የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 8/15 ገጽ 30
  • ታስታውሳላችሁን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳላችሁን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዓለማዊ ቅዠቶችን አስወግዳችሁ የመንግሥቱን እውነቶች ተከታተሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • መረቡና ዓሦቹ ለአንተ ምን ትርጉም ይኖራቸዋል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • “የተሰጡ” ሰዎች፣ የይሖዋ ዝግጅት ክፍል ናቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • “ከጭንቀት ቀን” ማን ያመልጥ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 8/15 ገጽ 30

ታስታውሳላችሁን?

በቅርቡ የወጡ የመጠበቂያ ግንብ እትሞችን በማንበብ ተደስታችኋልን? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ትችሉ እንደሆነ ተመልከቱ፦

▫ ናታኒምና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ከባቢሎን ምርኮ ሲመለሱ የተሰጧቸው ተጨማሪ የአገልግሎት መብቶች ለምን ነገር ጥላ ሊሆኑ ይችላሉ?

በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ ያሉት የመንፈሳዊ እሥራኤል ቀሪዎች በቁጥር እያነሱ ሲሄዱ ሌሎች በጎች ደግሞ እየጨመሩ ይሄዳሉ። ከእነዚህ በግ መሰል ሰዎች ውስጥ አንዳንዶቹ በናታኒምና በሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች እንደሆነው ሁሉ በቅቡዓኑ የበላይ ተመልካችነት ሥር ሆነው ከባድ ኃላፊነቶችን እንዲሸከሙ ተመድበዋል። (ኢሳይያስ 61:5)—4/15 ገጽ 16-17

▫ ነቢዩ ሶፎንያስ “ምናልባት በይሖዋ ቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል” ሲል ምን ማለቱ ነበር? (ሶፎንያስ 2:2, 3)

ማንኛውም ሰው በመጪው “ታላቅ መከራ” ወቅት ከለላ ማግኘቱ አንዴ የዳነ ለሁልጊዜ ዳነ በሚባለው ዓይነት አባባል አይደለም። (ማቴዎስ 24:13, 21) በዚያ ቀን መሰወር የሚመካው አንድ ሰው ሦስት ነገሮችን ማድረጉን በመቀጠሉ ላይ ነው። እነሱም ይሖዋን መፈለግ፣ ጽድቅን መፈለግና ትሕትናን መፈለግ ናቸው።—5/1፣ ገጽ 15-16

▫ ሚካኤል በ“ፍጻሜ ዘመን” “የሚቆመው” በምን መንገድ ነው? (ዳንኤል 12:1, 4)

ሚካኤል በሰማይ ንጉሥ ሆኖ ከተሾመበት ከ1914 ጀምሮ ስለ ይሖዋ ሕዝቦች “ቆሟል”። በቅርቡ ግን ሚካኤል በአንድ ልዩ መንገድ ይኸውም ከምድር ገጽ ላይ ማንኛውንም ክፋት ለማስወገድ የይሖዋ ወኪል በመሆንና የአምላክ ሕዝቦች አዳኝ በመሆን ይቆማል።—5/1፣ ገጽ 17

▫ እውነተኛ ደስታ የተመካው በምን ላይ ነው?

እውነተኛ ደስታ የተመካው ከይሖዋ ጋር ባለን ውድ ዝምድና፣ በሞገሱና በበረከቱ ላይ ነው። (ምሳሌ 10:22) ስለዚህ እውነተኛ ደስታ ለይሖዋ ከመታዘዝና ለፈቃዱም በደስታ ከመገዛት ውጭ አይገኝም። (ሉቃስ 11:28)—5/15 ገጽ 16, 19

▫ ኢየሱስ የመፈወስ ተአምራቱን ሲያከናውን በተፈዋሹ በኩል እምነት ያስፈልግ ነበርን?

ብዙዎች ለመፈወስ ወደ ኢየሱስ ለመምጣት መጠነኛ እምነት ያስፈልጋቸው ነበር። (ማቴዎስ 8:13) ይሁን እንጂ ኢየሱስ ተአምሩን እንዲፈጽምላቸው እምነት እንዳላቸው መግለጽ አያስፈልግም ነበር፣ ምክንያቱም ለምሳሌ ኢየሱስ እርሱ ማን መሆኑን ያላወቀውን አንድ ሽባ ሰው ፈውሶ ነበር። (ዮሐንስ 5:5-13) ኢየሱስ ሊይዙት ከመጡት ከጠላቶቹ መካከል የነበረውን የሊቀ ካህናቱን ሎሌ ጆሮ እንኳን ሳይቀር ፈውሷል። (ሉቃስ 22:50, 51) እነዚህ ተአምራት የተፈጸሙት በአምላክ መንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው እንጂ በታማሚው ግለሰብ እምነት ምክንያት አልነበረም።—6/1፣ ገጽ 3

▫ ኢየሱስ በማቴዎስ 13:47-50 ላይ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ የተገለጸው “መረብ” የሚያመለክተው ምንድን ነው?

“መረቡ” የሚያመለክተው የአምላክ ጉባኤ ነኝ የሚልና “ዓሣ” የሚሰበስበውን ምድራዊ መሣሪያ ነው። እርሱም ሕዝበ ክርስትናንና የቅቡዓን ክርስቲያኖችን ጉባኤም ጭምር ያጠቃልላል። ሆኖም የቅቡዓን ክርስቲያኖች ጉባኤ ከማቴዎስ 13:49 ጋር በመስማማት በመላእክት መሪነት ‘መልካሙን ዓሣ’ መሰብሰባቸውን ቀጥለዋል።—6/15፣ ገጽ 20

▫ በእሥራኤል የነበሩ ዳኞች የዳኝነት ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ በሥራ ሊያውሉ የሚገቧቸው አንዳንዶቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች ምን ነበሩ?

ለሀብታምና ለድሃ እኩል ፍትሕ መስጠት፣ ጥብቅ የሆነ ያለማዳላት ጠባይና ጉቦን አለመቀበል ነበሩ። (ዘሌዋውያን 19:15፤ ዘዳግም 16:19)—7/1፣ ገጽ 13

▫ ሽማግሌዎች ለዳኝነት ሲቀመጡ ምን ለማግኘት መጣር ይኖርባቸዋል?

አንዱ ዓላማ ስለ ጉዳዩ እውነቱን ለማወቅ ሲሆን ይህም በፍቅር መደረግ አለበት። እውነቱ ከታወቀ በኋላ ሽማግሌዎቹ ጉባኤውን ለመጠበቅና በውስጡም የይሖዋን ከፍተኛ የሥነ ምግባር ደረጃዎች ለማስከበርና የአምላክ መንፈስ ቅዱስ ያለምንም እገዳ እንዲፈስ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው። ሽማግሌዎቹ ጉዳዩን ማጣራታቸው ከተቻለ በአደጋ ላይ ያለውን ኃጢአተኛ ለመርዳትም ጭምር ነው። (ከሉቃስ 15:8-10 ጋር አወዳድር።)—7/1፣ ገጽ 18-19

▫ ከሕገ ወጥ የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት ጋር ተዛምዶ ባላቸው የቁም ቅዠቶች በሐሳብ መጫወት በጣም ጎጂ የሆነው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ በማቴዎስ 5:27, 28 ላይ በተናገራቸው ቃላት መሠረት ሁልጊዜ ለፆታ ግንኙነት የቁም ቅዠቶች የሚገዙ ሰዎች በልባቸው ዝሙት ፈጽመዋል። ስለዚህ እነዚህ የቁም ቅዠቶች ወደ ፆታ ብልግና ሊያደርሱ ስለሚችሉ እውነተኛ አደጋ አላቸው።—7/15፣ ገጽ 15

▫ ችግሮቻችንን በተገቢው አስተያየት እንድንመለከታቸውና ብሎም እንድንታገሣቸው ይሖዋ ሊረዳን የሚችለው በምን መንገዶች ነው?

በአማኝ መሰሎቻችን አማካኝነት ወይም መጽሐፍ ቅዱስ በምናጠናበት ጊዜ ችግሮቻችንን እንዴት ማየት እንዳለብን የሚያመለክቱ ጥቅሶች ወደ አእምሮአችን ሊመጡ ይችላሉ። በአምላክ መሪነት የተደረጉ ሁኔታዎች ምን ማድረግ እንዳለብን እንድናውቅ ሊረዱን ይችላሉ። መላእክት እኛን በመምራት ተካፋይነት ሊኖራቸው ይችላል፣ ወይም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት አመራር እንቀበል ይሆናል።(ዕብራውያን 1:14)—7/15፣ ገጽ 21

▫ በ325 እዘአ በኒቂያ የተደረገው ጉባኤ የሥላሴን መሠረተ ትምህርት መሥርቷል ወይም አጽድቋልን?

አልመሠረተም ወይም አላጸደቀም። ምክንያቱም የኒቂያ ጉባኤ ወልድና አብ “በባሕርይ አንድ” ናቸው። በማለት ወልድን ከአብ ጋር ያስተካከለ ብቻ ነበር። አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድነት በሦስትነት ያላቸው እያንዳንዳቸው እውነተኛ አምላክ ናቸው የሚለው ሐሳብ በዚያ ጉባኤም ሆነ በቀደሙት የቤተ ክርስቲያን አባቶች ተብለው በሚጠሩት ዘንድ አልተስፋፋም ነበር።—8/1፣ ገጽ 20

▫ ኢዮብ በኖረበት ዘመን ለይሖዋ ታማኝ የነበረ ሰው እርሱ ብቻ ነበርን? (ኢዮብ 1:8)

አልነበረም፤ መጽሐፈ ኢዮብ ራሱም ኤሊሁ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንደነበረው ያመለክታል። እንደዚሁም ኢዮብ በኖረበት ዘመን በግብፅ ይኖሩ የነበሩ ብዙ እሥራኤላውያን ነበሩ፤ ስለዚህ እነዚያ ሁሉ ሰዎች ለአምላክ ታማኞች ያልነበሩና ተቀባይነት አላገኙም ብለን የምናስብበት ምክንያት የለም።—8/1፣ ገጽ 31

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ