አንድነት ካለው የወንድማማች ማኅበር ጋር ተቀላቀሉ
ነገሩ የተከናወነው ነሐሴ 7, 1993 በዩክሬን ሪፑብሊክ በኪየቭ ከተማ በሚገኘው ስታዲየም ነበር። ከ64,000 በላይ የነበሩት ተሰብሳቢዎች ይህ ሁኔታ የሚፈጸምበትን ጊዜ መድረስ በጉጉት ይጠባበቃሉ። ከዚያም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩት ሰዎች ለቀረቡላቸው በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሁለት ጥያቄዎች “ዳ !” (“አዎ!”) በማለት ጮክ ብለው መለሱ። በዚህ መንገድ ስለ እምነታቸው በሕዝብ ፊት ምሥክርነት ከሰጡ በኋላ በስታዲየሙ ውስጥ ከሚገኙት ስድስት የመጠመቂያ ገንዳዎች ወደ አንዱ እየሄዱ በመጠመቅ ራሳቸውን ለይሖዋ አምላክ የወሰኑ መሆናቸውን አሳዩ።—ማቴዎስ 28:19
በዚህ የ“መለኮታዊ ትምህርት” ብሔራት አቀፍ የይሖዋ ምሥክሮች ሦስተኛ የስብሰባ ቀን ላይ የተገኙት ሰዎች አንድ በጣም ትልቅ ነገር ሲከናወን ማለትም የአንድ የተከፋፈለ ቤተ ክርስቲያን አባል ለመሆን ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድነት ያለው የክርስቲያን ጉባኤ አባል ለመሆን 7,402 ሰዎች ሲጠመቁ ተመልክተዋል።
ስለ እውነተኛው ክርስቲያናዊ አንድነት የበለጠ ለማወቅ የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ የፖ. ሣ. ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ ብለው ወይም በገጽ 2 ላይ ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉልን።