤት በ93ኛው ኮርስ ጀምሮ እስካሁን የሚቀበላቸውን እጥፍ በማድረግ 50 ተማሪዎችን የሚቀበል መሆኑን የሚገልጽ አስደሳች ማስታወቂያ ተናገር። ረዥምና ደማቅ ጭብጨባ ተሰማ!
የጧቱ ፕሮግራም ያበቃው ሃያ አራቱ ተማሪዎች ዲፕሎማቸውን ሲቀበሉ ነበር። ወደተለያዩ 12 አገሮች ለመሄድ ጉዞ ሊጀምሩ ነው። ክፍሉም የአስተዳደር አካሉንና የቤቴል ቤተሰብን በማመስገን የውሳኔ ቃል አቀረበ። በምሳ ሰዓት የመጠበቂያ ግንብ እርሻዎች ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ቻርልስ ጄ ራይስ አጭር የመጠበቂያ ግንብ ጥናት መራ።ከዚያም ምሩቃኑ በዎልክሂል ኒውዮርክ የአምስት ወር ኮርስ ላይ እያሉ በመስክ አገልግሎት ላይ ያጋጠሟቸውን ተሞክሮዎች በትያትር መልክ በማቅረብ ደማቅ ፕሮግራም አቀረቡ። ከዚያ በኋላ በአካባቢው ያሉ ጉባኤዎች የተውጣጡ አስፋፊዎች አሁን ፈጣሪያቸውን የሚያስታውሱ ወጣቶች በሚል ርዕስ ድራማ አቀረቡ።
ፕሮግራሙን ለመዝጋት የ95 ዓመት ዕድሜ የሆነው የአስተዳደር አካል አባል፣ ወንድም ጆርጅ ጋንጋስ ለይሖዋ የጋለና ቀስቃሽ የሆነ ጸሎት አቀረበ። አድማጮቹ በሙሉ ደስ ብሎአቸው ተመለሱ። እያንዳንዳቸው በዓለም አቀፍ የሰብል መሰብሰብ ሥራ ከምን ጊዜውም የበለጠ ድርሻ ለማበርከት እንደተነቃቁ ምንም ጥርጥር የለውም።
[በገጽ 22 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
የክፍሉ እስታትስቲክስ
የተወከሉ አገሮች ብዛት፦ 6
የተመደቡባቸው አገሮች ብዛት፦ 12
የተማሪዎች ብዛት፦ 24
ባልና ሚስት የሆኑ፦ 12
አማካኝ ዕድሜ፦ 33.4
በእውነት ውስጥ የቆዩበት ዓመት ርዝመት በአማካይ፦ 16.13
በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የቆዩበት ዓመት መጠን በአማካይ፦ 11.3
[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የመጠበቂያ ግንብ የጊልያድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት የ91ኛው ኮርስ ተመራቂዎች
ከታች ባለው ዝርዝር የመስመሮቹ ቁጥር የተሰጠው ከፊት ጀምሮ ወደኋላ ሲሆን በእያንዳንዱ መስመር ያሉት ሰዎች የተዘረዘረው ከቀኝ ወደ ግራ ነው።
(1) ማክደውል ኤ፤ ያንግኪስት ኤል፤ ሾካን ቢ፤ ዋርግኒየር ኤን፤ ሚለር ዋይ፤ ሚዮኖዝ ኤም፤ (2) ቤልስ ኤም፤ ፔሬዝ ዲ፤ አቲክ ኢ፤ ቫይኒካይነን ኤ፤ ምስትበርግ ኬ፤ (3) ደ ፕሪስት ዲ፤ ደ ፕሪስት ቲ፤ ፔሬዝ አር፤ ዋርግኒየር ጄ፤ ሚዮኖዝ ጄ፤ ሚለር ጄ፤ (4) ማክደወል ኤስ፤ ቤልስ ዲ፤ ሾካን ኤም፤ አቲክስ ሲ፤ ያንግኪስት ደብልዩ፤ ቫይንካይነን ጄ፤ ምስትበርግ ኤስ