የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 7/1 ገጽ 32
  • አምላክን የምንፈልግበት ጊዜ አሁን ነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክን የምንፈልግበት ጊዜ አሁን ነው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 7/1 ገጽ 32

አምላክን የምንፈልግበት ጊዜ አሁን ነው

በዚህ ገጽ ላይ ያለው ሥዕል በአንድ ወቅት የብዙ ወንድና ሴት አማልክት የአምልኮ ማዕከል የነበረው የአቴናውያን ግንብ ነው። ከግንቡ (አክሮፖሊስ) ስር ደግሞ በጥንት ጊዜ የፍርድ ችሎት ይሰማበት ነበር የሚባለው አሪዮስፋጎስ አለ። ከ2,000 ዓመታት ገደማ በፊት ሐዋሪያው ጳውሎስ የሚያስደንቅ ንግግር ያደረገው እዚህ ቦታ ነበር። ጳውሎስ በዚያ ቦታ ከተናገራቸው ቃላት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

“ምናልባት እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ፣ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፣ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም። . . . በእርሱ ሕያዋን ነንና እንኖርማለን።”—ሥራ 17:26-28

የሰው ዘር ሁሉ የጳውሎስን ቃላት ልብ ብሏቸው ቢሆን ኖሮ የሰው ልጅ ታሪክ ከአሁኑ የተለየ አቅጣጫ ይከተል ነበር። ሰዎች የሰው ወገን ሁሉ የተፈጠረው በአጽናፈ ዓለሙ ጌታ በይሖዋ መሆኑን ተገንዝበው ቢሆን ኖሮ በምድር ላይ የተከሰቱት ጦርነቶችና መከራዎች ባልኖሩም ነበር።

ዛሬ የሰው ዘር በብሔራዊ ስሜት፣ በመደብ ልዩነቶች፣ በዘር ጥላቻዎችና በማኅበራዊ ደረጃዎች ተከፋፍሎአል። ይሁን እንጂ የጳውሎስ ቃላት አሁንም ቢሆን እውነትነታቸው አልቀነሰም። ሁላችንም ብንሆን በአምላክ ከተፈጠረው አንድ ሰው የመጣን ነን። በዚህም ምክንያት ሁላችንም ወንድማማቾችና እህትማማቾች ነን። አሁንም ቢሆን አምላክን የምንፈልግበት ጊዜ አላለፈም።

የጳውሎስ ቃላት ይበልጥ አጣዳፊ መሆናቸውን የምንገነዘበው የንግግሩን የመጨረሻ ቃላት ልብ ስንላቸው ነው። ጳውሎስ እንዲህ አለ፦ “ቀን ቀጥሮአልና፣ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጧል።”

የኢየሱስ ከሙታን መነሳት ሊታበል የማይቻል ታሪካዊ ሀቅ ነው። ጳውሎስም እንዳመለከተው ኢየሱስ ከሙታን መነሳቱ ወደ ፊት የሰው ዘሮች የሚፈረዱበት ጊዜ ለመኖሩ ዋስትና ይሆናል። ታዲያ ይህ የፍርድ ቀን መቼ ነው? ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ ቆሞ እነዚህን ቃላት ከተናገረ 2,000 ዓመታት አካባቢ እንደሆኑት እናውቃለን። በእርግጥም የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ የፍርዱ ቀን በጣም መቅረቡን ያመለክታል። በጣም አሳሳቢ የሆነ ነገር ነው! አምላክን በሙሉ ልባችን መፈለግ ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ አጣዳፊ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ጳውሎስ ለአቴና ሰዎች እንደተናገረው አምላክ “አሁን በየቦታቸው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል”!—ሥራ 17:30, 31

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ